Jump to content

እሑድ

ከውክፔዲያ
የ03:50, 24 ማርች 2014 ዕትም (ከ71.127.137.198 (ውይይት) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

እሑድ የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ሲሆን በቅዳሜ እና በሰኞ መካከል ይገኛል። ሰኞ የሳምንቱ መጀመሪያ ቀን በሆነባቸው አገሮች ግን እሑድ የመጨረሻ ቀን ነው።

በብዙ አብያተ ክርስትያናት ዘንድ እሑድ እንደ ሰንበት ይቆጠራል። ሆኖም በሕገ ሙሴ ሰባተኛው ቀን ቅዳሜ ሲሆን ከሥራ ሁሉ እረፍት የሚድረግበት ሰንበት ቅዳሜ ነው። እሑድ ለአረመኔ ሮማውያን ሃይማኖት ጸሐይ ያመለኩበት ቀን ስለ ነበር፣ የሮማ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስመጋቢት 10 ቀን 313 ዓ.ም. በአዋጅ እሑድ ለሮማ ዜጎች ሁሉ የእረፍት ቀን እንዲሆንላቸው አዘዘ። ጥቂት አመታት ከዚህ በኋላ ቆስጠንጢኖስ ወደ ክርስትና ቢገባም እሑድ በሮማ ሕጋዊ እረፍት ቀን ከመሆኑ አልተቋረጠም። ስለዚህ ነው እሑድ በካቶሊክና በብዙዎቹ አብያተ ክርስትያናት እስከ ዛሬ ድረስ እንደ ሰንበት የሚቆጠረው።