የካቲት ፲፮
Appearance
(ከየካቲት 16 የተዛወረ)
የካቲት ፲፮፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፷፮ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፶፩ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፺፱ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በግራትዚያኒ የሚመራ የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት በዝዋይ አካባቢ የጦር አዝማቾቹን የራስ ደስታ ዳምጠውን እና የደጃዝማች በየነ መርድን አርበኞት ድል አደረጉ። ሁለቱም ኢትዮጵያውያን አዝማቾች ሕይወታቸውን በዚህ ዕለት ሰዉ። ኢጣሊያውያኑ ራስ ደስታን ከያዟቸው በኋላ በጥይት ደበደቧቸው፡፡
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም ኢትዮጵያ ላይ በፈነዳው አብዮት አስገዳጅነት የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የሕዝቡን ሸክም ለማቃለል የነዳጅ ዋጋ ቅነሳን የሚያካትት ኤኮኖሚያዊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ይፋ አደረገ።
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - የግራዚያኒ ሠራዊት በአሩሲና በማረቆ ላይ ትልቅ ጦርነት አድርጎ፣ ራስ ደስታ ዳምጠው እና አብረዋቸው የነበሩትን የጦር አለቆች ማርኮ በዚህ ዕለት በፋሺስቶች እጅ ተገደሉ። [1]
- ^ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ (፲፱፻፷፭ ዓ/ም)፤ ገጽ ፪፻፲፭
- ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፤ "ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ" (፩ኛ መጽሐፍ)፤ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት (፲፱፻፷፭ ዓ/ም)
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |