ገዘሃራ ማርያም

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ገዘሃራ ማርያም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ገዘሃራ ማርያም
270px
ገዘሃራ ማርያም መልከም ምድር
ከፍታ 1326 ሜትር (4500 ጫማ)
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ 320 ህዝብ በግምት
  • ስፋት=350 ስኩዊር ኪ.ሜ
  • የአይር ሁኔታ=ወይና ዳጋ
  • የቦታ አቀማመጥ=ተራራማ
  • የህዝብ አሰፋፈር=የተራረቀ
ገዘሃራ ማርያም is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ገዘሃራ ማርያም

11°36′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°16′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

ገዘሃራ ማርያም በአማራ ክልል አዊ ዞን ከ[ፋግታ ለኮማ] ወረዳ ከአ/ቅዳም በደቡብ-ምእራብ አቅጣጫ 8.5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ልዩ የቀበሌ ሥፍራ ነች።

ገዘሃራ ማርያም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የእግዚኸሪያ ማርያም ገዳም አጭር ታሪክ እግዚኸሪያ ማርያም ገዳም አሁን የምትጠራበትን ስያሜ ከማግኘትዋ በፊት ድሃ ማርያም ተብላ ትጠራ እንደነበር የአካባቢው ቀደምት ነዋሪዎች ያስረዳሉ ፡፡ድሃ ማርያም ትባል የነበረውም ቤተክርስቲያኗ በጫካ የተከበበች ስለነበር ብዙ አስፈሪ ነብርና የመሳሰሉ የዱር አራዊት በጫካው ውስጥ ስለነበሩ እነኚህን በመፍራት ምዕመናን በቦታው ተገኝተው የማይንከባከቧት ፣በዳሰሳ ጎጂ ውስጥ የነበረች ስለነበረ ነው ይላሉ ፡፡ ድሃ ማርያም የተተከለችው ከ1860 ዓ.ም በፊት እንደነበረም ጨምረው ይገልፃሉ ፡፡ ከዚህ በኋላ አንድ አጋጣሚ ተፈጠረ ይላሉ ፡፡ ይኸውም አጼ ቴዋድሮስ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀሱ ስለነበር በአሁኑ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ወምበራ ወረዳ የግዛት አንድነትን ለማናጋት የተነሱ ኃይሎች በመኖራቸው ሰራዊታቸውን ይዘው ለዘመቻ ወደ ዚሁ ቦታ ጉዞ ሲያደርጉ ገዘኸራ ተብሎ ከሚጠራው ቀበሌ ድሃ ማርያም ቤተክርስቲያን ካለችበት ቦታ ፊት ለፊት ባለ መንገድ ሲደርሱ በቅሎቸው ትቆማለች አፄው በአለንጋ ቢመቷትም አልንቀሳቀስ ትላለች ፡፡ አፄውም ሙኒት ምንነካት ይሉና ወርደው በአካባቢው ያሉ አባቶችን አስጠርተው እዚህ አካባቢ ምን አለ በቅሎዬ አልሄድ አለች ብለው ጠየቋቸው፤ የአካባቢው ባለበትም ከዚህ ቦታ ፊት ለፊት ድሃ ማርያም የምትባል ተንከባካቢ የሌላት ቤተክርስቲያን አለች አሉዋቸው ፡፡ በዚህን ጊዜ አፄው ፊታቸውን ወደ ድሃ ማርያም አዙረው ተሳልመው አንቺ እነቴ ማርያም አሁን የምሄደው ወደ ጦርነት ነው ድል አድርጌ እንደመጣ ብትረጂኝ ተመልሼ እሰራሻለሁ ብለው ተሳሉ ፡፡ ከዚያ በኋላ ሙኒት ላይ ወጡ ሙኒትም መጓዝ ጀመረች አፄ ቴዎድሮስም ካሰቡበት ቦታ ደርሰው በጦርነቱ ድል አድርገው ከጊዜ በኋላ ሲመለሱ በዚያው በተለመደው በተለመደው መንገድ ሲያልፉ ለዘመቻ ሲሄዱ ሙኒት በቅሎቸው ከቆመችበት አፄ ቴዎድሮስ ተመልሰው ለድሃ ማርያም ስለት ከተሳሉበት ቦታ ሲደርሱ አሁንም ሙኒት በቅሎቸው ቆመች ፣በአለንጋ ብትመታም አልንቀሳቀስ አለች ይህ ሙኒት ዘመቻ ሲሄዱም ድል አድርገው ሲመለሱም ቁማ አልንቀሳቀስ ያለችበት ከድሃ ማርያም ቤተክርስቲያ ፊት ለፊት በ500 ሜትር ርቀት ላይ ያለው ለጥ ያለ ሜዳ እስካሁን ድረስ ሽንኩር (የአዊኛ ቃል ሲሆን ትርጉሙም የተጋጠ ማለት ነው) በመባል ይታወቃል ፡፡ አፄ ቴዎድሮስ በጦርነቱ ድል በማድረጋቸው ተደስተው ስለነበር ድሃ ማርያም ወደ ዘመቻው ሲሄድ የተሳሉበትን ስለት ርስተዋል ፡፡ በዚህም ላይ ሙኒት በቅሎቸው አልንቀሳቀስ ማለት ግራ አጋብቷቸዋል እናም ምን ችግር ተፈጠረ ብለው ተከታዮቻቸውን ጠየቁ የቅርብ አማካሪያቸውም ጌታዬ ሆይ ከአሁን በፊት ለዘመቻ ስንሄድ ከዚህ ቦታ ስለት አለብዎት አሉዋቸው ፡፡ በዚህን ጊዜ አስታወሱና ሙኒት በቅሎቸውን ማሪኝ ብለው ባይ አንቺ ምሪኝ አሉዎት በቅሎዎም በቀጥታ በቀጭን መንገድ ወደ ድሃ ማርያም ይዛቸው ገባች ፡፡ አፄ ቴዎድሮስም በጫካ የተዋጠችውን ድሃ ማርያምን ጫካውን በተከተለችው ሰራዊት አስመንጥረው ከቤተክርስቲያኗ ፊት ለፊት በ200 ሜትር ርቀት ካለ “ጎዳኻይ” ከተባለ ሰፈሩ ፡፡ ይህ ጎዳኻይ የተባለው ኮረብታ ያኔ አፄው በሰፈሩ ጊዜ በአማረኛው አጠራር አደባባይ ተብሎ የተሰየመና የአካባቢው ህብረተሰብ የአፍ መፍቻ ቋንቋው አዊጚ በመሆኑ በአዊኛ እስካሁን ድረስ ጎዳኻይ እየተባለ ይጠራ ፡፡ አሁንም ድረስ ይህንን በማስታወስ የአካባቢው ነዎሪዎች በዚህ የጎዳኻይ ኮረብታ በአመት አንድ ጊዜ ደመራ ተክለው የመስቀል በዓል በጋራ ያከብራሉ ፡፡ እነዚህ ጎዳኻይ ከተባለ ቦታ የሰፈሩት አፄ ቴዎድሮስ የሰባት ቤት አገው ህዝብን በስለታቸው መሰረት ድሃ ማርያምን ለመስራት ወደ

