ጋን ማክ ዴላ

ከውክፔዲያ

ጋን ማክ ዴላአየርላንድ ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ ከፊር ቦልግ የአየርላንድ ከፍተኛ ንጉሥ ነበር። ሚስቱ ኤውዳር ወይም ኤታር ተባለች።

5000 ፊር ቦልግ አይርላንድን በ1130 መርከቦች በወረሩበት ጊዜ (1538 ዓክልበ. ግድም) ጋን ከዴላ ሌላ ልጆች ጋር ሻለቃ ነበረ። ጋንና ወንድሙ ሴንጋን ደሴቱን በእንበር ዱብግላይዝ (አሁን ኮርክ ወደብ) ገቡ። የጋን ክፍል ስሜን መንስተር ሲሆን ሴንጋን ደቡብ መንስተር ተቀበለ። ደግሞ ሩድራይግ ለ፪ አመት ገዝቶ ካረፈ በኋላ፣ ጋንና ወንድሙ ጌናን በጋርዮሽ ከፍተኛ ንጉሦች ሆነው ተከተሉት። ነገር ግን ከአራት አመት በኋላ ሁለቱ ከ፪ ሲህ ሰዎች ጋራ በቸነፈር ሞቱ። የተረፈው ወንድማቸው ሴንጋን ተከተላቸው።

ቀዳሚው
ሩድራይግ
አይርላንድ (ኤልጋ) ከፍተኛ ንጉሥ
1534-1530 ዓክልበ. (አፈታሪክ)
ተከታይ
ሴንጋን