1 ሳባ

ከውክፔዲያ

1 ሳባ በጥንታዊ የኢትዮጵያ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ከንጉሥ ሆርካም ቀጥሎና ከንጉሥ ሶፋሪድ አስቀድሞ ለ30 ዓመታት የኩሽ መንግሥት (ኢትዮጵያ) ንጉሥ ነበረ። የነገሠበት ዘመን በየምንጩ የሚለያይ ነው፤ ለምሳሌ በተክለጻድቅ መኩሪያ ዝርዝር ከ2375 እስከ 2345 ዓክልበ. ነበረ። በሌላ ቁጠራ ከ2094 እስከ 2064 ዓክልበ. ነገሠ።

አለቃ ታዬ እንደ ጻፈው በ15ኛ ዓመቱ በግብጽና በሱዳን ላይ ረሃብ ስለ ጸና ከከነዓን ልጆች የሰማሪዎን (ሳምሪ) ተወላጅ ዋቶ እና ነገዱ (ወይጦ) ወደ ኩሽ ገቡ።

ቀዳሚው
ሆርካም
ኩሽ ንጉሥ
2094-2064 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሶፋሪድ