የአእምሮ እድገት ውስንነት
የአእምሮ እድገት ውስንነት | |
---|---|
Classification and external resources | |
![]() በተደጋጋሚ እቃዎችን መደርደር እና ረድፍ ማስያዝ ከአእምሮ እድገት ውስንነት ጋር ተያይዞ ይነሳል፡፡ | |
Patient UK | የአእምሮ እድገት ውስንነት |
ማህበራዊ መስተጋብሮች እና ግንኙነቶች ላይ ባለ እክል እንዲሁም በተገደበ እና ተደጋጋሚ በሆነ ባህሪ የሚገለፅ የእድገት መዛባት ነው፡፡[1] ወላጆች አብዛኛው ጊዜ ይህን ምልክት በልጆቻቸው የመጀመሪያዎቹ 3 አመቶች ላይ ያስተዋላሉ፡፡[2] ] እነዚህ ምልክቶች አብዛኛው ጊዜ በጊዜ ሂደት እየጎሉ የሚመጡ ቢሆንም፤ አንዳንድ በአእምሮ እድገት ውስንነት የሚጠቁ ልጆች ግን በመደበኛ የእድገት ሂደት ውስጥ እያሉ የግንኙነት እንዲሁም በማህበራዊ መስተጋብር ክህሎታቸው ሊቀንስ ይችላል፡፡[3]
የአእምሮ እድገት ውስንነት ከዘር ወደ ዘር መተላለፍ እንዲሁም ከአካባቢው ምክንያቶች ጋር ይያያዛል፡፡[4] በእርግዝና ወቅት ሊኖሩ የሚችሉ እንደ ኩፍኝ፣ እንደ ቫልፕሮይክ አሲድ፣ አልኮል፣ ኮኬን፣ ፀረ-ተባይ እንዲሁም ሊድ ያሉ ጎጂ ንጥረ ነገሮች መጋለጥ እንዲሁም የአየር ብክለት፣ የፅንሱ እድገት መገደብ እንዲሁም ራስን በራስ የመከላከል የጤና መዛባት ያሉ ነገሮች የአእምሮ እድገት ውስንነትን የመከሰት እድል ሊጨምሩ ይችላሉ፡፡[5][6][7] እንደክትባት ያሉ አንዳንድ አካባብያዊ ምክንያቶች የአእምሮ እድገት ውስንነት መንስኤ ሊሆኑ ይችላል የሚለው መላምት ውሸት እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡[8] የአእምሮ እድገት ውስነንት የአእምሮን መረጃን የመሰብሰብ እና የማዋቀር ሂደትን እንዲሁም የነርቭ ህዋሳት እና መጋጠሚያዎች የሚጋጠሙበትን እና የሚሰሩበትን ሂደት ያዛባል፤ ይሄ እንዴት እንደሚሆን ግን እስካሁን ግልፅ በሆነ መልኩ አልተረዳነውም፡፡[9] ዲያግኖስቲክስ እና ስታትስቲካል ማንዋል ኦፍ ሜንታል ዲሶርደርስ (ዲ.ኤስ.ኤም-5) የአእምሮ እድገት ውስንነትን እና፤ ልክ እንደ አስፐርገር ሲንድረም እንዲሁም በሌላ መንገድ ያልተገለፀ የተንሰራፋ የእድገት መዛባት (ፒ.ዲ.ዲ-ኤን.ኦ.ኤስ) ያሉ መለስ የአእምሮ እድገት ውስንነት አይነቶችን ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር (ኤ.ኤስ.ዲ) በሚለው ምረመራ ውስጥ ያካትታቸዋል፡፡[10]
ቀደም ብሎ የሚደረግ የባህሪ መዛባት ህክምና ወይም የንግግር ህክምና የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ልጆች ራሳቸውን እንዲንከባከቡ እንዲሁም የተሻለ የማህበራዊ እና ከሰዎች ጋር ያለ የግንኙነት ክህሎት እንዲኖራቸው ይረዳቸዋል፡፡[11][12] ምንም እንኳን የታወቅ ፍቱን መድሃኒት ባይኖረውም[11]]አንዳንድ ግን ያገገሙ ልጆች እንዳሉ የህክምናው ማህደር ያሳያል፡፡[13] አንዳንድ በአእምሮ እድገት ውስንነት የተጠቁ አዋቂዎች ለብቻቸው መኖር አይችሉም፡፡[14] የአእምሮ እድገት ውስንነትን በተመለከተ ሁለት ሃሳቦች ዳብረዋል፤ አንዳንድ ሰዎች ፍቱን የሆነ መፍትሄ እየፈለጉለት ሲሆን ሌሎች ደግሞ የአእምሮ እድገት ውስንነትን እንደልዩነት ተቀብለን መቀጠል አለብን ይላሉ፡፡ [15][16]
በአለም አቀፍ ደረጃ፣ በ2015 በተደረገው ጥናት 24.8 ሚሊየን ሰዎች የአእምሮ እድገት ውስንነት ተጠቂዎች ናቸው፡፡[17] በ 2000ዎቹ አመተምህረት ውስጥ በአለም ላይ ካሉ 1000 ሰዎች ከ1 እስከ 2 ሰዎች በዚህ ይጠቁ ነበር፡፡[18] Iበ2017 አመተ ምህረት በተሰራው ጥናት ባደጉት ሃገራት ውስጥ ካሉት ልጆች ውስጥ 1.5% በኤ.ኤስ.ዲ የተጠቁ ናቸው[19]በ2000 ከነበረው 0.7% ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚገኙ ነበሩ [20] ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ላይ ከ4 እስከ 5 እጥፍ ይከሰታል፡፡[20] በዚህም የተጠቁ ሰዎች ከ1960 ጀምሮ ባለው አመተምህረት በአስገራሚ ሁኔታ ጨምሯል፤ ይሄም ሊሆን የቻለው ምናልባት የህክምናውም ሂደተ ስለተለወጠ ሊሆን ይችላል፡፡[18] በአእምሮ እድገት ውስንነት የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በእርግጥ ጨምሯል ወይ? የሚለው መልስ የሚሻ ጥያቄ ነው፡፡[18]
- ^ American Psychiatric Association, ed (2013). "Autism Spectrum Disorder, 299.00 (F84.0)". Diagnostic and Statistical Manual of Mental Disorders, Fifth Edition. American Psychiatric Publishing.
- ^ "Diagnosis of autism spectrum disorders in the first 3 years of life". Nat Clin Pract Neurol 4 (3): 138–147. 2008. doi:10.1038/ncpneuro0731. PMID 18253102.
