ጌታቸው ወልዩ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search


ጌታቸው ወልዩ ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ነው።የተለያዩ ትምህርቶችን በከፍተኛ ትምህርት ተቁዋማት ገብቶ ተከታትሉዋል። በፍልስፍና፤ ፔዳጎጂ፤ ሳይኮሎጂ፤ ስነ-ጽሁፍ፤ጋዜጠኝነት፤ ኮሙኒኬሽን፤ ማርኬቲንግ፤ ታሪክ፤ ኣለም አቀፍ ጉዳዮችና ጂኦ ፖለቲክስ ላይ ሰፊ እውቀትና ልምድ ያለው ባለሙያ ነው፡፡በዓባይ ወንዝ ዙሪያ የኣባይ መዘዝ፤የዓባይ ጉዳይነ ያልተዘጋው ዶሴ የሚሉ ሶስት መጽሐፍትን ከዓመታት በፊት አዘጋጅቱዋል።በዓባይ ላይ ሶስት የአማርኛ መጽሃፍትን በመጻፍና በቀዳሚነት በማዘጋጀት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ነው።በዓባይ ላይ ጥናት ለመስራት በመርከብ፤በአውሮፕላንና ሔሊኮፕተር፤በእግርና ጋማ ከብት፤ በመኪናና ባቡር ፈታኝ ጉዞ ያደረገ ዓባይ አስታዋሽ ባጣበት ዘመን የደከመ ጋዜጠኛና ደራሲ ነው።ከዓባይ መነሻ ጮቄና ግሽ ዓባይ ተነስቶ ጣናና ባህርዳርን ፤ጢስ ዓባይን አልፎ እስከ ወለጋ ደቡብ ሱዳንና ካርቱም አልሞርጋን፤እንዲሁም ናይልን እስከ ደቡባዊ ግብጽ ድረስ ያካለለ፤ ተከዜን ከላሊበላ ከፍተኛ ስፍራዎች አንስቶ እስከ ሱዳን አትባራ፤ባሮን ከምዕራብ ኢትዮጵያ እስከ ሶባት የፈተሸ፤ መከራውን አይቶ በሱዳን ፖሊሶች ተሰቃይቶ የነጭና ጥቁር ዐባዮች መገናኛ ትክክለኛ ስፍራ በፎቶ ያነሳና በመጽሃፉ ያቀረበ የሀገር ባለውለታ ነው፡፤በዓባይ ላይ በርካታ ትንተናና ጽሁፍ ያቀረበ፤ሊቀ ናይል የሚባለው ኢትዮጵያ ቲቪ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ከርሱ መጽሃፍት ውጭ የማይታሰቡ፤ዛሬ ሚዲያው፤ ባለስልጣናት፤ምሁሩ፤አርቲስቱና ሌላው ሁሉ መነሻቸውን የርሱ መጽሃፍት ያደረጉ ናቸው።በጋዜጠኛነቱ የተዋጣለት እስከ ዋና አዘጋጅ የደረሰ፤በሚዲያ ከሺ በላይ መጣጥፍ፤ትርጉም ስራዎች፤ግጥሞች፤የጉዞ ታሪኮች፤ወዘተ ያቀረበ፤በርካታ ታዋቂ ጋዜጠኞችን ያስተማረ፤በኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች ተጋባዥ እንግዳና መምህር የነበረ፤በሚዩዚክ ሜይዴይና በርካታ መድረኮች ጥናት ያቀረበ፡ብዙ መድረኮችን የ