Jump to content

የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ

ከውክፔዲያ
የ21:03, 9 ሜይ 2017 ዕትም (ከAmaraBot (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
በመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ በስተጀርባው ያለው ትርዒት።

የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳጥንታዊ ግብጽ የተገኘ ቅርስ ሲሆን፣ ኩልን ወዘተ. ለማደባለቅ ከተጠቀሙት ሠሌዳዎች አንድ ነው። የተሠራበት ዘመን 3100 ዓክልበ. አካባቢ መሆኑ ይታመናል። ይህም በፈርዖኖች ቅድመ-ዘመን ነበረ፤ በአባይ ወንዝ ሸለቆ የነበሩት ሀገራት በአንድ የግብጽ መንግሥት ገና ሳይዋሀዱ ማለት ነው።

በሠሌዳው ፊት ላይ፣ በሦስት መስመሮች የሚራመዱ እንስሶች (ከብት፣ አህያና ፍየል) ይታያሉ። አራተኛውም መስመር አትክልትን ያሳያል። በአንዳንድ ሊቃውንት አስተሳሰብ ዘንድ፣ በአትክልቱ አጠገብ አንዱ ምልክት «ቴሄኑ» (ልብያ) የሚባል ሃይሮግሊፍ ነው፤ ስለዚህ ሠሌዳው ደግሞ የቴሄኑ ሠሌዳ ወይም የሊብያ ሠሌዳ ተብሏል። ሌሎች ሊቃውንት ግን ምልክቱ «ቴሄኑ» አይደለምና የግዮን ሸለቆ ከቶሞች ይሆናሉ ብለዋል።

በሠሌዳው ጀርባ ሰባት መንደሮች ወይም ከተሞች አሉ። እነዚህ 7 ከተሞች በግድግዳዎች ውስጥ ሲሆኑ እያንዳንዱ ከተማ በውስጡና በላዩ ልዩ ልዩ ምልክት አለበት። በላዩ ያለው ምልክት መኰትኰቻ የያዘ አውሬ፣ ተኋን ወይም ወፍ አይነት ነው። ከዚህ ጭምር በየከተማው የቅያስ ምልክቶች በልዩ ልዩ መጠኖች አሉ። በድምሩ 28 ቅያሶች አሉ፤ ይህ ምናልባት የሕዝብ ወይም የሕንፃ ብዛት ያመልክታል።

  • 1ኛው - ላይኛው ምልክት ጠፍቷል፤ የውስጡ ምልክት ጢንዚዛ፤ 4 ቅያሶች፤
  • 2ኛው - ላይኛው ምልክት የለም፤ የውስጡ ምልክት 2 ሰዎች ሲታገሉ፤ ቅያስ የለም፤
  • 3ኛው - ላይኛው ምልክት የለም፤ የውስጡ ምልክት ሺመላ፤ 7 ቅያሶች፤
  • 4ኛው - ላይኛው ምልክት ጭላት፤ የውስጡ ምልክት ጉጉት፤ 8 ቅያሶች፤
  • 5ኛው - ላይኛው ምልክት 2 ጭላቶች በዓላማዎች ላይ፣ ማረሻዎች ይዘው፤ የውስጡ ምልክት የወረቀት ተክል፤ 3 ቅያሶች፤
  • 6ኛው - ላይኛው ምልክት ጊንጥ ነው፤ የውስጡ ምልክት ቤተመንግሥት፤ 3 ቅያሶች፤
  • 7ኛው - ላይኛው ምልክት አንበሳ ነው፤ የውስጡ ምልክት የ«ካ» (ነፍስ) እጆች፣ 3 ቅያሶች።