Jump to content

ቅዱስ ጴጥሮስ

ከውክፔዲያ
የ03:39, 5 ጁላይ 2023 ዕትም (ከክርስቶስሰምራ (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
ቅዱስ ጴጥሮስ
ቅዱስ ጴጥሮስ 575 ዓም እንደ ተሳለ፣ ደብረ ሲና ቤተ ክርስቲያን
ሊቀ ሐዋርያት
የተወለደው በ ፩ኛው ክፍለ ዘመን
በገሊላ
ስም መጀመሪያ ስምኦን በኋላ ጴጥሮስ
የአባት ስም ዮሐንስ ወይም ዮና
ዓመታዊ በዓላት ሐምሌ ፭ ጴጥሮስ ወጳውሎስ
የሚታወቀው በሊቀ ሐዋርያነቱ ፣ የገነትን ቁልፍ ከክርስቶስ በመቀበሉ ፣ የመጀመሪያ ጳጳስ በሮም ከተማ በመሆኑ ፣ በሰማዕትነቱ ፣ ተዘቅዝቆ በመሰቀሉ
ያረፈበት በ፷፬-፷፰ ዓ.ም.በቯቲካን ሂል፣ክሌመንታይል ቻፕል፣ ሮም፣
ጣሊያን፣በሮሜ መንግሥት፡በራሱ ምርጫ ተዘቅዝቆ በመሰቀል
የሚከበረው በመላው የክርስትና ሃይማኖት እምነት ተከታይ
ሥራው መጀመሪያ ዐሣ አጥማጅ በኋላ ወንጌል ፀሐፊ ሰባኪም


ቅዱስ ጴጥሮስ ወይም ስምዖን ጴጥሮስ (አራማይስጥ፦ ሸማዮን ከፓ፤ ዕብራይስጥ፦שמעון בר יונה‎ ፦ ሽምዖን ባር ዮና፤ ግሪክኛ፦ ፔትሮስ፤ 8 ዓክልበ. ግ. - 56 ዓም) የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ እና መጀመርያው የሮሜ ጳጳስ (ፓፓ) ነበሩ።

ጴጥሮስ በመጸሐፍ ቅዱስ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ክርስቶስ ጴጥሮስን ብዙ ጊዜ ከመጥፋት ያዳነው ደቀመዝሙር ነበር ምክኒያቱም በመሰለው መንገድ ወይም በስሜታዊነት እየሱስን ሳያማክር ይናገር ፣ይመራ ስለነበር ነው ። ይህም ገና በመንፈሳዊ ዕውቀት ስላላደገ ሆነ ። በተለይ እየሱስ ስለ ስቃዩ፣ሞቱ፣መነሳቱ ለደቀመዝሙሮቹ ሲነግራቸው ጴጥሮስ ባለመረዳቱ ክርስቶስ የዛን ጊዜ ለጴጥሮስ አጥብቆ ጸለየለት በኋላው የሚፈታተነውን ስለሚያውቅ ። ለነገሩ "እኔን ማን ይሉኛል" ? ለሚለ ው የክርስቶስ ጥያቄ ትክክለኛው መልስ የሰጠው ጴጥሮስ ነበረ ። ይህንንም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ በክርስቶስ ትምህርት ማዳበር የሚጠበቅበት አንድ ትልቅ እርምጃ ነበር እየሱስ ክርስቶስም እንደሚክደው፣እንደሚፀፀት፣በልቡም በጣም እንደሚወደው ያውቅ ነበር ። ከክርስቶስ ትንሣዔ በኋላም ወደ ዐሣ አጥማጅነት ተመልሶ ሄዷል በዛም ወቅት በዐሣ ጠመዳ ተአምሩን አሳይቶት ሁሉ በእጁ እንደሆነ አሳምኖት ልቡ እንዲሰበር አድርጎ ለወንጌል ሰበካ ለገነት ቁልፍ ተረካቢነት ከዛም አልፎ ከዕርገት በኋላ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ የሚያውቀው ጸንቶለት የማያውቀው ተገልጾለት በአንድ ቀን ስብከት ፫ሺህ ሕዝብ የወንጌልን ቃል ለማሳመንና ለሰማዕትነት አብቅቶታል ።

የመጀመሪያዪቱ የጴጥሮስ፡ መልእክት ምዕራፍ ፩

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

1-2፤የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ሐዋርያ፡ጴጥሮስ፥እግዚአብሔር፡አብ፡አስቀድሞ፡እንዳወቃቸው፡በመንፈስም፡ እንደሚቀደሱ፥ይታዘዙና፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ደም፡ይረጩ፡ዘንድ፡ለተመረጡት፡በጳንጦስና፡በገላትያ፡ በቀጰዶቅያም፡በእስያም፡በቢታንያም፡ለተበተኑ፡መጻተኛዎች፤ጸጋና፡ሰላም፡ይብዛላችኹ። 3-5፤ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ከሙታን፡በመነሣቱ፡ለሕያው፡ተስፋና፡ለማይጠፋ፥እድፈትም፡ ለሌለበት፥ለማያልፍም፡ርስት፡እንደ፡ምሕረቱ፡ብዛት፡ኹለተኛ፡የወለደን፡የጌታችን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ አምላክና፡አባት፡ይባረክ፤ይህም፡ርስት፡በመጨረሻው፡ዘመን፡ይገለጥ፡ዘንድ፡ለተዘጋጀ፡መዳን፡በእምነት፡ በእግዚአብሔር፡ኀይል፡ለተጠበቃችኹ፡ለእናንተ፡በሰማይ፡ቀርቶላችዃል። 6-7፤በዚህም፡እጅግ፡ደስ፡ይላችዃል፥ነገር፡ግን፥በእሳት፡ምንም፡ቢፈተን፡ከሚጠፋው፡ወርቅ፡ይልቅ፡ አብልጦ፡የሚከብር፡የተፈተነ፡እምነታችኹ፥ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ሲገለጥ፥ለምስጋናና፡ለክብር፡ለውዳሴም፡ይገኝ፡ ዘንድ፡አኹን፡ለጥቂት፡ጊዜ፡ቢያስፈልግ፡በልዩ፡ልዩ፡ፈተና፡ዐዝናችዃል። 8-9፤ርሱንም፡ሳታዩት፡ትወዱታላችኹ፤አኹንም፡ምንም፡ባታዩት፡በርሱ፡አምናችኹ፥የእምነታችኹን፡ፍጻሜ፡ ርሱም፡የነፍሳችኹን፡መዳን፡እየተቀበላችኹ፥በማይነገርና፡ክብር፡በሞላበት፡ሐሤት፡ደስ፡ይላችዃል። 10፤ለእናንተም፡ስለሚሰጠው፡ጸጋ፡ትንቢት፡የተናገሩት፡ነቢያት፡ስለዚህ፡መዳን፡ተግተው፡እየፈለጉ፡መረመሩት፤ 11፤በእነርሱም፡የነበረ፡የክርስቶስ፡መንፈስ፥ስለክርስቶስ፡መከራ፡ከርሱም፡በዃላ፡ስለሚመጣው፡ክብር፡ አስቀድሞ፡እየመሰከረ፥በምን፡ወይም፡እንዴት፡ባለ፡ዘመን፡እንዳመለከተ፡ይመረምሩ፡ነበር። 12፤ለእነርሱም፡ከሰማይ፡በተላከ፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ወንጌልን፡የሰበኩላችኹ፡ሰዎች፡አኹን፡ባወሩላችኹ፡ነገር፡ እናንተን፡እንጂ፡ራሳቸውን፡እንዳላገለገሉ፡ተገለጠላቸው፤ይህንም፡ነገር፡መላእክቱ፡ሊመለከቱ፡ይመኛሉ። 13፤ስለዚህ፥የልቡናችኹን፡ወገብ፡ታጥቃችኹና፡በመጠን፡ኖራችኹ፥ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ሲገለጥ፡የምታገኙትን፡ ጸጋ፡ፈጽማችኹ፡ተስፋ፡አድርጉ። 14፤እንደሚታዘዙ፡ልጆች፡ባለማወቃችኹ፡አስቀድሞ፡የኖራችኹበትን፡ምኞት፡አትከተሉ። 15-16፤ዳሩ፡ግን፦እኔ፡ቅዱስ፡ነኝና፡ቅዱሳን፡ኹኑ፡ተብሎ፡ስለ፡ተጻፈ፡የጠራችኹ፡ቅዱስ፡እንደ፡ኾነ፡ እናንተ፡ደግሞ፡በኑሯችኹ፡ዅሉ፡ቅዱሳን፡ኹኑ። 17፤ለሰው፡ፊትም፡ሳያደላ፡በያንዳንዱ፡ላይ፡እንደ፡ሥራው፡የሚፈርደውን፡አባት፡ብላችኹ፡ብትጠሩ፡ በእንግድነታችኹ፡ዘመን፡በፍርሀት፡ኑሩ። 18-19፤ከአባቶቻችኹ፡ከወረሳችኹት፡ከከንቱ፡ኑሯችኹ፡በሚያልፍ፡ነገር፡በብር፡ወይም፡በወርቅ፡ ሳይኾን፥ነውርና፡እድፍ፡እንደ፡ሌለው፡እንደ፡በግ፡ደም፡በክቡር፡የክርስቶስ፡ደም፡እንደ፡ተዋጃችኹ፡ ታውቃላችኹ። 20-21፤ዓለም፡ሳይፈጠር፡እንኳ፡አስቀድሞ፡ታወቀ፥ነገር፡ግን፥እምነታችኹና፡ተስፋችኹ፡በእግዚአብሔር፡ ይኾን፡ዘንድ፥ከሙታን፡ባስነሣው፡ክብርንም፡በሰጠው፡በእግዚአብሔር፡በርሱ፡ስለምታምኑ፡ስለ፡እናንተ፡በዘመኑ፡መጨረሻ፡ተገለጠ። 22፤ለእውነት፡እየታዘዛችኹ፡ግብዝነት፡ለሌለበት፡ለወንድማማች፡መዋደድ፡ነፍሳችኹን፡አንጽታችኹ፡ርስ፡ በርሳችኹ፡ከልባችኹ፡አጥብቃችኹ፡ተዋደዱ። 23፤ዳግመኛ፡የተወለዳችኹት፡ከሚጠፋ፡ዘር፡አይደለም፥በሕያውና፡ለዘለዓለም፡በሚኖር፡በእግዚአብሔር፡ ቃል፡ከማይጠፋ፡ዘር፡ነው፡እንጂ። 24፤ሥጋ፡ዅሉ፡እንደ፡ሣር፡ክብሩም፡ዅሉ፡እንደ፡ሣር፡አበባ፡ነውና፤ሣሩ፡ይጠወልጋል፡አበባውም፡ ይረግፋል፤ 25፤የጌታ፡ቃል፡ግን፡ለዘለዓለም፡ይኖራል።በወንጌልም፡የተሰበከላችኹ፡ቃል፡ይህ፡ነው።