- ^ "Regression in autistic spectrum disorders". Neuropsychol Rev 18 (4): 305–319. 2008. doi:10.1007/s11065-008-9073-y. PMID 18956241.
- ^ "Autism risk factors: genes, environment, and gene-environment interactions". Dialogues in Clinical Neuroscience 14 (3): 281–292. 2012. PMID 23226953.
- ^ "Prenatal factors associated with autism spectrum disorder (ASD)". Reproductive Toxicology 56: 155–169. 2015. doi:10.1016/j.reprotox.2015.05.007. PMID 26021712.
- ^ "Neurodevelopment: The Impact of Nutrition and Inflammation During Preconception and Pregnancy in Low-Resource Settings". Pediatrics 139 (Suppl 1): S38–S49. 2017. doi:10.1542/peds.2016-2828F. PMID 28562247.
- ^ "Pathophysiology of autism spectrum disorders: revisiting gastrointestinal involvement and immune imbalance.". World J Gastroenterol 20 (29): 9942–9951. 2014. doi:10.3748/wjg.v20.i29.9942. PMID 25110424.
- ^ "Incidence of autism spectrum disorders: changes over time and their meaning". Acta Paediatr 94 (1): 2–15. 2005. doi:10.1111/j.1651-2227.2005.tb01779.x. PMID 15858952.
- ^ "Autism". Lancet 374 (9701): 1627–1638. 2009. doi:10.1016/S0140-6736(09)61376-3. PMID 19819542.
- ^ "Identification and evaluation of children with autism spectrum disorders". Pediatrics 120 (5): 1183–1215. 2007. doi:10.1542/peds.2007-2361. PMID 17967920.
- ^ ሀ ለ Management of children with autism spectrum disorders. 120. November 2007. pp. 1162–1182. https://pediatrics.aappublications.org/content/120/5/1162 በ2020-08-06 የተቃኘ.
- ^ Autism Spectrum Disorder: Primary Care Principles. 94. December 2016. pp. 972–979.
- ^ Can children with autism recover? If so, how?. 18. December 2008. pp. 339–366. https://www.academia.edu/16961306 በ2020-08-06 የተቃኘ.
- ^ A systematic review and meta-analysis of the long-term overall outcome of autism spectrum disorders in adolescence and adulthood. 133. June 2016. pp. 445–452.
- ^ Fieldwork on another planet: social science perspectives on the autism spectrum. 3. pp. 325–341.
- ^ Frith, Uta (October 2014). "Autism – are we any closer to explaining the enigma?". The Psychologist (British Psychological Society) 27: pp. 744–745. Archived from the original on 2023-03-15. https://web.archive.org/web/20230315141155/https://thepsychologist.bps.org.uk/volume-27/edition-10/autism-are-we-any-closer-explaining-enigma በ2025-05-21 የተቃኘ.
- ^ Global, regional, and national incidence, prevalence, and years lived with disability for 310 diseases and injuries, 1990–2015: a systematic analysis for the Global Burden of Disease Study 2015.
- ^ ሀ ለ ሐ The epidemiology of autism spectrum disorders.
- ^ The changing epidemiology of autism spectrum disorders.
- ^ ሀ ለ "ASD data and statistics". CDC.gov.