ጀምስ ፒስ

ከውክፔዲያ

ኬኔዝ ጀምስ ፒስ (በእንግሊዝኛKenneth James Peace)፣ ልደት (እ.ኤ.አ) ሴፕቴምበር 28፣ 1963 (መጋቢት ፲፯ ቀን ፲፱፻፶፮ ዓ.ም.)፣ ፔይስሌይ (በእንግሊዝኛPaisley)፣ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ፒያኖ ተጫዋች እና ቪዡዋል አርቲስት (የሥነ /ጥበብ ባለሙያ) ነው።

ጀምስ ፒስ በዊስባደን ውስጥ

የሕይወት ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጅምስ ፒስ[1][2] የተወለደው እንደ አውሮጳውያን አቈጣጠር (እ.ኤ.አ) ሴፕቴምበር 28፣ 1963  በፔይስሌይ፣ ስኮትላንድ (በእንግሊዝኛScotland) ውስጥ ነው።[1] አብዛኛውን የልጅነት ጊዜውን ያሳለፈው በምዕራብ ስኮትላንድ በምትገኝ ትንሽ የባሕር ዳርቻ የጎብኚዎች መዳረሻ በሆነችው በሄለንስበርግ (በእንግሊዝኛHelensburgh) ውስጥ ነው። ከቤተሰቦቹ መካከል ብዙ ከያኒያን አሉ (ለምሳሌ፣ ጆን ማክጊ፣ በእንግሊዝኛJohn McGhie)። ከሙዚቃ አቀናባሪው ከፌሊክስ ባርንስ (በእንግሊዝኛFelix Burns) ጋርም ይዛመዳል።[1][3] ከስምንት ዓመቱ ጀምሮ የፒያኖ ትምህርትን ተምሯል። የመጀመሪያውን ሕዝባዊ ትእይንት ያደረገው፣ በአሥራ አራት ዓመቱ የስኮት ጃፕሊንን (በእንግሊዝኛScott Joplin) ሙዚቃ በተጫወተ ጊዜ ነበር። ከዚያም ከአንድ ዓመት በኋላ፣ ደምበርተን (በእንግሊዝኛDumbarton) በሚገኘው የቅዱስ አንድሪው ቤተክርስቲያን ውስጥ የፒያኖ ተጫዋች ሆኖ ተሰየመ። በአሥራ ስድስት ዓመቱ፣ (አሁን የስኮትላንድ ሮያል ኮንስርቫቶር [በእንግሊዝኛRoyal Conservatoire of Scotland] በሚባለው) በሮያል ስኮቲሽ የሙዚቃ እና የድራማ አካዴሚ ውስጥ በትምህርት ቤቱ ታሪክ በዕድሜ ትንሹ የሙሉ ጊዜ ተማሪ በመሆን መማር ጀመረ። እ.ኤ.አ በ1983 እ.ኤ.አ ከግላዝጎ (በእንግሊዝኛGlasgow) ዩኒቨርሲቲ  በመጀመሪያ (በእንግሊዝኛB.A.) ዲግሪ ተመረቀ።[4][5] በቀጣዩ ዓመት፣ የመንደልሰንን (በጀርመንኛ፦ Mendelssohn) ፒያኖ ኮንሴርቶ ቁጥር 1ን፣ ከአር.ኤስ.ኤ.ኤም.ዲ ኦርኬስትራ ጋር በመጫወት በሙዚቃዊ ትወና ዲፕሎማ አገኘ።[1] መደበኛ ትምህርቱን ከፈጸመ በኋላ፣ በፒያኖ ተጫዋችነቱ በጣም የሚፈለግ ሆኖ፣ ከ1988 – 1991 ድረስ በኤዲንቦሮ (በእንግሊዝኛEdinburgh) ውስጥ ኖረ።[1][3]

Tango Milonga op. 26
Tango XVIII by James Peace (James Peace, piano)

ጀምስ ፒስ በጀርመን (በጀርመንኛDeutschland)፣ ባድ ናውሐይም (በጀርመንኛBad Nauheim)፣ ውስጥ ከ1991 – 2009 (እ.ኤ.አ) ኖረ።[6][7][8] እ.ኤ.አ ከ1998 ጀምሮ ታንጎ ሙዚቃን አጥንቶ፣ የራሱን በታንጎ ሙዚቃ የተፀነሰ የፒያኖ ቅንብር የያዘ፣ “ታንጎ ስኮትቲሽ” (በእንግሊዝኛScottish Tango) የሚባል ሲዲ አዘጋጀ።[8][9] እ.ኤ.አ በ2002 የቪክቶሪያ የሙዚቃ አካዴሚ (በእንግሊዝኛVictoria College of Music) የክብር አባል ሆነ።[3][8] በዚያው ዓመት፣ በመስከረም ወር ወደ ሰሜን ጀርመን፣[[10] በኅዳር ደግሞ በሩቅ ምሥራቅ ውስጥ የሙዚቃ ድግስ ጉዞ አደረገ። በሆንግ ኮንግ ውስጥ የራሱን ታንጎ XVII ለመጀመሪያ ጊዜ ተጫወተ።[8][11][12]ቶክዮ ደግሞ የአይ ፒ.ዲ.ኤን (በእንግሊዝኛInternational Piano Duo Association) የክብር ሜዳሊያ ተሸለመ።[1][3][5][8][13]