1፤እንግዲህ፡ክፋትን፡ዅሉ፡ተንኰልንም፡ዅሉ፡ግብዝነትንም፡ቅንአትንም፡ሐሜትንም፡ዅሉ፡አስወግዳችኹ፥ 2-3፤ጌታ፡ቸር፡መኾኑን፡ቀምሳችኹ፡እንደ፡ኾነ፥ለመዳን፡በርሱ፡እንድታድጉ፡አኹን፡እንደ፡ተወለዱ፡ ሕፃናት፡ተንኰል፡የሌለበትን፡የቃልን፡ወተት፡ተመኙ። 4፤በሰውም፡ወደተጣለ፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ግን፡ወደተመረጠና፡ክቡር፡ወደኾነው፡ወደ፡ሕያው፡ድንጋይ፡ወደ፡ርሱ፡እየቀረባችኹ፥ 5፤እናንተ፡ደግሞ፡እንደ፡ሕያዋን፡ድንጋዮች፡ኾናችኹ፥በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ለእግዚአብሔር፡ደስ፡የሚያሠኝ፡ መንፈሳዊ፡መሥዋዕትን፡ታቀርቡ፡ዘንድ፡ቅዱሳን፡ካህናት፡እንድትኾኑ፡መንፈሳዊ፡ቤት፡ለመኾን፡ተሠሩ። 6፤በመጽሐፍ፦እንሆ፥የተመረጠና፡የከበረን፡የማእዘን፡ራስ፡ድንጋይ፡በጽዮን፡አኖራለኹ፥በርሱም፡ የሚያምን፡አያፍርም፡ተብሎ፡ተጽፏልና። 7፤እንግዲህ፡ክብሩ፡ለእናንተ፡ለምታምኑት፡ነው፤ለማያምኑ፡ግን፡ዐናጢዎች፡የጣሉት፡ድንጋይ፡ርሱ፡ የማእዘን፡ራስ፡የዕንቅፋትም፡ድንጋይ፡የማሰናከያም፡አለት፡ኾነ፤ 8፤የማያምኑ፡ስለ፡ኾኑ፡በቃሉ፡ይሰናከሉበታልና፤ለዚህ፡ደግሞ፡የተመደቡ፡ናቸው። 9፤እናንተ፡ግን፡ከጨለማ፡ወደሚደነቅ፡ብርሃኑ፡የጠራችኹን፡የርሱን፡በጎነት፡እንድትናገሩ፡የተመረጠ፡ ትውልድ፥የንጉሥ፡ካህናት፥ቅዱስ፡ሕዝብ፥ለርስቱ፡የተለየ፡ወገን፡ናችኹ፤ 10፤እናንተ፡ቀድሞ፡ወገን፡አልነበራችኹም፡አኹን፡ግን፡የእግዚአብሔር፡ወገን፡ናችኹ፤እናንተ፡ምሕረት፡ ያገኛችኹ፡አልነበራችኹም፡አኹን፡ግን፡ምሕረትን፡አግኝታችዃል። 11፤ወዳጆች፡ሆይ፥ነፍስን፡ከሚዋጋ፡ሥጋዊ፡ምኞት፡ትርቁ፡ዘንድ፡እንግዳዎችና፡መጻተኛዎች፡እንደ፡ መኾናችኹ፡እለምናችዃለኹ፤ 12፤ስለሚመለከቱት፡ስለ፡መልካም፡ሥራችኹ፥ክፉ፡እንደምታደርጉ፡በዚያ፡እናንተን፡በሚያሙበት፡ ነገር፥በሚጐበኝበት፡ቀን፡እግዚአብሔርን፡ያከብሩት፡ዘንድ፡በአሕዛብ፡መካከል፡ኑሯችኹ፡መልካም፡ይኹን። 13፤ስለ፡ጌታ፡ብላችኹ፡ለሰው፡ሥርዐት፡ዅሉ፡ተገዙ፤ለንጉሥም፡ቢኾን፥ከዅሉ፡በላይ፡ነውና፤ 14፤ለመኳንንትም፡ቢኾን፥ክፉ፡የሚያደርጉትን፡ለመቅጣት፡በጎም፡የሚያደርጉትን፡ለማመስገን፡ከርሱ፡ ተልከዋልና፥ተገዙ። 15፤በጎ፡እያደረጋችኹ፥የማያውቁትን፡ሞኞች፡ዝም፡ታሠኙ፡ዘንድ፡እንዲህ፡የእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡ነውና፤ 16፤ሐራነት፡ወጥታችኹ፡እንደእግዚአብሔር፡ባሪያዎች፡ኹኑ፡እንጂ፡ያ፡ሐራነት፡ለክፋት፡መሸፈኛ፡እንዲኾን፡ አታድርጉ። 17፤ዅሉን፡አክብሩ፥ወንድሞችን፡ውደዱ፥እግዚአብሔርን፡ፍሩ፥ንጉሥን፡አክብሩ። 18፤ሎሌዎች፡ሆይ፥ለበጎዎችና፡ለገሮች፡ጌታዎቻችኹ፡ብቻ፡ሳይኾን፡ለጠማማዎች፡ደግሞ፡በፍርሀት፡ዅሉ፡ ተገዙ። 19፤በግፍ፡መከራን፡የሚቀበል፡ሰው፡እግዚአብሔርን፡እያሰበ፡ሐዘንን፡ቢታገሥ፡ምስጋና፡ይገ፟ባ፟ዋልና። 20፤ኀጢአት፡አድርጋችኹ፡ስትጐሰሙ፡ብትታገሡ፥ምን፡ክብር፡አለበት፧ነገር፡ግን፡መልካም፡አድርጋችኹ፡ መከራን፡ስትቀበሉ፡ብትታገሡ፥ይህ፡ነገር፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ምስጋና፡ይገ፟ባ፟ዋል። 21፤የተጠራችኹለት፡ለዚህ፡ነውና፤ክርስቶስ፡ደግሞ፡ፍለጋውን፡እንድትከተሉ፡ምሳሌ፡ትቶላችኹ፡ስለ፡ እናንተ፡መከራን፡ተቀብሏልና። 22፤ርሱም፡ኀጢአት፡አላደረገም፥ተንኰልም፡በአፉ፡አልተገኘበትም፤ 23፤ሲሰድቡት፡መልሶ፡አልተሳደበም፥መከራንም፡ሲቀበል፡አልዛተም፤ነገር፡ግን፥በጽድቅ፡ለሚፈርደው፡ ራሱን፡አሳልፎ፡ሰጠ፤24፤ለኀጢአት፡ሞተን፡ለጽድቅ፡እንድንኖር፥ርሱ፡ራሱ፡በሥጋው፡ኀጢአታችንን፡በዕንጨት፡ላይ፡ ተሸከመ፤[*]፡ 25፤በመገረፉ፡ቍስል፡ተፈወሳችኹ።እንደ፡በጎች፡ትቅበዘበዙ፡ነበርና፥አኹን፡ግን፡ወደነፍሳችኹ፡እረኛና፡ ጠባቂ፡ተመልሳችዃል። [*]፤በግእዝ፡እንዲህ፡ተጽፏል።ወበእንተ፡ኃጥኣዊነ፡ውእቱ፡ተሰቅለ፡ዲበ፡ዕፅ፡በሥጋሁ፡ከመ፡ያውፅአነ፡እምኃጥኣዊነ፡ወበጽድቁ፡ ያሕይወነ።