እሳቸው አስጠሩ ፡፡ ጥሪውን ሰምቶ በመጣው ህዝብ የቤተክርሰቲያኗ ስራ ተጀመረ ፡፡ መሰረቱ ከድንጋይና አፈር ከፍ ብሎ ተሰራ፡፡ በነጭ፣በሀር፣በቢጫና በአርንጓዴ የተጌጠች ድሃ ማርያም ተሰራች ፡፡ በቤተክርስቲያኗ ዙሪያ አሁን ትላልቅ ሆኖ የሚታይ ከ350 በላይ ፅድና ለልብስ ማጠቢያ የሚሆን እንዶድም አስተከሉ ፡፡ አፄ ቴዎድሮስም ይህችን ቤተክርስቲያን ለማሰራት 8 ወር በዚያው እንደተቀመጡ አባቶች ያስረዳሉ ፡፡ ፅዱ የተተከለው በሚያዚያ ወር ስለነበረ እንዳይደርቅ ውሃ የሚያጠጡ ሰዎች ለአንድ ሰው አንድ ጠገራ ብር ሂሳብ ቀጥረው ያሰሩ ነበር ፡፡ የቤተክርስቲያኗ ስራ ሲጠናቀቅም አፄ ቴዎድሮስ ከዛሬ ጀምሮ ድሃ ማርያም ትባል የነበረች ቤተክርስቲያን የእናት ድሃ የለችምና አባብላ ማርያም ብዬ ሰይሜታለሁ አሉ ፡፡ በዚህን ጊዜ ከመኳንንቱ አንዱ ንጉስ ሆይ አባብላ ማርያም ያሏት በምን ምክንያት ነው ብለው ጠየቋቸው ፡፡ አፄ ቴዎድሮስም አባብላ ማርያም ያልኳዎት ወደ ጦርነት ስሄድ ትልቅ ታምር አሳየችኝ እኔም በታምራቷ አምኜ በሰላም ከነሰራዊቴ አሸንፌ ብመለስ ቤትሽን ቁሜ አሰራለሁ ብዬ ተሳልኩኝ ስለዚህ ከለመንኳት በላይ አድርገችልኝ ፡፡ እኔም ሰውነኝና ስመለስ በደስታየ ብዛት እራስቼ አልፌ ልሄድ ስል እራሷ በበቅሎዬ አድራ አስታወሰችኝ ሰትቆጣ የእናትናት ባህሪ ሳትነፍገኝ እንደ ልጅ አባበላኝ ነው ከዚህች ቦታ ያመጣችኝ ከዚህ ከቸርነቷ በመነሳት ነው አባብላ ማርያም ያልኋት ብለው መልስውለታል ፡፡ አፄ ቴዎድሮስ የቤተክርስቲያኗን ስራ ካሰፈፀሙ በኋላ የምርቃ ስነ-ስርዓቱን ለማስፈፀም ግብፃዊውን አቡነ ቄርሎስን ሃምሳ ቆሞስ መቶቄ አስቀርበው ፡- “መሐልዋ ገነት ዳሯ እሳት ትሁን ደባ ለባሽ መነኩሴ ያሳተዳድራት ነፍስ የገደለ፣ቋንጃ የቆረጠ፣አስደውሎ ገብቶ ነፍስ ይደንበት” ብለው የግድምና ስነ ስርዓት አስፈፅመው ከዛሬ 148

