Jump to content

ሹዱሩል

ከውክፔዲያ
የ22:18, 30 ጃንዩዌሪ 2014 ዕትም (ከCodex Sinaiticus (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

ሹ-ዱሩል ወይንም ሹ-ቱሩል ከ2001 እስከ 1986 ዓክልበ. ግድም የአካድ መጨረሻ ንጉሥ ነበረ።

ሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ከዱዱ ቀጥሎ ለ፲፭ ዓመት እንደ ነገሠ ይዘግባል። ሆኖም ለእርሱ ዘመን አንዳችም «የዓመት ስም» አልተረፈልንም።

እንደ አባቱ ዱዱ ዘመን ጉታውያን በጠቅላላው መስጴጦምያን ሠፍረው የሹዱሩል ግዛት ከአካድ ከተማ እንዳልራቀ ከጥቂት ቅርሶች ብቻ ሊታወቅ ይቻላል። ከአካድ ከተማ ጭምር ቱቱብኤሽኑና ይገዛ ነበር። ከዚያ በላይ አሁን ዲያላ ወንዝ የሚባለው በዚያን ጊዜ «ሹዱሩል ወንዝ» በሚለው ስም ይታወቅ ነበር።[1]

በዝርዝሩ ዘንድ ከሹዱሩል በኋላ አካድ ተሸነፈና የመስጴጦምያ ላዕላይነት ከአካድ ወደ ኡሩክ (ኦሬክ) ተዛወረ። ከዚያ ስድስት የኡሩክ ነገሥታት ይዘርዝራል። ሆኖም ከነዚህ ፮ የአንዳችም ኅልውና በሥነ ቅርስ ገና አልተረጋገጠም። ጉታውያን በገቡበት ወቅት አንዳንድ ደቡባዊ ከተማ-አገር እንደ ኡሩክ፣ ኡርላጋሽ በራሳቸው ከንቲቦች ሥር ነጻ ሆነው ነበር። ሆኖም የአካድ መንግሥት መጨረሻ ውድቀት በኤላም ንጉሥ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ ዕጅ እንደ ደረሰ ይመስላል።

ቀዳሚው
ዱዱ
አካድ ንጉሥ
2001-1986 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
የለም

ተዋቢ መጻሕፍት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  1. Donald M. Matthews, The Early Glyptic of Tell Brak: Cylinder Seals of Third Millennium Syria 1997, p. 15.