 1-2፤እንዲሁም፥እናንተ፡ሚስቶች፡ሆይ፥ከባሎቻችኹ፡አንዳንዱ፡ለትምህርት፡የማይታዘዙ፡ቢኖሩ፥በፍርሀት፡ ያለውን፡ንጹሑን፡ኑሯችኹን፡እየተመለከቱ፡ያለትምህርት፡በሚስቶቻቸው፡ኑሮ፡እንዲገኙ፡ተገዙላቸው። 3፤ለእናንተም፡ጠጕርን፡በመሸረብና፡ወርቅን፡በማንጠልጠል፡ወይም፡ልብስን፡በመጐናጸፍ፡በውጭ፡የኾነ፡ ሽልማት፡አይኹንላችኹ፥ 4፤ነገር፡ግን፥በእግዚአብሔር፡ፊት፡ዋጋው፡እጅግ፡የከበረ፡የዋህና፡ዝግተኛ፡መንፈስ፡ያለውን፡ የማይጠፋውን፡ልብስ፡ለብሶ፡የተሰወረ፡የልብ፡ሰው፡ይኹንላችኹ። 5፤እንዲህ፡በቀድሞ፡ዘመን፡በእግዚአብሔር፡ተስፋ፡ያደረጉት፡ቅዱሳት፡ሴቶች፡ደግሞ፡ለባሎቻቸው፡ሲገዙ፡ ተሸልመው፡ነበርና፤ 6፤እንዲሁም፡ሳራ፡ለአብርሃም፦ጌታ፡ብላ፡እየጠራችው፡ታዘዘችለት፤እናንተም፡ከሚያስደነግጥ፡ነገር፡ አንዳች፡እንኳ፡ሳትፈሩ፡መልካም፡ብታደርጉ፥ልጆቿ፡ናችኹ። 7፤እንዲሁም፥እናንተ፡ባሎች፡ሆይ፥ደካማ፡ፍጥረት፡ስለ፡ኾኑ፡ከሚስቶቻችኹ፡ጋራ፡በማስተዋል፡ ዐብራችኹ፡ኑሩ፤ጸሎታችኹ፡እንዳይከለከል፥ዐብረው፡ደግሞ፡የሕይወትን፡ጸጋ፡እንደሚወርሱ፡አድርጋችኹ፡ አክብሯቸው። 8፤በመጨረሻው፡ዅላችኹ፡ባንድ፡ልብ፡ኹኑ፥የሌላው፡መከራ፡ለእናንተ፡እንደሚኾን፡አድርጉ፥እንደ፡ ወንድሞች፡ተዋደዱ፥ርኅሩኆችና፡ትሑታን፡ኹኑ፤ 9፤ክፉን፡በክፉ፡ፈንታ፡ወይም፡ስድብን፡በስድብ፡ፈንታ፡አትመልሱ፥በዚህ፡ፈንታ፡ባርኩ፡እንጂ፤በረከትን፡ ልትወርሱ፡ለዚህ፡ተጠርታችዃልና። 10፤ሕይወትን፡ሊወድ፡መልካሞችንም፡ቀኖች፡ሊያይ፡የሚፈልግ፡ሰው፥ምላሱን፡ከክፉ፡ከንፈሮቹንም፡ ተንኰልን፡ከመናገር፡ይከልክል፤ 11፤ከክፉ፡ፈቀቅ፡ይበል፥መልካምንም፡ያድርግ፥ሰላምን፡ይሻ፡ይከተለውም፤ 12፤የጌታ፡ዐይኖች፡ወደ፡ጻድቃን፡ናቸውና፥ዦሮዎቹም፡ለጸሎታቸው፡ተከፍተዋል፥የጌታ፡ፊት፡ግን፡ክፉ፡ነገርን፡በሚያደርጉ፡ላይ፡ነው። 13፤በጎንም፡ለማድረግ፡ብትቀኑ፡የሚያስጨንቃችኹ፡ማን፡ነው፧ 14፤ነገር፡ግን፥ስለ፡ጽድቅ፡እንኳ፡መከራን፡ብትቀበሉ፡ብፁዓን፡ናችኹ።ማስፈራራታቸውንም፡አትፍሩ፡ አትናወጡም፥ 15፤ዳሩ፡ግን፡ጌታን፡ርሱም፡ክርስቶስ፡በልባችኹ፡ቀድሱት።በእናንተ፡ስላለ፡ተስፋ፡ምክንያትን፡ ለሚጠይቋችኹ፡ዅሉ፡መልስ፡ለመስጠት፡ዘወትር፡የተዘጋጃችኹ፡ኹኑ፥ነገር፡ግን፥በየዋህነትና፡በፍርሀት፡ይኹን። 16፤በክርስቶስ፡ያለውን፡መልካሙን፡ኑሯችኹን፡የሚሳደቡ፡ሰዎች፡ክፉን፡እንደምታደርጉ፡በሚያሙበት፡ነገር፡ እንዲያፍሩ፡በጎ፡ኅሊና፡ይኑራችኹ። 17፤የእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡እንዲህ፡ቢኾን፥ክፉ፡ስለ፡ማድረግ፡ሳይኾን፡በጎ፡ስለ፡ማድረግ፡መከራን፡ ብትቀበሉ፡ይሻላችዃልና። 18፤ክርስቶስ፡ደግሞ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እንዲያቀርበን፡ርሱ፡ጻድቅ፡ኾኖ፡ስለ፡ዐመፀኛዎች፡አንድ፡ጊዜ፡ በኀጢአት፡ምክንያት፡ሞቷልና፤በሥጋ፡ሞተ፡በመንፈስ፡ግን፡ሕያው፡ኾነ፥ 19፤በርሱም፡ደግሞ፡ኼዶ፡በወህኒ፡ለነበሩ፡ነፍሳት፡ሰበከላቸው፤ 20፤ጥቂቶች፡ማለት፡ስምንት፡ነፍስ፡በውሃ፡የዳኑበት፡መርከብ፡ሲዘጋጅ፥የእግዚአብሔር፡ትዕግሥት፡በኖኅ፡ ዘመን፡በቈየ፡ጊዜ፡ቀድሞ፡አልታዘዙም። 21፤ይህም፡ውሃ፡ደግሞ፡ማለት፡ጥምቅት፡ምሳሌው፡ኾኖ፡አኹን፡ያድነናል፥የሰውነትን፡እድፍ፡ማስወገድ፡ አይደለም፥ለእግዚአብሔር፡የበጎ፡ኅሊና፡ልመና፡ነው፡እንጂ፥ይህም፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ትንሣኤ፡ነው፤ 22፤ርሱም፡መላእክትና፡ሥልጣናት፡ኀይላትም፡ከተገዙለት፡በዃላ፡ወደ፡ሰማይ፡ኼዶ፡በእግዚአብሔር፡ቀኝ፡አለ።

