Jump to content

ሃይድሮጅን

ከውክፔዲያ
የ10:04, 16 ጁላይ 2021 ዕትም (ከShihab1729 (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

ሀይድሮጅን

የውሃ ዘር ወይም ሃይድሮጅን ና ኦክሲጅን ከውሃ እንዴት እንደሚመረት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ከውሃ ሃይድሮጅንና ኦክሲጅን እራስህ አምርት
የሃይድሮጂን ስፔክት ሙከራ

እያንዳንዱ የውሃ ሞለኪዩን ከሁለት የሃይድሮጅን አተም ና ከአንድ የኦክሲጅን አተም የተሰራ ነው። ነገር ግን እኒህ አተሞች በከፍተኛ ጉልበት ስለተጣበቁ እርስ በርሳቸውን አላቆ አተሞቹን ለማግኘት ጉልበት ያስፈልጋል። ለዚህ ተግባር የሚውሉ ብዙ መንገዶች ቢኖሩም፣ በጣም ቀላሉና ማንም ሰው እቤቱ እኒህን ጋዞች (ኦክሲጅን እና ሃይድሮጅን) ለማግኘት ሊጠቀምበት የሚችል መንገድ ቢኖር ኤሌክትሮላይሲስ ይባላል።

ለኤሌክትሮላይሲስ የሚያስፈልጉ እቃወች፡

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  • አንድ ወይም ከዚያ በላይ ባትሪ ድንጋይ
  • ሁለት መካከለኛ ርዝመት ያላቸው የኤሌክትሪክ ገመዶች
  • ሁለት ፊኛወች
  • ሁለት፣ ከጎን በሚታየው ስዕል መሰረት የተያያዙ ቱቦወች
  • ጨው የሟሟበት ውሃ

ሃይድሮጅንና ኦክሲጅኑን አምርቶ መሰብሰብ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጨው የሟሟበት ውሃ በቱቦወቹ ከተሞላ በኃላ፣ የኤሌክትሪክ ገመዶቹ ውሃው ውስጥ በስዕሉ በሚታየው መልኩ ይቀመጣሉ። ከባትሪው ጋር ገመዱ ሲገናኝ ውሃው አረፋ መድፈቅ ይጀምራል። ይህ ከመሆኑ በፊት ግን የቱቦወቹን አፎች በፊኛወች መዝጋት በጣም ጠቃሚ ነው። በዚህ ሁኔታ ከባትሪው ፖዚቲቭ በሚመጣው ገምድ ጎን ባለው ቱቦ ላይ የተገጠመው ፊኛ በሃይድሮጅን ጋዝ ይነፋል። በኔጌቲቩ ጎን ደግሞ ንጹህ ኦክሲጅን ፊኛውን ይሞላል። በዚህ መንገድ እኒህን ሁለት ጋዞች ከውሃ ይመረታሉ። ማስጠንቀቂያ <font color = red> ሃይድሮጅን እጅግ ተቀጣጣይ ጋዝ ስለሆነ በጥንቃቄ መያዝ አለበት! ንጹህ ኦክሲጅን እንዲሁ እሳት ሲያገኝ ቦግ ብሎ የሚቀጣጠል አደገኛ ጋዝ ነው </font>