Jump to content

ንጉስ ጊንጥ

ከውክፔዲያ
የ17:28, 15 ጁላይ 2013 ዕትም (ከCodex Sinaiticus (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
የንጉሥ ጊንጥ ቅርጽ በጊንጥ ዱላ ላይ።

«ጊንጥ» (አጠራሩ በግብጽኛ ምናልባት «ሠልክ» ነው) ከግብጽ ቀድሞ ዘመነ መንግሥት ወቅት በፊት በሆነው ጊዜ የነበረ ንጉሥ። ከናርመር ትንሽ አስቀድሞ ሲገዛ በመላው አገሩ ላይ እንደ ገዛ ግን አይመስልም። ብዙ የተበለጠ መረጃ የጊንጥ ዱላ በተባለው ቅርስ ላይ ይገኛል።

አቢዶስ ከተማ፣ «ንጉሥ ጊንጥ» የተባለው ሰው መቃብር ለሥነ ቅርስ ይታወቃል። ሆኖም በአንዳንድ ሊቃውንት አስተሳሰብ፣ ይህ ግለሠብ ሌላ ንጉሥ ጊንጥ ይሆናል።