ውክፔዲያ:Today's featured article/ሓምሌ 10, 2010

ከውክፔዲያ
የመሬት ውስጣዊ ክፍል

መሬት ከፀሐይ ባላት ርቀት ሶስተኛ (3ኛ) በግዝፈት ደግሞ ከፕላኔቶች ሁሉ አምስተኛ ግዙፍ የሆነች ፈለክ (ፕላኔት) ናት። በግዝፈት እና በይዘት ቋጥኛዊ ይዘት ካላቸው ወይንም በእንግሊዝኛው ተሬስትሪያል ፕላኔቶች ከሚባሉት የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች። በተለምዶ ዓለም ወይም ምድር እየተባለች ትጠራለች። በሳይንሳዊ የተለምዶ ስም ደግሞ «ሰማያዊዋ ፕላኔት» እየተባለች ትጠራለች። ይህች ፕላኔት የሰው ልጅን ጨምሮ ለብዙ ሚሊዮን ዝርያዎች መኖሪያ ናት። ከምድር ብዛት (ከላይ አፈር) አትክልት ሁሉ እየበቀሉ ሲሆን ለሰው ልጅና ለእንስሳ ያስፈለጉት እህል፣ ፍራፍሬ፣ መድኃኒቶችና ሌሎችም ሁሉ ታስገኛለች። ይህም የታወቀች ብቸኛዋ ህይወት ያለው ነገር መኖሪያ ያደርጋታል። ስለዚህ ነው በተለያዩ እምነቶች ዘንድ ምድራዊት እማማችን የተባለች። «አብርሃማዊ» በተባሉት ሃይማኖቶች (በተለይ ክርስትና፣ እስልምናና አይሁድና) ቅዱሳን መጻሕፍት እንደሚሊት፣ የመሬት እድሜ (ወይም ቢያንስ የተገኙባት ሕያዋን እድሜ) ከ7 ሺህ አመታት በላይ ብዙ አይሆንም። ከተፈጠረች ያስቆጠረችው አመት በውል ባይታወቅም ግን በጊዜያችን ባሉት ሳይንሳዊ ዘዴዎች ባኩል የመሬት አማካይ እድሜ ወደ 4.6 ቢሊዮን አመታት ገደማ ይጠጋል። ከዚያን ግዜ ወዲህ በ1 ቢሊዮን አመት ውስጥ ህይወት ያለው ነገር መኖር ጀመረ።