 1-2፤ክርስቶስም፡በሥጋ፡ስለ፡እኛ፡መከራን፡ስለተቀበለ፥ከእንግዲህ፡ወዲህ፡በሥጋ፡ልትኖሩ፡በቀረላችኹ፡ ዘመን፡እንደእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡እንጂ፡እንደ፡ሰው፡ምኞት፡እንዳትኖሩ፥እናንተ፡ደግሞ፡ያን፡ዐሳብ፡እንደ፡ ዕቃ፡ጦር፡አድርጋችኹ፡ያዙት፥በሥጋ፡መከራን፡የተቀበለ፡ኀጢአትን፡ትቷልና። 3፤የአሕዛብን፡ፈቃድ፡ያደረጋችኹበት፡በመዳራትና፡በሥጋ፡ምኞትም፡በስካርም፡በዘፈንም፡ያለልክም፡ በመጠጣት፡ነውርም፡ባለበት፡በጣዖት፡ማምለክ፡የተመላለሳችኹበት፡ያለፈው፡ዘመን፡ይበቃልና። 4፤በዚህም፡ነገር፡ወደዚያ፡መዳራት፡ብዛት፡ከነርሱ፡ጋራ፡ስለማትሮጡ፡እየተሳደቡ፡ይደነቃሉ፤ 5፤ግን፡እነርሱ፡በሕያዋንና፡በሙታን፡ላይ፡ሊፈርድ፡ለተዘጋጀው፡መልስ፡ይሰጣሉ። 6፤እንደሰዎች፡በሥጋ፡እንዲፈረድባቸው፡በመንፈስ፡ግን፡እንደ፡እግዚአብሔር፡እንዲኖሩ፡ስለዚህ፡ምክንያት፡ ወንጌል፡ለሙታን፡ደግሞ፡ተሰብኮላቸው፡ነበርና። 7፤ዳሩ፡ግን፡የነገር፡ዅሉ፡መጨረሻ፡ቀርቧል።እንግዲህ፡እንደ፡ባላእምሮ፡ዐስቡ፥ 8፤ትጸልዩም፡ዘንድ፡በመጠን፡ኑሩ፤ፍቅር፡የኀጢአትን፡ብዛት፡ይሸፍናልና፥ከዅሉ፡በፊት፡ርስ፡በርሳችኹ፡ አጥብቃችኹ፡ተዋደዱ። 9፤ያለማንጐራጐር፡ርስ፡በርሳችኹ፡እንግድነትን፡ተቀባበሉ፤ 10፤ልዩ፡ልዩን፡የእግዚአብሔርን፡ጸጋ፡ደጋግ፡መጋቢዎች፡እንደ፡መኾናችኹ፥እያንዳንዳችኹ፡የጸጋን፡ስጦታ፡እንደተቀበላችኹ፡መጠን፡በዚያው፡ጸጋ፡ርስ፡በርሳችኹ፡አገልግሉ፤11፤ማንም፡ሰው፡የሚናገር፡ቢኾን፥እንደእግዚአብሔር፡ቃል፡ይናገር፤የሚያገለግልም፡ቢኾን፥እግዚአብሔር፡ በሚሰጠኝ፡ኀይል፡ነው፡ብሎ፡ያገልግል፤ክብርና፡ሥልጣን፡እስከ፡ዘለዓለም፡ድረስ፡ለርሱ፡በሚኾነው፡ በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡በኩል፡እግዚአብሔር፡በነገር፡ዅሉ፡ይከብር፡ዘንድ፤አሜን። 12፤ወዳጆች፡ሆይ፥በእናንተ፡መካከል፡እንደ፡እሳት፡ሊፈትናችኹ፡ስለሚኾነው፡መከራ፡ድንቅ፡ነገር፡እንደ፡ መጣባችኹ፡አትደነቁ፤ 13፤ነገር፡ግን፥ክብሩ፡ሲገለጥ፡ደግሞ፡ሐሤት፡እያደረጋችኹ፡ደስ፡እንዲላችኹ፥በክርስቶስ፡መከራ፡ በምትካፈሉበት፡ልክ፡ደስ፡ይበላችኹ። 14፤ስለክርስቶስ፡ስም፡ብትነቀፉ፡የክብር፡መንፈስ፡የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡በእናንተ፡ላይ፡ያርፋልና፥ብፁዓን፡ናችኹ። 15፤ከእናንተ፡ማንም፡ነፍሰ፡ገዳይ፡ወይም፡ሌባ፡ወይም፡ክፉ፡አድራጊ፡እንደሚኾን፡ወይም፡በሌላዎች፡ጕዳይ፡እንደሚገ፟ባ፟፡ኾኖ፡መከራን፡አይቀበል፤ 16፤ክርስቲያን፡እንደሚኾን፡ግን፡መከራን፡ቢቀበል፡ስለዚህ፡ስም፡እግዚአብሔርን፡ያመስግን፡እንጂ፡አይፈር። 17፤ፍርድ፡ከእግዚአብሔር፡ቤት፡ተነሥቶ፡የሚዠመርበት፡ጊዜ፡ደርሷልና፤አስቀድሞም፡በእኛ፡የሚዠመር፡ ከኾነ፡ለእግዚአብሔር፡ወንጌል፡የማይታዘዙ፡መጨረሻቸው፡ምን፡ይኾን፧ 18፤ጻድቅም፡በጭንቅ፡የሚድን፡ከኾነ፡ዐመፀኛውና፡ኀጢአተኛው፡ወዴት፡ይታይ፡ዘንድ፡አለው፧ 19፤ስለዚህ፥ደግሞ፡እንደእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡መከራን፡የሚቀበሉ፥መልካምን፡እያደረጉ፡ነፍሳቸውን፡ ለታመነ፡ፈጣሪ፡ዐደራ፡ይስጡ።

 1፤እንግዲህ፡እኔ፥ከነርሱ፡ጋራ፡ሽማግሌ፡የክርስቶስም፡መከራ፡ምስክር፡ደግሞም፡ሊገለጥ፡ካለው፡ክብር፡ ተካፋይ፡የኾንኹ፥በመካከላቸው፡ያሉትን፡ሽማግሌዎች፡እመክራቸዋለኹ፤ 2፤በእናንተ፡ዘንድ፡ያለውን፡የእግዚአብሔርን፡መንጋ፡ጠብቁ፤እንደእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡በውድ፡እንጂ፡ በግድ፡ሳይኾን፥በበጎ፡ፈቃድ፡እንጂ፡መጥፎውን፡ረብ፡በመመኘት፡ሳይኾን፡ጐብኙት፤ 3፤ለመንጋው፡ምሳሌ፡ኹኑ፡እንጂ፡ማኅበሮቻችኹን፡በኀይል፡አትግዙ፤ 4፤የእረኛዎችም፡አለቃ፡በሚገለጥበት፡ጊዜ፡የማያልፈውን፡የክብርን፡አክሊል፡ትቀበላላችኹ። 5፤እንዲሁም፥ጐበዞች፡ሆይ፥ለሽማግሌዎች፡ተገዙ፤ዅላችኹም፡ርስ፡በርሳችኹ፡እየተዋረዳችኹ፡ትሕትናን፡ እንደ፡ልብስ፡ታጠቁ፥እግዚአብሔር፡ትዕቢተኛዎችን፡ይቃወማልና፥ለትሑታን፡ግን፡ጸጋን፡ይሰጣል። 6፤እንግዲህ፡በጊዜው፡ከፍ፡እንዲያደርጋችኹ፡ከኀይለኛው፡ከእግዚአብሔር፡እጅ፡በታች፡ራሳችኹን፡አዋርዱ፤ 7፤ርሱ፡ስለ፡እናንተ፡ያስባልና፥የሚያስጨንቃችኹን፡ዅሉ፡በርሱ፡ላይ፡ጣሉት። 8፤በመጠን፡ኑሩ፡ንቁም፥ባላጋራችኹ፡ዲያብሎስ፡የሚውጠውን፡ፈልጎ፡እንደሚያገሣ፡አንበሳ፡ይዞራልና፤ 9፤በዓለም፡ያሉት፡ወንድሞቻችኹ፡ያን፡መከራ፡በሙሉ፡እንዲቀበሉ፡እያወቃችኹ፡በእምነት፡ጸንታችኹ፡ ተቃወሙት። 10፤በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ወደዘለዓለም፡ክብሩ፡የጠራችኹ፥የጸጋ፡ዅሉ፡አምላክ፥ለጥቂት፡ጊዜ፡መከራን፡ ከተቀበላችኹ፡በዃላ፥ራሱ፡ፍጹማን፡ያደርጋችዃል፥ያጸናችኹማል፥ያበረታችኹማል። 11፤ለርሱ፡ክብርና፡ኀይል፡እስከ፡ዘለዓለም፡ድረስ፡ይኹን፤አሜን። 12፤እየመከርዃችኹና፡የምትቆሙባት፡ጸጋ፡እውነተኛ፡የእግዚአብሔር፡ጸጋ፡እንድትኾን፡እየመሰከርኹላችኹ፥የታመነ፡ወንድም፡እንደ፡ኾነ፡በቈጠርኹት፡በስልዋኖስ፡እጅ፡በዐጪሩ፡ጽፌላችዃለኹ። 13፤ከእናንተ፡ጋራ፡ተመርጣ፡በባቢሎን፡ያለች፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ልጄም፡ማርቆስ፡ሰላምታ፡ያቀርቡላችዃል። 14፤በፍቅር፡አሳሳም፡ርስ፡በርሳችኹ፡ሰላምታ፡ተሰጣጡ።በክርስቶስ፡ላላችኹ፡ለኹላችኹ፡ሰላም፡ ይኹን።አሜን፨

የሁለተኛዪቱ የጴጥሮስ መልክት ምዕራፍ ፩

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

 1፤የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ባሪያና፡ሐዋርያ፡የኾነ፡ስምዖን፡ጴጥሮስ፥በአምላካችንና፡በመድኀኒታችን፡በኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ጽድቅ፡ካገኘነው፡ጋራ፡የተካከለ፡የክብር፡እምነትን፡ላገኙ፤ 2-3፤የመለኮቱ፡ኀይል፥በገዛ፡ክብሩና፡በበጎነቱ፡የጠራንን፡በማወቅ፥ለሕይወትና፡እግዚአብሔርን፡ለመምሰል፡ የሚኾነውን፡ነገር፡ዅሉ፡ስለ፡ሰጠን፥በእግዚአብሔርና፡በጌታችን፡በኢየሱስ፡ዕውቀት፡ጸጋና፡ሰላም፡ ይብዛላችኹ። 4፤ስለ፡ክፉ፡ምኞት፡በዓለም፡ካለው፡ጥፋት፡አምልጣችኹ፡ከመለኮት፡ባሕርይ፡ተካፋዮች፡በተስፋ፡ቃል፡ እንድትኾኑ፥በእነዚያ፡ክብርና፡በጎነት፡የተከበረና፡እጅግ፡ታላቅ፡የኾነ፡ተስፋን፡ሰጠን። 5፤ስለዚህም፡ምክንያት፡ትጋትን፡ዅሉ፡እያሳያችኹ፡በእምነታችኹ፡በጎነትን፡ጨምሩ፥ 6፤በበጎነትም፡ዕውቀትን፥በዕውቀትም፡ራስን፡መግዛት፥ራስንም፡በመግዛት፡መጽናትን፥በመጽናትም፡ እግዚአብሔርን፡መምሰል፥ 7፤እግዚአብሔርንም፡በመምሰል፡የወንድማማችን፡መዋደድ፥በወንድማማችም፡መዋደድ፡ፍቅርን፡ጨምሩ። 8፤እነዚህ፡ነገሮች፡ለእናንተ፡ኾነው፡ቢበዙ፥በጌታችን፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ዕውቀት፡ሥራ፡ፈቶችና፡ፍሬ፡ ቢሶች፡እንዳትኾኑ፡ያደርጓችዃልና፤ 9፤እነዚህ፡ነገሮች፡የሌሉት፡ዕውር፡ነውና፥በቅርብም፡ያለውን፡ብቻ፡ያያል፥የቀደመውንም፡ኀጢአቱን፡ መንጻት፡ረስቷል። 10፤ስለዚህ፥ወንድሞች፡ሆይ፥መጠራታችኹንና፡መመረጣችኹን፡ታጸኑ፡ዘንድ፡ከፊት፡ይልቅ፡ ትጉ፤እነዚህን፡ብታደርጉ፡ከቶ፡አትሰናከሉምና። 11፤እንዲሁ፡ወደዘለዓለሙ፡ወደጌታችንና፡መድኀኒታችን፡ወደኢየሱስ፡ክርስቶስ፡መንግሥት፡መግባት፡ በሙላት፡ይሰጣችዃልና። 12፤ስለዚህ፥እነዚህን፡ነገሮች፡ምንም፡ብታውቁ፥በእናንተም፡ዘንድ፡ባለ፡እውነት፡ምንም፡ብትጸኑ፥ስለ፡ እነዚህ፡ዘወትር፡እንዳሳስባችኹ፡ቸል፡አልልም። 13፤ዅልጊዜም፡በዚህ፡ማደሪያ፡ሳለኹ፡በማሳሰቤ፡ላነቃችኹ፡የሚገ፟ባ፟ኝ፡ይመስለኛል። 14፤ጌታችን፡ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡እንዳመለከተኝ፡ከዚህ፡ማደሪያዬ፡መለየቴ፡ፈጥኖ፡እንዲኾን፡ዐውቃለኹና። 15፤ከመውጣቴም፡በዃላ፡እነዚህን፡ነገሮች፡እንድታስቡ፡በየጊዜው፡ትችሉ፡ዘንድ፡እተጋለኹ። 16፤የርሱን፡ግርማ፡አይተን፡እንጂ፡በብልኀት፡የተፈጠረውን፡ተረት፡ሳንከተል፡የጌታችንን፡የኢየሱስ፡ ክርስቶስን፡ኀይልና፡መምጣት፡አስታወቅናችኹ። 17፤ከገናናው፡ክብር፦በርሱ፡ደስ፡የሚለኝ፡የምወደ፟ው፡ልጄ፡ይህ፡ነው፡የሚል፡ያ፡ድምፅ፡በመጣለት፡ጊዜ፡ ከእግዚአብሔር፡አብ፡ክብርንና፡ምስጋናን፡ተቀብሏልና፤ 18፤እኛም፡በቅዱሱ፡ተራራ፡ከርሱ፡ጋራ፡ሳለን፡ይህን፡ድምፅ፡ከሰማይ፡ሲወርድ፡ሰማን። 19፤ከርሱም፡ይልቅ፡እጅግ፡የጸና፡የትንቢት፡ቃል፡አለን፤ምድርም፡እስኪጠባ፡ድረስ፡የንጋትም፡ኮከብ፡ በልባችኹ፡እስኪወጣ፡ድረስ፥ሰው፡በጨለማ፡ስፍራ፡የሚበራን፡መብራት፡እንደሚጠነቀቅ፡ይህን፡ቃል፡ እየጠነቀቃችኹ፡መልካም፡ታደርጋላችኹ። 20፤ይህን፡በመዠመሪያ፡ዕወቁ፤በመጽሐፍ፡ያለውን፡ትንቢት፡ዅሉ፡ማንም፡ለገዛ፡ራሱ፡ሊተረጕም፡ አልተፈቀደም፤ 21፤ትንቢት፡ከቶ፡በሰው፡ፈቃድ፡አልመጣምና፥ዳሩ፡ግን፡በእግዚአብሔር፡ተልከው፡ቅዱሳን፡ሰዎች፡ በመንፈስ፡ቅዱስ፡ተነድተው፡ተናገሩ።