በቀጣዮቹ ዓመታት የሙዚቃ ትእይንቶቹ በአውሮፓ ውስጥ ያተኮሩ ነበሩ። የራሱን ታንጎ በሚከተሉት ዋና ከተሞች ውስጥ አቀረበ፦ አምስተርዳምአቴና[14] በርሊን[15] ብራሰልስ፣ ሄልሲንኪሊዝቦንለንደንማድሪድ[16] ኦስሎ[17] ሬይክያቪክ[18] እና ቪየና

James Peace - Idylls Op.4b

በ2005 እ.ኤ.አ በፓሪስ ውስጥ ከሚገኘው «የሉቴሴ» አካዴሚዓለም አቀፍ ኅብረት (በፊረንሳይኛInternationale Académie de Lutèce) የወርቅ ሜዳሊያ ተሸለመ።[1][3] እ.ኤ.አ በ2008 ደግሞ የለንደን የሙዚቃ አካዴሚ (በእንግሊዝኛLondon College of Music) የክብር አባል ሆነ።[1]

በኤዲንብራ ውስጥ ለጥቂት ጊዜያት ከቆየ በኋላ፣[3]ቪስባድን (በጀርመንኛWiesbaden)፣ ጀርመን፣ ውስጥ ለመኖር እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2010 ወደ ጀርመን ተመለሰ።[1][2] በዚች ውብ ከተማ የሐሳብ ቀስቃሽነት በራሱ ሙዚቃ ላይ አጫጭር ፊልሞችን እንዲሠራ አደረገው። ይህም “ኬ. ጀምስ ፒስ ኢን ቪስባድን” (በእንግሊዝኛK. James Peace in Wiesbaden) የተሰኘውን ፊልም ይጨምራል።[19][20]    

ሽልማቶች እና ክብሮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

⁖ «የአግነስ ሚለር» ውድድር (በእንግሊዝኛAgnes Millar Prize for sight-reading) የመጀመሪያ ደረጃ ሽልማት። ግላዝጎ፣ 1983 (እ.ኤ.አ)[4]

⁖ እ.ኢ.ሲ ውድድር (በእንግሊዝኛEducational Institute of Scotland Prize for piano accompaniment)። ግላዝጎ፣ 1984 (እ.ኤ.አ)[4]

⁖ «ሲበለኡሲ» ወድድር (በእንግሊዝኛSibelius Essay Prize)። 1985 (እ.ኤ.አ)[4]

⁖ በዓለም አቀፍ የሙዚቃ ቅንብር ውድድር፣ ቲ.አይ.ኤም (በጣሊያንኛTorneo Internazionale di Musica)፣ ዲፕሎማ። ሮም፣ 2000 (እ.ኤ.አ)[1][2][5]

⁖ አይ.ቢ.ኤል.ኤ ፋውንዴሽን (በእንግሊዝኛIBLA Foundation)፣ ዲፕሎማ። ኒው ዮርክ፣ 2002 (እ.ኤ.አ)[1][2][5][13]

⁖ የከብር ሜዳሊያ፣ ይ.ፒ.ዲ.ኤ.፣ ቶክዮ፣ 2002 (እ.ኤ.አ)[1][2]

⁖ የወርቅ ሜዳሊያ፣ «የሉቴሴ» ዓለም አቀፍ ኀብረት። ፓሪስ፣ 2008 (እ.ኤ.አ)[1][2]

የሠራቸው ሥራዎች ዝርዝር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

⁖ የማለዳ ፍቅር ዝማሬ (በእንግሊዝኛ፦ Aubade)

⁖ ሥነ ሥርዓት ሰልፍ ፩ (በእንግሊዝኛ፦ Ceremonial March No.1)

⁖ ሥነ ሥርዓት ሰልፍ ፪ (በእንግሊዝኛ፦ Ceremonial March No.2)

⁖ ዝምተኛ እምባዎች (በእንግሊዝኛ፦ Silent Tears)

⁖ የመኸር ወርቅ (በእንግሊዝኛ፦ Autumn Gold)[21]

⁖ የተዘነጉ ቅጠላት (በእንግሊዝኛ፦ Forgotten Leaves)

⁖ ዘለዓለማዊ ዝማሬ (በእንግሊዝኛ፦ Eternal Song)[1]

⁖ ለኦቦ እና ለፒያኖ ሶናታ (በእንግሊዝኛ፦ Oboe Sonata)

⁖ ለጆርጂያ (በጂዮርጅኛ፦ საქართველოსთვის)

  ግጥሞች ፦ ታማሪ ጪክቫይድዝ፣ ዩራቢ ጪክቫይደዝ፣ ጀምስ ፒስ

⁖ የወደቀ ውሃ (በእንግሊዝኛ፦ The Waterfall)

⁖ ኢዲሊስ (በእንግሊዝኛ፦ Idylls)

