የአገራት ኮመንዌልዝ

ከውክፔዲያ
የኮመንዌልዝ አባላት። ሰማያዊ፦ እስካሁን የንግሥት ኤልሳበጥ ግዛት የሆነ፤ አረንጓዴ፦ ሌላ (የራሱን) ንጉሥ ያለው አባል፤ ቀይ፦ ምንም ንጉሥ የሌለው (ሪፐብሊክ የሆነ) አባል።

የአገራት ኮመንዌልዝ (እንግሊዝኛ፦ Commonwealth of Nations) የኢንተርናሽናል አገራት ስምምነት ማኅበር ነው። አሁን 53 አባላት አገራት አሉት።

እነዚህ አገራት በተለይ በታሪክ የዩናይትድ ኪንግደም ግዛቶች ነበሩ። ብዙዎቹ ግን አሁን የራሳቸው መንግሥት አላቸው፤ አንዳንዶቹም እስካሁን የዳግማዊት ንግሥት ኤልሳበጥ ግዛቶች ሆነው ቀርተዋል።

1942 ዓም የተመሠረተ የኢንተርናሽናል መንግሥታት ባህልና ምጣኔ ሀብት ስምምነት ወይም ጓደኝነት ነው።