 1፤ነገር፡ግን፥ሐሰተኛዎች፡ነቢያት፡ደግሞ፡በሕዝቡ፡መካከል፡ነበሩ፡እንዲሁም፡በመካከላችኹ፡ደግሞ፡ ሐሰተኛዎች፡አስተማሪዎች፡ይኾናሉ፤እነርሱም፡የዋጃቸውን፡ጌታ፡እንኳ፡ክደው፡የሚፈጥንን፡ጥፋት፡በራሳቸው፡ ላይ፡እየሳቡ፡የሚያጠፋ፡ኑፋቄን፡አሹልከው፡ያገባሉ፤ 2፤ብዙዎችም፡በመዳራታቸው፡ይከተሏቸዋል፡በእነርሱም፡ጠንቅ፡የእውነት፡መንገድ፡ይሰደባል። 3፤ገንዘብንም፡በመመኘት፡በተፈጠረ፡ነገር፡ይረቡባችዃል፤ፍርዳቸውም፡ከጥንት፡ዠምሮ፡አይዘገይም፡ ጥፋታቸውም፡አያንቀላፋም። 4፤እግዚአብሔር፡ኀጢአትን፡ላደረጉ፡መላእክት፡ሳይራራላቸው፡ወደ፡ገሃነም፡ጥሎ፡በጨለማ፡ጕድጓድ፡ ለፍርድ፡ሊጠበቁ፡አሳልፎ፡ከሰጣቸው፥ 5፤ለቀደመውም፡ዓለም፡ሳይራራ፡ከሌላዎች፡ሰባት፡ጋራ፡ጽድቅን፡የሚሰብከውን፡ኖኅን፡አድኖ፡ በኀጢአተኛዎች፡ዓለም፡ላይ፡የጥፋትን፡ውሃ፡ካወረደ፥6፤ኀጢአትንም፡ያደርጉ፡ዘንድ፡ላሉት፡ምሳሌ፡አድርጎ፡ከተማዎችን፡ሰዶምንና፡ገሞራን፡ዐመድ፡እስኪኾኑ፡ ድረስ፡አቃጥሎና፡ገልብጦ፡ከፈረደባቸው፥ 7-8፤ጻድቅ፡ሎጥም፡በመካከላቸው፡ሲኖር፡እያየና፡እየሰማ፡ዕለት፡ዕለት፡በዐመፀኛ፡ሥራቸው፡ጻድቅ፡ ነፍሱን፡አስጨንቆ፡ነበርና፥በዐመፀኛዎች፡ሴሰኛ፡ኑሮ፡የተገፋውን፡ያን፡ጻድቅ፡ካዳነ፥ 9-10፤ጌታ፡እግዚአብሔርን፡የሚያመልኩትን፡ከፈተና፡እንዴት፡እንዲያድን፥በደለኛዎችንም፡ይልቁንም፡ በርኩስ፡ምኞት፡የሥጋን፡ፍትወት፡እየተከተሉ፡የሚመላለሱትን፡ጌትነትንም፡የሚንቁትን፡እየቀጣቸው፡ለፍርድ፡ ቀን፡እንዴት፡እንዲጠብቅ፡ያውቃል።ደፋሮችና፡ኵሩዎች፡ኾነው፡ሥልጣን፡ያላቸውን፡ሲሳደቡ፡ አይንቀጠቀጡም፤ 11፤ዳሩ፡ግን፡መላእክት፡በኀይልና፡በብርታት፡ከነርሱ፡ይልቅ፡ምንም፡ቢበልጡ፡በጌታ፡ፊት፡በእነርሱ፡ላይ፡ የስድብን፡ፍርድ፡አያመጡም። 12፤እነዚህ፡ግን፡ለመጠመድና፡ለመጥፋት፡በፍጥረታቸው፡እንደ፡ተወለዱ፡አእምሮ፡እንደ፡ ሌላቸው፡ እንስሳዎች፡ኾነው፥በማያውቁት፡ነገር፡እየተሳደቡ፡በጥፋታቸው፡ይጠፋሉ፤ 13፤የዐመፃቸውን፡ደመ፡ወዝ፡ይቀበላሉ።በቀን፡ሲዘፍኑ፡እንደ፡ተድላ፡ይቈጥሩታል፤ነውረኛዎችና፡ርኩሳን፡ ኾነው፡ከእናንተ፡ጋራ፡ሲጋበዙ፡በፍቅር፡ግብዣ፡ይዘፍናሉ፤ 14፤ምንዝር፡የሞላባቸው፡ኀጢአትንም፡የማይተዉ፡ዐይኖች፡አሏቸው፤የማይጸኑትን፡ነፍሳት፡ ያታልላሉ፤መመኘትን፡የለመደ፡ልብ፡አላቸው፤የተረገሙ፡ናቸው። 15፤ቅንን፡መንገድ፡ትተው፡ተሳሳቱ፤የባሶርን፡ልጅ፡የበለዓምን፡መንገድ፡ተከተሉ፤ርሱ፡የዐመፃን፡ደመ፡ ወዝ፡ወደደ፥ 16፤ነገር፡ግን፥ስለ፡መተላለፉ፡ተዘለፈ፤ቃል፡የሌለው፡አህያ፡በሰው፡ቃል፡ተናግሮ፡የነቢዩን፡እብድነት፡ አገደ። 17፤ድቅድቅ፡ጨለማ፡ለዘለዓለም፡የተጠበቀላቸው፡እነዚህ፡ውሃ፡የሌለባቸው፡ምንጮች፡በዐውሎ፡ነፋስም፡ የተነዱ፡ደመናዎች፡ናቸው። 18፤ከንቱና፡ከመጠን፡ይልቅ፡ታላቅ፡የኾነውን፡ቃል፡ይናገራሉና፥በስሕተትም፡ከሚኖሩት፡አኹን፡ የሚያመልጡትን፡በሥጋ፡ሴሰኛ፡ምኞት፡ያታልላሉ። 19፤ራሳቸው፡የጥፋት፡ባሪያዎች፡ኾነው፦ሐራነት፡ትወጣላችኹ፡እያሉ፡ተስፋ፡ይሰጧቸዋል፤ሰው፡ ለተሸነፈበት፡ለርሱ፡ተገዝቶ፡ባሪያ፡ነውና። 20፤በጌታችንና፡በመድኀኒታችን፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ዕውቀት፡ከዓለም፡ርኵሰት፡ካመለጡ፡በዃላ፡ዳግመኛ፡ በርሷ፡ተጠላልፈው፡የተሸነፉ፡ቢኾኑ፥ከፊተኛው፡ኑሯቸው፡ይልቅ፡የዃለኛው፡የባሰ፡ኾኖባቸዋል። 21፤ዐውቀዋት፡ከተሰጣቸው፡ከቅድስት፡ትእዛዝ፡ከሚመለሱ፡የጽድቅን፡መንገድ፡ባላወቋት፡በተሻላቸው፡ ነበርና። 22፤ውሻ፡ወደ፡ትፋቱ፡ይመለሳል፥ደግሞ፦የታጠበች፡ዕሪያ፡በጭቃ፡ለመንከባለል፡ትመለሳለች፡እንደሚባል፡እውነተኛዎች፡ምሳሌዎች፡ኾኖባቸዋል።

