Jump to content

ነጨሪኸት

ከውክፔዲያ
የ16:16, 15 ጁላይ 2013 ዕትም (ከCodex Sinaiticus (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
የነጨሪኸት ምስል

ነጨሪኸት (ወይም ጆሠር) በጥንታዊ ግብጽ የነገሠ ፈርዖን ነበረ። ሹሙ እምሖተፕ መጀመርያውን ሀረም (ፒራሚድ) በሳቃራ እንዲገነባ ያዘዘው እሱ ነበር። የዘመኑ አመታት ጊዜ ልክ ባይታወቅም ምናልባት በ2982 አክልበ. የሚያሕል ነበር።

የሱ መቃበር ሀረም ከሁሉ አስቀድሞ የተገነባው ሀረም ሲሆን ከተደረቡ ደረጃዎች ተሠራ እንጂ እንደ ኋለኞቹ ሀረሞች ቅርጽ አልነበረም። በዚህ ወቅት በግዮን ሸለቆ የኖሩት ሕዝቦች የነገሥታትን ሕንጻዎች በግድ ይሠሩ ጀመር።

ነጨሪኸት ደግሞ ዘመቻ በሲና አካባቢ አድርጎ፣ በዚያ በአለት በተቀረጸው ጽሕፈት የሴት ወገንና የሔሩ ወገን ምልክቶች ይታያሉ። ከነጨሪኸት በፊት የነገሡት ፈርዖኖች ፐርብሰንኃሠኸምዊ የሴት ወገን ምልክት ወደ አርማቸው ጨምረው ቢሆንም፣ የነጨሪኸት አርማ (ሰረኽ) ግን የሔሩ ምልክት (ጭላት) ብቻ አሳየ።

የተደረጀው ሀረም