ጌናን

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ጌናን ማክ ዴላአየርላንድ ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ ከፊር ቦልግ የአየርላንድ ከፍተኛ ንጉሥ ነበር። ሚስቱ ክኑቃ ተባለች።

5000 ፊር ቦልግ አይርላንድን በ1130 መርከቦች በወረሩበት ጊዜ (1538 ዓክልበ. ግድም) ጌናን ከዴላ ሌላ ልጆች ጋር ሻለቃ ነበረ። ጌናንና ወንድሙ ሩድራይግ ከንዑስ-ወገናቸው ፊር ዶምናይን ጋር ደሴቱን በእንበር ዶምናይን (አሁን ደንድረም ወሽመጥ) ገቡ። የጌናን ክፍል ኮናኽት የሚባል ክፍላገር ሆነ። ደግሞ ሩድራይግ ለ፪ አመት ገዝቶ ካረፈ በኋላ፣ ጌናንና ወንድሙ ጋን ማክ ዴላ በጋርዮሽ ከፍተኛ ንጉሦች ሆነው ተከተሉት። ነገር ግን ከአራት አመት በኋላ ሁለቱ ከ፪ ሲህ ሰዎች ጋራ በቸነፈር ሞቱ። የተረፈው ወንድማቸው ሴንጋን ተከተላቸው።

ቀዳሚው
ሩድራይግ
አይርላንድ (ኤልጋ) ከፍተኛ ንጉሥ
1534-1530 ዓክልበ. (አፈታሪክ)
ተከታይ
ሴንጋን