አረቄ
አረቄ የሚለው ቃል ከበርካታ የመካከለኛው ምስራቅ የአልኮል መጠጥ ስያሜ ጋር ይመሳሰላል በአረብ araq ማለት የተጣራ ማለት ነው
አረቄ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ የአልኮል መጠጥ ነው።
-
አረቄ ማውጫ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ
አረቄ አወጣጥ
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
- የኢትዮጵያ አረቄ አዘገጃጀት በአጭሩ...
1ኛ• በበቂ ሁኔታ ደርቆ የተፈጨ እኩል ይዘት ያላቸው በቆሎ እና ብቅል ማዘጋጀት (ለምሳሌ አንድ ቁና ብቅል እና አንድ ቁና በቆሎ) . 2ኛ• ብቅሉን በእንስራ አድርጎ በላዩ ላይ ውሃ መሙላት። . 3ኛ• በመቀጠልም የተፈጨው በቆሎ በዋድያት /በዝርግ እቃ/ አድርጎ በውሀ ከተንፈረፈረ በኋላ በማግስቱ በብረት ምጣድ ማንኮር። . 4ኛ• በመቀጠልም በተዘጀው ብቅል ላይ በሶስተኛው ቀን 1 እንስራ ውሃ ተጨምሮ እንኩሮው ይደረጋል። . 5ኛ• ከዚህ በኋላ ቢያንስ በ6ኛ ወይም 7ኛ ወይም 10ኛ ቀኑ እንደየሠው የሥራ ባህል እየታየ አረቄውን ጥዶ ማውጣት ይቻላል፡፡ . 6ኛ• አረቄውን ለማውጣት በእሳት ላይ የሚጣደውም እንስራ ሲሆን እንስራው ሲጣድም ጋደም /ዘንበል/ ብሎ ነው፡፡ . 7ኛ• እንስራው ሲጣድም ከቂጡ በኩል የተጣመመ ሸምበቆ በእንስራው አንገት ላይ ይሰካና የእንስራው አፍ በጭቃ ይመረጋል፡፡ ሸምበቆው የተጣመመ የሚሆንበት ምክንያትም አረቄው ከእንስራው በተጣመመው ሸንበቆ በኩል ወደ ኮዳው እንዲወርድ እንዲያግዝ ነው፡፡ በሌላ መልኩ እንስራው የሚመረግበት ምክንያትም የሚወጣው አረቄ የእንፋሎቱ ውጤት በመሆኑ እንፋሎቱ እንዳይወጣና ቀዳዳ እንስራው አፉ ላይ እንዳይኖር በማሰብ ነው፡፡ . 8ኛ• በመቀጠልም በተጣደው እንስራ አንገት ላይ ጠማማው ሸምበቆ ከተደረገ በኋ በሸምበቆው አፍ እና በኮዳው አፋ የምትገባ ቀለም መሳይ ክፍት ቀጭን ሸንበቆ ከተደረገች በኋላ በጎራሽ /ዋድያት/ ዝርግ ሸክላ ኮዳው እንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡ በመቀጠልም ከኮዳው አንገት እስኪደርስ ውሃ በጎራሹ ውስጥ እንዲሞላ ያደርጋል፡፡ [ውሃ በጎራሽ ውስጥ የሚደረግበት ምክንያት ኮዳው እንዳይፈነዳ እና ውሃው ኮዳውን እንዲያቀዘቅዘው በማሰብ ነው፡፡ ከጎራሹ ውሃ የሚደረገውም የተወሰነ እሳት ከነደደ በኋላ ነው፡፡] . 9ኛ• በመቀጠልም እሳት በተደጋጋሚ እንዲነዱበት ከተደረገ በኋላ አረቄ ሁኖ ለመውጣት እና አንድ ኮዳ ለመሙላት ቢያንስ 4 ስዓታትን ይፈጃል፡፡ እሳቱ በተደጋጋሚ ከነደደ በኋላ በመጀመሪያ የማውጣው የኮዳው አረቄ ዋናው አረቄ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ የሚገኘው አረቄ ግን ሳቢያ /መጠቅለያ/ ይባላል፡፡በዚህ መልኩ ቆንጆ የሃበሻ አረቄን ማዘጋጀት ይቻላል፡፡