ፍቅር እስከ መቃብር
ፍቅር እስከ መቃብር በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም.[1] በደራሲ ሀዲስ አለማየሁ የቀረበ ልብ ወለድ ሲሆን ሰብለ ወንጌል እና በዛብህ የሚባሉ የሁለት ገፀ ባህሪያትን ፍቅር ይተርካል።
ይህ ድርሰት ከሌሎች ልብወለድ ሥራዎች ለየት የሚያደርገው ደራሲው ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ በፊደል አጠቃቀም ላይ ለውጥ አድርገው በማቅረባቸው ነው። ይኸውም ለምሳሌ ያህል ሦስት «ሀ»ዎች፣ ሁለት «ሰ»ዎች፣ ሁለት «ኣ»ዎች የመሳሰሉትን እንደ አንድ ወይም የመጀመሪያውን ብቻ በመያዝ ነው። በተጨማሪም ጠብቀው በሚነገሩ ቃላት ላይ ከላይ አንድ ነጥብ በማስቀመጥ ይታወቃሉ።[1]ሀዲስ ኣለማየሁ በኢትዮጵያ ስነ-ፅሑፍ የራሳቸው ትልቅ አሻራ አኑረው ያለፉ አንጋፋ ደራሲ ናቸው።
የታሪኩ ማጠቃለያ
በዛብህ ጎጃም ማንኩሳ ውስጥ ከእናቱ ከውድነሽ በጣሙና ከአባቱን ከቦጋለ መብራት ይወለዳል። በሽታ ይበዛበትና በዛብህ ይባላል። እናቱ ከበሽታው እንዲድን ስእለት ይሳላሉ። ዕድል ሆኖ በዛብህ ይተርፋል፤ አድጎ ጎበዝ ልጅ ይሆናል። ቀድሞ በሽታ፣ ከዚያም ደግሞ ዕውቀትና ፍቅር (የሰው መውደድ) ይበዛበታል። በወጣትነቱ ይቀድስና ለቤተሰቡ ገንዘብ ማምጣት ይጀምራል። ቀድሞ የስእለት ልጅ መባልን አይጠላም ነበር። ሲያድግ ግን ትርጉሙን በመረዳቱ ነጻነቱን ለማግኘት ዲማን ጥሎ ወደደብረ ወርቅ ይሄዳል። እዚያም ከእመት ጠጂቱ ዘንድ ይጠጋል። ትንሽ ዜማና ቅኔም ይማራል። ደብተራ በየነ መጥቶ የወላጆቹን ሞት ሲያረዳው ወደዲማ ይወርዳል። በተክለ አልፍአው በዓል በመልካም ድምጹ ፊታውራሪ መሸሻንና ወይዘሮ ጥሩአይነትን ያወድሳል። ፊታውራሪ መሸሻም የሰብለ መምህር አድርገው ይቀጥሩታል። ሰብለና በዛብህ የሕይወት ገጠመኞቻቸው በመጠኑ ስለሚመሳሰል ይግባባሉ። በመሃል ፊታውራሪ አሰጋኸኝ ሰብለን በፈት ወግ አገባለሁ በማለቱ በርሱና በፊታውራሪ መሸሻ መካከል ጥል ተፈጠረ፤ ሆኖም በሃይማኖት ጣልቃገብነት ሳይዋጉ ቀሩ። ከዚያም ደግሞ ፊታውራሪ ከባላገሮች ጋራ በግብር ጉዳይ ተጣሉ። ፊታውራሪ ተማርከው ሳለ የበዛብህንና የሰብለወንጌልን የፍቅር ዜና ይሰማሉ። ወዲያውም መጥተው ሰብለን በሌሊት ያስሯታል። የሰብለ አጎት ጉዱ ካሳም ሁለቱን ለማስመለጥ ወጣ፣ ወረደ። የዕጣ ነገር ሆኖ ግን ሳይሳካ ቀረ። በዛብህ ግን በግራጌታ ቀለመወርቅና በጉዱ ካሳ ጥረት ወደአዲስ አበባ ይሄዳል። በራጉኤል ቤተክርስቲያንም የቅኔ መምህር ሆኖ ይቀጠራል። ባደረጉላቸው ውለታ ምክንያት ፊታውራሪ መሸሻ ሰብለን ለፊታውራሪ ታፈሰ ሊድሯት ይሞክራሉ። የሰብለን አቋም አውቀው አባ ተክለሃይማኖት በተባሉ መነኩሴ ያስጠብቋቷል። መነኩሴው ግን ሰክረው ሰብለ ታመልጣለች። ፍለጋ ሲሄዱ ፊታውራሪ ከፈረስ ላይ ተወርውረው፣ ተንኮታክተው ይሞታሉ። ወይዘሮ ጥሩአይነትም ቤተክርስቲያን ውስጥ ከደረጃ ላይ ተንሸራትተው ወድቀው ይሞታሉ። ሰብለ ደግሞ በዛብህን ለማግኘት መነኩሴ መስላ ወደአዲስ አበባ ትሄዳለች። ደርሳም በዛብህ አለመኖሩን ትሰማና ጎሃጽዮን ትወርዳለች። በዚያም በዛብህ ተደብድቦ፣ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ አይነት ሁኔታ ላይ ሳለ ይገናኛሉ። እንደምንም ብለው ሥጋ ወደሙን ይቀበላሉ። ጥቂት ቆይቶ በዛብህ ይሞታል። ሰብለም መንኩሳ፣ የበዛብህን አስከሬን ባጠገቧ አድርጋ ስትኖር ከጉዱ ካሳ ጋራ ይገናኛሉ። ጉዱ የተሰኘው ካሳ ዳምጤም እርሷ ዘንድ ይቀመጣል። አስራ አምስት ቀናት አንድ ላይ ይኖሩና ሰብለ የልብ በሽታዋ ተነሥቶባት ትሞታለች፣ ጉዱ ካሳም ከበዛብህ አጠገብ ያስተኛታል። በሦስተኛው አመት ጉዱም አረፍተ ዘበዛብህ ጎጃም ማንኩሳ ውስጥ ከእናቱ ከውድነሽ በጣሙና ከአባቱን ከቦጋለ መብራት ይወለዳል። በሽታ ይበዛበትና በዛብህ ይባላል። እናቱ ከበሽታው እንዲድን ስእለት ይሳላሉ። ዕድል ሆኖ በዛብህ ይተርፋል፤ አድጎ ጎበዝ ልጅ ይሆናል። ቀድሞ በሽታ፣ ከዚያም ደግሞ ዕውቀትና ፍቅር (የሰው መውደድ) ይበዛበታል። በወጣትነቱ ይቀድስና ለቤተሰቡ ገንዘብ ማምጣት ይጀምራል። ቀድሞ የስእለት ልጅ መባልን አይጠላም ነበር። ሲያድግ ግን ትርጉሙን በመረዳቱ ነጻነቱን ለማግኘት ዲማን ጥሎ ወደደብረ ወርቅ ይሄዳል። እዚያም ከእመት ጠጂቱ ዘንድ ይጠጋል። ትንሽ ዜማና ቅኔም ይማራል። ደብተራ በየነ መጥቶ የወላጆቹን ሞት ሲያረዳው ወደዲማ ይወርዳል። በተክለ አልፍአው በዓል በመልካም ድምጹ ፊታውራሪ መሸሻንና ወይዘሮ ጥሩአይነትን ያወድሳል። ፊታውራሪ መሸሻም የሰብለ መምህር አድርገው ይቀጥሩታል። ሰብለና በዛብህ የሕይወት ገጠመኞቻቸው በመጠኑ ስለሚመሳሰል ይግባባሉ። በመሃል ፊታውራሪ አሰጋኸኝ ሰብለን በፈት ወግ አገባለሁ በማለቱ በርሱና በፊታውራሪ መሸሻ መካከል ጥል ተፈጠረ፤ ሆኖም በሃይማኖት ጣልቃገብነት ሳይዋጉ ቀሩ። ከዚያም ደግሞ ፊታውራሪ ከባላገሮች ጋራ በግብር ጉዳይ ተጣሉ። ፊታውራሪ ተማርከው ሳለ የበዛብህንና የሰብለወንጌልን የፍቅር ዜና ይሰማሉ። ወዲያውም መጥተው ሰብለን በሌሊት ያስሯታል። የሰብለ አጎት ጉዱ ካሳም ሁለቱን ለማስመለጥ ወጣ፣ ወረደ። የዕጣ ነገር ሆኖ ግን ሳይሳካ ቀረ። በዛብህ ግን በግራጌታ ቀለመወርቅና በጉዱ ካሳ ጥረት ወደአዲስ አበባ ይሄዳል። በራጉኤል ቤተክርስቲያንም የቅኔ መምህር ሆኖ ይቀጠራል። ባደረጉላቸው ውለታ ምክንያት ፊታውራሪ መሸሻ ሰብለን ለፊታውራሪ ታፈሰ ሊድሯት ይሞክራሉ። የሰብለን አቋም አውቀው አባ ተክለሃይማኖት በተባሉ መነኩሴ ያስጠብቋቷል። መነኩሴው ግን ሰክረው ሰብለ ታመልጣለች። ፍለጋ ሲሄዱ ፊታውራሪ ከፈረስ ላይ ተወርውረው፣ ተንኮታክተው ይሞታሉ። ወይዘሮ ጥሩአይነትም ቤተክርስቲያን ውስጥ ከደረጃ ላይ ተንሸራትተው ወድቀው ይሞታሉ። ሰብለ ደግሞ በዛብህን ለማግኘት መነኩሴ መስላ ወደአዲስ አበባ ትሄዳለች። ደርሳም በዛብህ አለመኖሩን ትሰማና ጎሃጽዮን ትወርዳለች። በዚያም በዛብህ ተደብድቦ፣ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ አይነት ሁኔታ ላይ ሳለ ይገናኛሉ። እንደምንም ብለው ሥጋ ወደሙን ይቀበላሉ። ጥቂት ቆይቶ በዛብህ ይሞታል። ሰብለም መንኩሳ፣ የበዛብህን አስከሬን ባጠገቧ አድርጋ ስትኖር ከጉዱ ካሳ ጋራ ይገናኛሉ። ጉዱ የተሰኘው ካሳ ዳምጤም እርሷ ዘንድ ይቀመጣል። አስራ አምስት ቀናት አንድ ላይ ይኖሩና ሰብለ የልብ በሽታዋ ተነሥቶባት ትሞታለች፣ ጉዱ ካሳም ከበዛብህ አጠገብ ያስተኛታል። በሦስተኛው አመት ጉዱም አረፍተ ዘመን ይገታዋል።
ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
- ^ ሀ ለ "ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ መዝገበ ህትመት ዳሰሳ፣ ቅፅ 25፣ ቁጥር 5፣ 2000 ዓ.ም.፣ ገፅ 18". Archived from the original on 2011-07-20. በ2010-11-19 የተወሰደ.
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |