Jump to content

ሴት መሪብሬ

ከውክፔዲያ
የ00:56, 6 ዲሴምበር 2016 ዕትም (ከTil Eulenspiegel (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

==

ሴት መሪብሬ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1744-1741 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ ሰኸተፕካሬ አንተፍ
ተከታይ 3 ሶበክሆተፕ
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት

==

ሴት መሪብሬ ላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1744 እስከ 1741 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የሰኸተፕካሬ አንተፍ ተከታይ ነበረ።

የሴት መሪብሬ ሕልውና እርግጥኛ አይደለም። ስሙ በቶሪኖ ቀኖና ላይ ብቻ በእርግጥነት ይታወቃል፣ በዚያም «<...>ኢብ<...> ሴት» ብቻ ይታያል። ዘመኑ ምን ያህል ጊዜ እንደ ቀረ ከ«<...>ና ፮ ቀን» በቀር ምንም አይነብም። በአንዳንድ ሊቃውንት አስተሳሰብ ግን ስሙ «መሪብሬ» ሲሆን ሐውልቶቹ በሚከተለው ዘመን በሌላው ፈርዖን ስም እንደ ተቀረጹ ያስባሉ። በነዚህ ቅርሶች ላይ ስሙ ተደምስሶ በመነመነ ምልክት እንደሚታይ ያምናሉ። ምንም እርግጠኛ ስላልሆነ ግን ትቃራኒ ሀሣቦች አሉ። በዝርዝሩ ዘንድ ከእርሱ ቀጥሎ 3 ሶበክሆተፕ (ሰኸምሬሰውጅታዊ) ገዛ። ይህም ሶበክሆተፕ ፈርዖን ከሆነ በፊት ማዕረጉ «የንጉሥ ሊቅ መኮንን» መባሉ ይመስላል።

ቀዳሚው
ሰኸተፕካሬ አንተፍ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን ተከታይ
3 ሶበክሆተፕ
  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)