 1-2፤ወዳጆች፡ሆይ፥አኹን፡የምጽፍላችኹ፡መልእክት፡ይህች፡ኹለተኛዪቱ፡ናት።በቅዱሳን፡ነቢያትም፡ ቀድሞ፡የተባለውን፡ቃል፡በሐዋርያታችኹም፡ያገኛችዃትን፡የጌታንና፡የመድኀኒትን፡ትእዛዝ፡እንድታስቡ፡ በኹለቱ፡እያሳሰብዃችኹ፡ቅን፡ልቡናችኹን፡አነቃቃለኹ። 3፤በመጨረሻው፡ዘመን፡እንደ፡ራሳቸው፡ምኞት፡የሚመላለሱ፡ዘባቾች፡በመዘበት፡እንዲመጡ፡ይህን፡በፊት፡ዕወቁ፤ 4፤እነርሱም፦የመምጣቱ፡የተስፋ፡ቃል፡ወዴት፡ነው፧አባቶች፡ከሞቱባት፡ጊዜ፥ከፍጥረት፡መዠመሪያ፡ ይዞ፡ዅሉ፡እንዳለ፡ይኖራልና፥ይላሉ። 5፤ሰማያት፡ከጥንት፡ዠምረው፡ምድርም፡በእግዚአብሔር፡ቃል፡ከውሃ፡ተጋጥማ፡በውሃ፡መካከል፡እንደ፡ ነበሩ፡ወደ፟ው፡አያስተውሉምና፤ 6፤በዚህም፡ምክንያት፡ያን፡ጊዜ፡የነበረ፡ዓለም፡በውሃ፡ሰጥሞ፡ጠፋ፤ 7፤አኹን፡ያሉ፡ሰማያትና፡ምድር፡ግን፡እግዚአብሔርን፡የማያመልኩት፡ሰዎች፡እስከሚጠፉበት፡እስከፍርድ፡ ቀን፡ድረስ፡ተጠብቀው፡በዚያ፡ቃል፡ለእሳት፡ቀርተዋል። 8፤እናንተ፡ግን፡ወዳጆች፡ሆይ፥በጌታ፡ዘንድ፡አንድ፡ቀን፡እንደ፡ሺሕ፡ዓመት፥ሺሕ፡ዓመትም፡እንደ፡ አንድ፡ቀን፡እንደ፡ኾነ፡ይህን፡አንድ፡ነገር፡አትርሱ። 9፤ለአንዳንዶች፡የሚዘገይ፡እንደሚመስላቸው፡ጌታ፡ስለተስፋ፡ቃሉ፡አይዘገይም፥ነገር፡ግን፥ዅሉ፡ወደ፡ ንስሓ፡እንዲደርሱ፡እንጂ፡ማንም፡እንዳይጠፋ፡ወዶ፡ስለ፡እናንተ፡ይታገሣል። 10፤የጌታው፡ቀን፡ግን፡እንደ፡ሌባ፡ኾኖ፡ይመጣል፤በዚያም፡ቀን፡ሰማያት፡በታላቅ፡ድምፅ፡ ያልፋሉ፥የሰማይም፡ፍጥረት፡በትልቅ፡ትኵሳት፡ይቀልጣል፥ምድርም፡በርሷም፡ላይ፡የተደረገው፡ዅሉ፡ ይቃጠላል። 11-12፤ይህ፡ዅሉ፡እንዲህ፡የሚቀልጥ፡ከኾነ፥የእግዚአብሔርን፡ቀን፡መምጣት፡እየጠበቃችኹና፡ እያስቸኰላችኹ፥በቅዱስ፡ኑሮ፡እግዚአብሔርንም፡በመምሰል፡እንደ፡ምን፡ልትኾኑ፡ይገ፟ባ፟ችዃል፧ስለዚያ፡ቀን፡ሰማያት፡ተ ቃጥለው፡ይቀልጣሉ፡የሰማይም፡ፍጥረት፡በትልቅ፡ትኵሳት፡ይፈታል፤ 13፤ነገር፡ግን፥ጽድቅ፡የሚኖርባትን፡ዐዲስ፡ሰማይና፡ዐዲስ፡ምድር፡እንደተስፋ፡ቃሉ፡እንጠብቃለን። 14፤ስለዚህ፥ወዳጆች፡ሆይ፥ይህን፡እየጠበቃችኹ፡ያለነውርና፡ያለነቀፋ፡ኾናችኹ፡በሰላም፡በርሱ፡እንድትገኙ፡ ትጉ፥ 15፤የጌታችንም፡ትዕግሥት፡መዳናችኹ፡እንደ፡ኾነ፡ቍጠሩ።እንዲህም፡የተወደደው፡ወንድማችን፡ጳውሎስ፡ ደግሞ፡እንደተሰጠው፡ጥበብ፡መጠን፡ጻፈላችኹ፥በመልእክቱም፡ዅሉ፡ደግሞ፡እንደ፡ነገረ፡ስለዚህ፡ነገር፡ ተናገረ። 16፤በእነዚያ፡ዘንድ፡ለማስተዋል፡የሚያስቸግር፡ነገር፡አለ፥ያልተማሩትና፡የማይጸኑትም፡ሰዎች፡ሌላዎችን፡ መጻሕፍት፡እንደሚያጣምሙ፡እነዚህን፡ደግሞ፡ለገዛ፡ጥፋታቸው፡ያጣምማሉ። 17፤እንግዲህ፡እናንተ፥ወዳጆች፡ሆይ፥ይህን፡አስቀድማችኹ፡ስለምታውቁ፥በዐመፀኛዎቹ፡ስሕተት፡ተስባችኹ፡ከራሳችኹ፡ጽናት፡እንዳትወድቁ፡ተጠንቀቁ፤18፤ነገር፡ግን፥በጌታችንና፡በመድኀኒታችን፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ጸጋና፡ዕውቀት፡እደጉ።ለርሱ፡አኹንም፡ እስከ፡ዘለዓለምም፡ቀን፡ድረስ፡ክብር፡ይኹን፤አሜን፨


: