ዶቅማ
Appearance
(ከዶክማ የተዛወረ)
ዶቅማ Syzygium guineense በአፍሪቃ አህጉር የተገኘ ዛፍ ሲሆን፣ በኢትዮጵያም እንዲሁ ይገኛል። ዛፉ እስከ 30ሜትር ቁመት ሊኖረው የሚችል ግዙፍ ተክል ነው። «ዶቅማ አብዛኛውን ጊዜ ወንዝ ዳርን ተንተርሶ በቆላ የአየር ንብረት የሚበቅል ሃገር በቀል ዛፍ ነው። ያልቀላው የዶቅማ ፍሬ ቅጠል መሰል ሲሆን የቀላው ደግሞ ጠቆር ያለ እና የመርዝ ዛፍን አሊያም የቡናን ፍሬ ይመስላል። የዶቅማ ፍሬ እጅግ የሚጣፍጥና ቢበሉት የማይሰለች ነው። በተለይም ወደ ጫካ ለተለያየ ስራ የሚጓዙ ሰዎች የዶቅማን ዛፍ ጥላ አረፍ ይሉበትና ፍሬውን ይመገቡታል። ለዱር አራዊትና አዕዋፋትም ቢሆን ተመራጭ ምግባቸው ነው እንጅ» [1]
- ^ የጎንጅ ቆላላ ወረዳ የሕዝብ ግንኙነት