ጥቅምት ፬
Appearance
(ከጥቅምት 4 የተዛወረ)
ጥቅምት ፬ ቀን የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፴፬ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ቀን በኋላ እስከ ዓመቱ ፍጻሜ ድረስ፤ በዘመነ ሉቃ ፫፻፴፪ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፴፩ ዕለታት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፵፯ ዓ.ም - የብሪታንያዋ ንግሥት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ ለሁለት ሣምንት ጉብኝት የመጡትን ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን በለንደን ቪክቶርያ የባቡር ጣቢያ ተቀበሉ።[1]
- ፲፱፻፶፭ ዓ.ም - የአሜሪካ ዓየር ኃይል የስለላ አውሮፕላን በኩባ ላይ የሶቭየት ኅብረት የኑክሊየር መሣሪያዎች በመገጣጠም ላይ መሆናቸውን የሚያሳዩ መረጃ ፎቶግራፎች አነሳ። ይኼም የኩባ ሚሳይል ክራይስስ በመባል የተጠራውን አደገኛ መፋጠጥ ያስከተለ ሂደት ነው።
- ፲፱፻፶፯ ዓ.ም - በአሜሪካ የሰብዐዊ መብት እንቅስቃሴ መሪ የነበሩት ጥቁር አሜሪካዊ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር የ ኖቤል ሰላማዊ ሽልማት አሸናፊነታቸው ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፻፸፬ ዓ.ም - የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት አንዋር ሳዳት በወታደራዊ ዓመጸኞች ጥይት በተገደሉ በሳምቱ ምክትላቸው ሆስኒ ሙባራክ ፬ኛው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆኑ።
- ፲፱፻፹፯ ዓ.ም - የፍልስጥኤም መሪ ያስር አራፋት እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ይስሓቅ ራቢን እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ (የአሁኑ ፕረዚዳንት) ስምዖን ፔሬስ የዓመቱ የ ኖቤል ሰላማዊ ሽልማት አሸናፊነታቸው ይፋ ተደረገ።
- ፲፱፻፺፪ ዓ.ም. - በምሥራቅ አፍሪቃ የታንዛኒያ መሪ የነበሩት፤ በወገኖቻቸው አቆላማጭ ጥሪ ምዋሊሙ (አስተማሪ) በመባል የሚታወቁት ጁልየስ ካምባራጌ ኔሬሬ በለንደን ሆስፒታል በሉኪሚያ በሽታ ምክንያት አረፉ። እኒህ ታላቅ አፍሪቃዊ መሪ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትን ከመሠረቱት አንዱ ሲሆኑ፤ በአህጉሩ የመጀመሪያው በፈቃዳቸው የፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸውን የለቀቁ ናቸው።
- ^ http://news.bbc.co.uk/player/nol/newsid_6570000/newsid_6572500/6572587.stm?bw=bb&mp=wm&news=1&bbcws=1
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |