Jump to content

ኤንመተና

ከውክፔዲያ
የ23:39, 7 ጁን 2013 ዕትም (ከCodex Sinaiticus (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
የንጉሥ ኤንመተና የብር ጋን

ኤንመተና[1] ከ2190 እስከ 2161 ዓክልበ. ድረስ ግድም የሱመር ከተማ ላጋሽ ንጉሥ ነበረ። ከአባቱ ከኤናናቱም በኋላ ለዘውዱ ተከተለው። ንግሥቱ ኒን-ሒሊሱ ተባለች። ኤንመተና ከኡሩክ ንጉሥና ከሱመር ላዕላይ አለቃ ከሉጋል-ኪኒሼ-ዱዱ ጋራ ስምምነት ተዋዋለ። አብረው የላጋሽን ጠላት የኡማ ንጉሶች ኡር-ሉማንና ኢሊን አሸነፉዋቸው። ከኤንመተና ዘመን አንዳንድ ቅርሶች ተገኝተዋል። ልጁም 2 ኤናናቱም ተከተለው።

ቀዳሚው
ኤናናቱም
ላጋሽ ገዥ
2190-2161 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
2 ኤናናቱም
  1. ^ ከ1966 ዓ.ም. አስቀድሞ ስሙ በኩኔፎርም ጽሕፈት እንደ ኤንተመና ይነበብ ነበር። አሁንም ብዙ ጊዜ «ኤንተመና» ተብሎ ይጻፋል። ዝርዝር ስለ ኤንመተና (እንግሊዝኛ)