የናቡከደነጾር የምስል ሕልም
የናቡከደነጾር የምስል ሕልም ከትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 2 የተገኘ ምሳሌ ነው።
በምሳሌው ዘንድ፣ የባቢሎን ንጉስ 2 ናቡከደነጾር በሚመላለስ ቅዠት ይታወካል እሱን ግን ለማስታወስ አይችልበትም። ሕልሙን ካልነገሩትና ካላስተረጎሙለት በቀር የሕልም አስተርጓሚዎቹን በሞት ንብረታቸውንም በማጥፋት ዛቻ ጣለባቸው። ስላልተቻላቸው ግን የባቢሎን ጠቢባን ሁሉ እንዲሞቱ አዘዘ።
ዳንኤል ጠቢብ ስለሆነ ይህ ማለት እሱ ደግሞ እንዲጠፋ ሲሆን ወደ ንጉስ ሂዶ ሕልሙን ከነትርጉሙ እንዲናገርለት ጊዜ ይለምነዋል። ከዚያ በኋላ "የሰማይ አምላክ" ሕልሙን ከነትርጉሙ ለዳንኤል ገለጸ። ወዲያው ወደ ንጉስ ተመልሶ ሕልሙ "በኋለኛው ዘመን የሚሆነውን" እንደሚገልጽ ይናገራል።
ዳንኤል እንደሚገልጸው በናቡከደነጾር ሕልም አንድ ታላቅ ብሩህ ምስል ወይም ጣኦት በፊቱ ሲቆም አየ። የምስሉ ራስ ከጥሩ ወርቅ፤ ደረቱና ክንዱ ከብር፤ ሆዱ ከነሐስ፤ እግሮቹ ከብረት፤ የግር ጣቶቹም ግማሽ ከብረት ግማሽ ከሸክላ ተሠሩ። አንድ ዓለት በድንገት ታይቶ ከብረትና ከሸክላ የተሠሩትን የእግር ጣቶች ሲመታ ምስሉ አቧራ እስከሚሆን ድረስ ንጉስ በሕልሙ አየ። የዛኔ ንፋስ አቧራውን በትኖ ድንጋዩ ምድርን ሁሉ የሚሞላ ተራራ ሆነ።
ለንጉስ ሕልሙ ምን እንደ ሆነ ከነገረው በኋላ፣ ዳንኤል አስተረጎመለት። ናቡከደነጾር እራሱ፣ የባቢሎን ንጉስ፣ የምስሉ ወርቃማ ራስ ነው። ከባቢሎን በኋላ ሌላ የሚያንስ መንግሥት ይመጣል፣ ይህም የብረት ደረትና እጆች መሳይ ይሆናል። ከሱ ተከትሎ ሦስተኛ የናስ መንግስት ይነሣል፤ ከዚያም አራተኛው መንግሥት እንደሚጨምቅ ብረት ሌሎቹን ሁሉ ይገዛል። ነገር ግን ይህ አራተኛው መንግሥት ይከፋፈላል፤ በመጨረሻም ግማሽ ብረትና ግማሽ ሸክላ እንደ ነበሩት እግሮችና ጣቶች ይሆናል።
- "በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ለዘላለም የማይፈርስ መንግሥት ያስነሣል፤ ለሌላ ሕዝብም የማይሰጥ መንግሥት ይሆናል፤ እነዚያንም መንግሥታት ሁሉ ትፈጫቸዋለች ታጠፋቸውማለች፣ ለዘላለምም ትቆማለች።" (ቁ.44)
(ይህ ማለት ከተራራው ያለ እጆች የተቀረጸው ጣኦቱንም የሚሰባብረው ድንጋይ መሆኑን ይገለጻል።)
ብዙ ጊዜ ሊቃውንትና ጻፎች ይህንን ሲአስተርጉሙ 1ኛው መንግሥት ባቢሎን፣ 2ኛው ሜዶን፣ 3ኛው ፋርስ፣ 4ኛው መቄዶን (ታላቁ እስክንድር) እንደ ሆነ የሚል እምነታቸውን ይገልጻሉ። ጻፎቹ ይህንን የሚያስቡ ትንቢተ ዳንኤል በአንጥያኮስ አፊፋኖስ ዘመን በዳንኤል ስም በማይታወቅ ሌላ ደራሲ እንደተጻፈ ስለሚቆጥሩት ነው። ነገር ግን ወንጌልን የሚቀበሉት ክርስቲያኖች ይህንን የጻፎቹን ሀሳብ አይቀበሉም፤ ምክኒያቱም በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ኢየሱስ ስለ ዳኔል ከምጻት በፊት ስለሚመጣ ኋለኛው መከራ ዘመን የነበየ ነቢይ ይለዋል። ስለዚህ ከኢየሱስ አስቀድሞ በ200 አመት የኖረ አፊፋኖስ ሊያመልከት አይችልም። እንግዲህ የምስሉ ብረታብረቶች መታወቂያ በላይ ከተጠቀሱት ጻፎች ግምት በትንሽ ይለያያል። በዚሁ ፈንታ ሕልሙን ከናቡከደነጾር ጀምሮ ወደፊት የእግዚአብሐር ዘላለማዊ መንግሥት እስከምትቆም ድረስ ስለ ባቢሎንና በባቢሎን መንገድ ስለሚከተሉት መንግሥታት አደረጃጀት የሚነካ ሕልም ይቆጥሩታል።
የወርቃማ ራስ መታወቂያ በማንም አይከራክርም፤ በመጽሐፉ ናቡከደነጾርና የባቢሎን መንግሥት መሆኑ ግልጽ ነውና። ነገር ግን በዚህ አሳብ፡ የብር ደረት የመሰለው 2ኛው መንግሥት ፋርስ ነው እንጂ ሜዶን አይሆንም። እንዲያውም ሜዶን በታሪክ ባቢሎንን መቸም ስላልተከተለው ነው፤ ፋርስ ግን በውነት ባቢሎንን ተከተለው። እንዲሁም ሦስተናው የነሃስ ሆድ የሆነው መንግሥት የእስክንድር ግሪክ መንግሥት እንደ ሆነ ይታስባል። ይህ ማለት አራተኛው የብረት እግሮች መንግሥት ሮማ መሆን አለበት። የብረትና የሸክላ ጣቶች ትርጉም ደግሞ ምናልባት ከሮማ መንግስት አመዶች የተነሱ አገሮች እንደሚሆኑ አንዳንዴ ይባላል፤ እነዚህም መጨረሻው (ድንጋዩ ወይም የእግዚአብሐር መንግሥት) ሲደርስ የሚገዙት አገሮች ይሆናሉ።
ጻፎቹ ትንቢተ ዳንኤል ከአንጥያኮስ ዘመን እንደ ሆነ ካላቸው ሀሳብ ውጭ፤ ምእራፉ እራሱ በናቡከደነጾር ሁለተኛው አመት እንደ ሆነ ይላል። ይህ በባቢሎን ላይ የነገሰው 2ኛው አመት 612 ዓክልበ. ሊሆን ይችላል፤ አለዚያ ጽድቅያስን ከዙፋኑ አውርዶ በይሁዳ ላይ የነገሰው 2ኛው አመት 595 ዓክልበ. ሊሆን ይችላል።