የካቲት ፫

ከውክፔዲያ
(ከየካቲት 3 የተዛወረ)
Jump to navigation Jump to search

የካቲት ፫ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፶፫ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፲፫ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፲፪ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ፲፰፻፵፯ ዓ/ም - ደጃዝማች ካሳ (ዓፄ ቴዎድሮስ)ና ደጃዝማች ውቤ ቧሂት ላይ ድንኳን ተክለው ተገናኙ። ደጃዝማች ካሳም የእንግሊዙን ሊቀ መኳስ ዮሐንስን (John Bell)በመንጥር አይተህ ንገረኝ አሉት። የሸማ ድንኳን ባየ ጊዜ ነገራቸው። ደጃዝማች ካሳም «አያሳድረኝ አላሳድረውም» ብለው ተናገሩ። ያንጊዜውንም ተነሣ አሉ። ባሰለፉትም ጊዜ እንዴህ ብለው በፍከራ ትንቢት ተናገሩ። «እንኳን ይህን ቁርጥማታም ወሎን፣ መትቼ የሻዋውን ንጉሥ እይዘዋለሁ። ስሜን ስሜን እንግርሀለሁ ያልሁህ ወታደር ስሜም ቴዎድሮስ ነው» አሉ። አስቀድሞ ገና በንጉሥ አምላክ በል። ስሜን ስሜን እነግርሀለሁ ብለው ነበርና። ያንጊዜውን እንዴህ አሉ። «ወታደር አይዞህ አትፍራ። የውቤ ነፍጥ የውቤ ነፍጥ ቢልህ የተለጎመው ጨርቅና ባሩድ ነው። አይነካህም» አሉት። እኔ የክርስቶስ በርያ ሁሉንም አሳይሀለሁ ወታደር ባሉ ጊዜ ሰልፍ ገጠመ። ደጃች ውቤም ተያዙ።

ልደት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕለተ ሞት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • የቴዎድሮስ ታሪክ፣ በብርሊን እንደሚገኝ አብነት፣ አሳታሚው ዶክቶር እኖ ሊትመን። በ፲፱፻ ወ ፪ ዓመት


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