ዓመት አካባቢ አስገደሟት ይላሉ ፡፡ በዚህ የግድምን ስነ- ስርዓት ጥሪ ተደርጎላቸው የተገኙት ግብፄዊው አቡነ ቄርሎስ አፄ ቴዎድሮስ አባብላ ማርያም ብለው የሰየሙትን የማርያም ገዳም እግዚኸሪያ ማርያም አንድነት ገዳም ብለው ሰይመውታል ፡፡ አፄ ቴዎድሮስም አባብላ ማርያም የተባለውን ስያሜ እንዲቀየር አይፈልጉም ነበርና አቡነ ቄርሎስን ለምን ሊቀይሩ ቻሉ ሲሉ ጠየቋቸው ፡፡ አቡነ ቄርሎስም ንጉስ ሆይ ስሙ የተቀየረበት ምክንያት ኢትዮጵያን መሳፍንት ከፈፍለው ይገዟት ነበር አሁን ግን እግዚአብሔር አምላክ በእርስዎ አድሮ አንድ ኢትዮጵያ ተብላለች እግዚኸሪያ ማርያም አንድነት ገዳም ያልኳትም በዚህ ምክንያት ነው አሏቸው ፡፡ አፄ ቴዎድሮስም ስያሜዋን ተስማምተው ተቀበሉ እስከ ዛሬም ድረስ በዚሁ ስያሜዋ ትጠራለች፡፡ ከዚህ በኋላ አጼ ቴዎድሮስ የእንግሊዝ ጦር ወደ ሀገራችን ዘልቆ መግባቱን ሰሙ ይህ ሁኔታ ድንገተኛ ስለነበረ በግጥም እንዲህ አሉ አርሜ ኮትኩቼ አሳምኜ ስመጣ አገው ክፉ አያጣ እንግሊዝ ሚሉት መጣ አንቺ አባብላ ማርያም አየሽ ይህን ጉድ ከእሳት ላይ ወጥጭ ጎርጎራን መንገድ አድርጌ መተማን እንዲሁ ስወርድ ብለው ለ8 ወራት ሰፍረው ከነበሩበት ጎዳኸይ ኮረብታ ከእነሰራዊታቸው አባብላ ማርያምን ለ3 ካህናት አስይዘው ለጦርነት ዘመቱ ፡፡ ከጦርነቱ ቦታም ከደረሱ በኋላም በውጊያው ሲሳተፉ ወጊያው በጣም ያየለ በመሆኑ መቅደላ ላይ በራሳቸው ሽጉጥ ህይወታቸውን አጠፉ ፡፡ አባብላ ማርያምን ይዘው ከአጼ ቴዎድሮስ ጋር ከሄዱ ሶስት ቄሶች ውስጥ ሁለቱ ህይወታቸው በጦርነቱ እዚያው መቅደላ አለቁ ፡፡ ሶስተኛው ቄስ ተክሌ ወንድም ታቦተ ማርያምንና የአጼ ቴዎድሮስን በቅሎ የሙኒትን የአንገት ቢልቢላ ይዘው ተመለሱ ፤አጼ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ በራሳቸው ሽጉጥ ህይወታቸውን ከቀኑ 6፡ 00 ሲያጠፉ እሳቸው ያሰሯት እግዚኻሪያ ማርያም

