ስጋ በል ዕፅዋት
Appearance
ስጋ በል ዕፅዋት ስጋ የሚበሉ አትክልቶችን የሚወክል ስም ነው። እነዚህ አትክልቶች በትንሹም ሆነ በአብዛኛው ንጥረ ነገራቸውን የሚያገኙት ከሚበሉት ስጋ ሲሆን አቅማቸውን ግን ከመሬት ነው። አብዛኞቹ ስጋ በል ዕፅዋት በራሪ ትንኞችን በወጥመዳቸው በመክተት ገድለው ይመገቡ እንጂ አንድ አንዶቹ እስከ አይጥ እስከመያዝ ድረስ ሃይል አላቸው። ይህ እንግዳ ተፈጥሮ እነዚህ እፅዋቶች በንጥረ ነገር በትጎሳቆለ መሬት ላይ ለማደግ ያስችላቸዋል። ቻርለስ ዳርዊን ስለነዚህ ተክሎች የመጀመሪያውን ታዋቂ ጽሁፍ በ1875 አቅርቧል። [1]
-
አበባው በጣበቂያ ጉንዳኑን ከራሱ ጋር አጣብቆ ሲበላው
-
ቬነስ ፍላይ ትራፕ የተሰኘው አበባ እራሱን በትንኙ ላይ በመክደን የትንኙን ስጋ እያጣጣመ ሲመገብ
- ^ Darwin C (1875). Insectivorous plants. London: John Murray. http://pages.britishlibrary.net/charles.darwin3/insectivorous/insect01.htm. "Archive copy". Archived from the original on 2006-10-23. በ2010-10-07 የተወሰደ.
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |