Jump to content

ባርነት

ከውክፔዲያ
የ07:08, 23 ኦክቶበር 2023 ዕትም (ከ83.146.253.130 (ውይይት) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

ባርነት በጠባብ ትርጉሙ «ሰዎችን እንደ ሌላ ሰው ንብረት የሚገዙበት፣ የሚሸጡበት፣ የሚለዋወጡበት ወይም የሚያዙበት ሁናቴ» ማለት ነው። ይህም ደግሞ «የንብረት ባርነት» ሲባል፣ ዛሬ በአሁኑ ሰዓት ሰዎች እንደ ንብረት መቆጠሩ በማናቸውም አገር ሁሉ ሕገወጥ ሆኖአል። በሰፊው ትርጉም ሰው ያለፈቃዱ ወይም ያለደመወዝ ሥራ ወይም አገልግሎት ለመፈጽም ቢገደድ፣ ይህ በተግባር ባርነት ሊባል ይችላል።

ከዝርዮቹ ሁሉ የሰው ልጅ ብቻ የሌሎቹን ዝርዮች (እንስሳ ወይም አትክልት) ለመግዛትና ለማስለምድ እንደ ተዘጋጀ ይመስላል። መጽሐፍ ቅዱስም ይህን ነጥብ በቀዳሚው ምዕራፍ ያውጣል። ሆኖም በሰው ልጅ ውስጥ የአለመተባበር ጸባይ ችግር ስላለ፣ በታሪክ ላይ ብዙ ጊዜ እርስ በርስ መገዛዛት የመረጡ ብዙ ሆነዋል። ስለዚህ በየአህጉሩ ከቅድመ-ታሪክ ጀምሮ ባርነት ይስፋፋ ነበር። በጥንታዊው ዘመን በጥንታዊ ግብጽ (3000 ዓክልበ. ግድም) ባርዮች እንደ ነበሩ ታውቋል። ከዚያም በኋላ ኤላምኪሽ የተባሉት ጥንታዊ አገራት እርስ በርስ ጦርነት ሲጀምሩ (2384 ዓክልበ.)፣ ከተማረኩት ሰዎች ቁጥር የባርነት መሠረት በዓለም ላይ ዳግመኛ ቆመ።

ከዚያውም ዘመን ወዲህ፣ በብዙ አገራት ባርነት ሕጋዊ ቢሆንም፣ በሌሎች አገራት ተከለክሏል። በድሮ ዘመን በብዙ አገራት ሕገ መንግሥት ዘንድ የባርነት ልማድ በሕጋዊነት ይጠበቅ ነበር። በ600 ዓክልበ. ግን በግሪክ አገርአቴና አለቃ ሶሎን ባወጣው ሕገ መንግሥት መሠረት፣ የእዳ ባርነት ተከለከለና ባርዮች የነበሩት የአቴና ዜጎች ነጻነታቸውን አገኙ። የባርዮች ሁኔታን የሚቀምሩት ሕግጋት ወይም ልማዶች በጊዜ ላይና ከአገር ወደ አገር ይለያዩ ነበር።

ኦቶማን ቱርኮች በጦርነት ብዙ አውሮጳውያንን ያማርኩ ነበር።

በተለይ እስልምና ከተነሣ በኋላ ብዙ ባርዮች እንደ ተማረኩ ተብሏል። የአውሮፓም መንግሥታት በአሜሪካዎች ውስጥ ቅኝ አገራት ከተከሉ በኋላ፣ እነርሱም በተለይ ከአፍሪካ የተማረኩትን ጥቁር ባርዮች ይግዙ ነበር። በ1764 ዓም ግን ባርያ መያዝ በኢንግላንድ ሕገወጥ እንደሚሆን ተበየነ። ከዚህም በኋላ በብዙ አውሮፓዊ አገራት እንዲሁም በዩናይትድ ስቴትስ ስሜን ክፍላገራት ባርነት ሕገ ወጥ ይደረግ ጀመር። ወደ ደቡብ የተረፉት ባርዮች ግን ነፃነታቸውን ያገኙ ከአሜሪካዊ ብሔራዊ ጦርነት ቀጥሎ ብቻ ሆነ። በ1858 ዓም የአሜሪካ ሕገ መንግሥት ፲፫ኛው ለውጥ ባርነትን በአሜሪካ ለዘለቄታ ከለከለ።

በአፍሪካ እንዲሁም በኢትዮጵያ የባርነት ልማድ ከዚህ በኋላ ተቀጠለ። ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጻፉት ታሪክ ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ ውስጥ ባርነትን ለመከልከል ስለተደረጉ ጥረቶች በሰፊው ገልጸዋል። አንድ ምዕራፍ በሙሉ፣ ምዕራፍ ፲፬ «ባሮች ነጻ እንዲወጡ ስለማድረጋችንና የነፃነታቸውም ነገር በያመቱ እየተሻሸለ ስለ መሔዱ» አቅርበዋል። እሳቸው እንደ ገለጹት፣ የጣልያን መንግስት ወኪሎች ስለ ኢትዮጵያ መክሰሻ ለማድረግ የባርነት ሁናቴ በማጋነን እያወሩ ነበር። ይሁንና «በፍጥረት ጌታና ባርያ ተብሎ የተለየ ነገር አለመኖሩ በሰው ልብ የታወቀ ስለ ሆነ»፣ ከ1845 ዓም ጀምሮ የነገሡት ነገስታት ዓፄ ቴዎድሮስ፣ ዓፄ ዮሐንስ ፬ኛና ዓፄ ዳግማዊ ምኒልክ ሁላቸው የባርነት ንግድ ሕገ ወጥ የሚያድርጉ አዋጆች ቢሰጡም፣ እነዚህ አዋጆች ባብዛኛው በባላባቶች ዘንድ ቸል ተብለው ነበርና ተግባራዊ አልሆኑም። አጼ ኃይለ ሥላሴ በበኩላቸው ባርዮች ነጻ እንዲወጡ ብዙ አዋጆች ሲያውጡ፣ ለማራኪዎቹም የሙት ቅጣት እስኪያገኙ ድረስ አወጁ። ፋሺስቶች ግን እንዳሉ የባርነት መኖሩን ዋና መክሰሻ አደረጉት። እስካሁንም ድረስ የእንግሊዝኛ ውክፔድያፕሮፓጋንዳ እንደሚተርክ፣ የኢትዮጵያ ባርዮች ነጻ የወጡ በጣልያኖች ትዕዛዝና ሥልጣኔ ብቻ ነበረ[1]፣ ከዚህም በላይ ሰብአዊ ንግድ (ባርነት) ዛሬ በኢትዮጵያ እንዳለ ይላል እንግሊዝኛው ውክፔድያ[2]። ባርነትና ሰብአዊ ንግድ በውነት ግን በኢትዮጵያ ወይም የትም አገር በዘመናችን በሕግ ክልክል ነው።. ኢትዮጵያውያንም ብዙ አልባኒያውያንን እና አንዳንድ የሮማንያን "ሰዎች" በባርነት ገዝተው ነበር በዚህ በጣም ይኮሩ ነበር።

  1. ^ en:Timeline_of_abolition_of_slavery_and_serfdom
  2. ^ en:Slavery in contemporary Africaen:Human trafficking in Ethiopia