ገብርኤል ቀልድ አታውቅም እንዴ!

ከውክፔዲያ

የደብሩ አለቃ ዛፍ ቆራጮችን ይኮናተሩና ሥራው እየተካሄደ ሳለ የገብርኤል ዕለት ከቆራጮቹ አንዱ በጣም ረጅም ዛፍ ላይ ወጥቶ ቅርንጫፍ ሲመለምል፤ ክፉ ነፋስ ይነሳና ያን ረጅም ዛፍ እንደጭራሮ ያወናጭፈው ጀመር። የዚህ ሁኔታ መፈጠር እጅግ በጣም ያስደነገጠውና ያስፈራው ቆራጭ፤ «ወይኔ ሲያቀብጠኝ በገብርኤል ዕለት! ለዚያውም በደብር ውስጥ። ገብርኤል ተቆጥቶ ሊገለኝ ነው» እያለ ካለቃቀሰ በኋላ «እንዲያው ቅዱስ ገብርኤል! የዛሬን ያወጣኸኝ እንደሁ አሥር ብር አገባልሃለሁ» ብሎ ይሳላል።

ወዲያው ስለቱን ሲጨርስ ነፋሱ ጸጥ ረጭ ይልለትና ከዚያ ዛፍ ላይ እየተሽቀዳደመ ይወርዳል። ሁለት እግሮቹ መሬት ላይ ሲቆሙ የአሥር ብሩ ነገር ይከነክነውና «ኤጭ! እኔ ሠርቼ በላቤ ወዝ ነው የማድረው፤ ገብርኤልም ሠርቶ ይብላ» ብሎ ስለቱን ላለማግባት ወሰነ። ትዝ ቢለው ጊዜ ለካ መፋሱን እዚያ ረጅም ዛፍ ላይ ትቶት ወርዶ ኖሯል።

ፊቱን ወደሰማይ ዞር አድርጎ፤ የርብድብድ ፈገግታ እያሳየ «ምነው ገብርኤል ቀልድ አታውቅም እንዴ!» አለ ይላሉ።