ፊኒክስ የአሪዞና ዋና ከተማ ነው። በጥንታዊ የኗሪዎች ፍርስራሽ ላይ በ1860 ዓ.ም. የተመሠረተው አሜሪካዊው ሰው ጃክ ስዊሊንግ ነበረ። በ1873 ዓ.ም. የከተማነት ሁኔታ ተቀበለና ከ1881 ዓ.ም. ጀምሮ የአሪዞና ጠቅላይ ግዛት መቀመጫ ሆነ።