ገዳም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ምንም ደመናና ዝናብ በሌለበት መብረቅ ጥሎ አቃጠላቸው ፡፡ ይህም እመቤቴ ማርያም በአሰሪዎ አጼ ቴዎድሮስ ሞት አምርራ በማዘኗ ነው ይላሉ፡፡ የአካባቢው ቀደምት ነዎሪዎች አጼ ቴዎድሮስ በእግዚኸሪያ ማርያም ስራ የ8 ወር ቆይታቸው ለቤተክርስቲያኗ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶች አበርክተዋል ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፡- 1. ግንዘት ብራና መፅሐፍ ፡- ይህ መፅሐፍ በሞት ጊዜ የሚደገም ሲሆን በውስጡ በተፃፈ ፅሑፍ የአጼ ቴዎድሮስ ክርስትና ስም ገብር ኪዳን የአጼ ቴዎድሮስ ባለቤት የክርስትና ስምም ወለተ ንግስትና ወለተ ኪዳን ይባል እንደ ነበር ያስረዳል ፡፡ መፅሐፍ ቤተክርስቲያንኗ አፄው በሞቱበት ዕለት ስትቃጠል በእሳት የተለበለበ ለመሆኑ አሁንም ማየት ይቻላል፡፡ 2. የእመቤቴ ማርያም ስዕል ከነ ልጅዎ ያለበት መቀደሻ ደወል 3. የሙኒት አንገት ቢልቢላ ከነሐስ የተሰራ 4. ከነሐስ የተሰራ ዘውድ አክሊል 5. ይስማው ጎንደር የሚባል ትልቅ ከበሮ 6. ህዝቡ ለጦርነት እንዲገባ የክተት ጥሪ የሚያስተላልፍበት ነጋሪት በአንድ በኩል እሳቸው በመንገድ ሲያርፉ ለመቀመጫነት እንዲያገለግል ሆኗ የተሰራ 7. ሁለት ማህተም አንዱ ከቀንድ አንዱ ከነሐስ የተሰራ “ዝማይተም ማህበረ እግዚኻራ ማርያም ርግብ ፃዳ” የሚል በመሀሉ የአጼ ምስል ሹሩባ እንደተሰሩ ያለበት እና ሌሎችም ይገኙበታል ፡፡ ይህን የመሰለ ታሪክ ተዳፍኗ እንዳይቀር እኛ ጀመርነው እንጂ አልጨረስነውም ሙሉ ታሪኩን በጥናትም ሆነ በሌላ ነገር የሚያጠኑ ምሁራን ከመጡ የወረዳው ባህልና ቱሪዝም እንዲሁም የአካባቢ ህብረተሰብ የላቀ ትብብር የሚያደርግ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን ፡፡

A[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

B[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

C[ለማስተካከል | ኮድ አርም]