የብርሃን መወላገድ

ከውክፔዲያ
ብርሃን ትንሽ ቀዳዳ ውስጥ ሲያልፍ እንደሚወላገድ እሚያሳይ

ሞገዶች እንቅፋት ሲያጋጥማቸው፣ በእንቅፋቱ ዙርያ የመጠምዘም ባህርይ ያሳያሉ። ከዚህ በተጻራሪ የዕለት ተለት ተመክሯችን እንደሚያረጋግጥልን ብርሃን በቀጥተኛ መንገድ እንደሚጓዝ ነው። ነገር ግን በጥንቃቄ ስናስተውል ይሄ ሙሉ በሙሉ እውነት ሆኖ አናገኘውም። ለምሳሌ ያንድን ቁስ ጥላ ስንመረመር ከሁለት አይነት ጥላወች እንደተሰራ እንረዳለን። ። አንደኛው ክፍል በጣም ጭለማ ሲሆን፣ ሌላው ብዙ ሳይጨልም ደብዘዝ ያለ ሆኖ እናገኛለን። ብርሃን በቀጥታ መንገድ ከተጓዘ ለምን ሁለት አይነት ጥላ ሊኖር ቻለ?

ስለሆነም ብርሃን ምንጊዜም በቀጥታ መንገድ አይጓዝም። ይልቁኑ የብርሃን ጨረር ስል የሆነ ጠርዝ ሲያጋጥመው ወይም ጠባብ ክፍተት ውስጥ ሲገባ ይጎብጣል። ይህ ኩነት የብርሃን መወላገድ ይሰኛል። በጠባብ ቀዳዳዎች አጮልቀን ስንመለከት ነገሮች ተንጋደው የሚታዩት ስለዚህ ምክንያት ነው።