⁖ ፳፬ ታኒጎዎች (በእንግሊዝኛ፦ 24 Tangos)[1][9][19][20]

⁖ ባላደ (በእንግሊዝኛ፦ Ballade)

የውጭ መያያዣዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

Souvenir de Buenos Aires, Op.29 Nr.3 (ሶቬኒዬር ደ ቡይነስ አይረስ፣ ኦፕ. 29፣ ቍ. 3)፣ Youtube

Autumn Gold op. 25 (ኦተምን ጎልድ ኦፕ. 25)፣ Youtube

Lento Lacrimoso op.10 (ሌንቶ ካክሪሞሶ ኦፕ. 10)፣ Youtube

ማጣቀሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Birgitta Lampert። “ዊዝ አውት ‘ፕሪክሊ’ ሳውንድስ”። Wiesbadener Tagblatt (ጋዜጣ በጀርመንኛ)፣  ፌብሩወሪ10 ቀን 2011 (እ.ኤ.አ)
  2. ^ Julia Anderton። “ታንጎ ላይክ ኤ ቢተርስዊት ስቶሪ”። Wiesbadener Kurier (ጋዜጣ በጀርመንኛ)፣ 24 ማርች 24 ቀን 2010 (እ.ኤ.አ)
  3. ^ Sabine Klein።  “ማይ ሚዩዚክ ኢዝ ላይክ ማይሰልፍ - ቬሪ ሮማንቲክ”። Frankfurter Rundschau (ጋዜጣ በጀርመንኛ)፣ 1992 እ.ኤ.አ፣ ውጤት 254፣ ገጽ 2
  4. ^ G. Müller። “ዘ ሶል ኦፍ ዘ ፒያኖ ዳንስስ ታንጎ”። Kulturspiegel Wetterau (ጋዜጣ በጀርመንኛ)፣ መይ17 ቀን 2001 (እ.ኤ.አ)
  5. ^ Deutsche Nationalbibliothek (ዶይቼ ናሲዮናል ቢብሊዮቴክ)። “ጀምስ ፒስ”
  6. ^ “ጀምስ ፒስ”። FRIZZ (የጀርመን መጽሔት)። ጃንዩዌሪ 2012 (እ.ኤ.አ)፣ ገጽ 5
  7. ^ Manfred Merz። “ኤ ቪርቱዎሲክ፣ ሴንሲቲቭሊ ከለርድ ሮማንቲክ ወርልድ”። Wetterauer Zeitung (ጋዜጣ በጀርመንኛ)፣ ኖቬምበር 12 ቀን 1992 (እ.ኤ.አ)
  8. ^ “ጀምስ ፒስ”። The Tango Times (ኒው ዮርክ መጽጤት)፣ 2002/2003። ውጤት 39፣ ገጽ 1፣2፣4 ኢና5
  9. ^ National Library of Scotland (ናሽናል ላይብራሪ ኦፍ ስኮትላንድ)። “Tango escocés”።
  10. ^ La Cadena (የደች መጽሔት)። ሴፕቴምበር ቀን 2002 (እ.ኤ.አ)፣ ገጽ5
  11. ^ TangoTang (የሆንግ ኮንግ ጋዜጣ)። ኦክተውበር 8 ቀን 2002 (እ.ኤ.አ)
  12. ^ “ጀምስ ፒስ”። South China Morning Post (ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት)፣ ኦክተውበር 9 ቀን 2002 (እ.ኤ.አ)
  13. ^ ይ.ፒ.ዲ.ኤ.፣ የሸሌማት ተሽላሚዎች 2002 (እ.ኤ.አ)
  14. ^ የኮንስርት ፕሮግራም ብሮሹር {Για σένα, Αγγεληκή}። ምርች 27 ቀን 2016 (እ.ኤ.አ)
  15. ^ Tangodanza (የደች መጽጤት)። ሙጤት 1/2002 እ.ኤ.አ
  16. ^ የስፔን ኮንስርት ጉብኝት “¡Feliz cincuenta cumpleaños!” (ሴፕቴምበር፣ 2013 እ.ኤ.አ)
  17. ^ Listen.no: Konsert: James Peace, Flygel. Munch Museum፣ ኦስሎ። ኦክቶብር 16 ቀን 2004 (እ.ኤ.አ)
  18. ^ Rikarður Ö. Pálsson። “Skozir Slaghörputangoár”። Morgunblaðið (በአይስላንድ ጋዜጣ)፣ ኦክቶበር 14 ቀን 2004 (እ.ኤ.አ)
  19. ^ National Library of Scotland (ስኮትሽ ናሽናል ሊብራሪ). “K. James Peace in Wiesbaden”
  20. ^ Deutsche Nationalbibliothek (ዶይቼ ናሲዮናል ቢብሊኦቴክ). “K. James Peace in Wiesbaden”
  21. ^ Schwäbische Post (ሽዌቢሸ ፖስት፣ የበጀርመን ጋዜጣ)። “ዘ ሳውንድ ኦፍ ዝ ቫዮሊን ሶርስ ኦቨር ዘ ኦርኬስትራ”። ጁን 4 ቀን 1994 (እ.ኤ.አ)