Jump to content

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 409

ከውክፔዲያ
የ01:10, 31 ጁላይ 2022 ዕትም (ከInternetArchiveBot (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
የአውሮፕላኑ ምስል

በረራ ቁጥር ፬፻፱ ጥር ፲፯ ቀን ፳፻፪ ዓ/ም ከሊባኖስ ርዕሰ መዲና ቤይሩት ወደ አዲስ አበባ እያመራ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አየር ዠበብ፣ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ባልታወቀ አደጋ ምክንያት በሜድትራኒያን ባሕር ላይ ውድቆ የሰመጠ በረራ ነበር።

አየር ዠበቡ የቦይንግ ፯፻፴፯ ፰-ኤኤስ ሲሆን[1] በጠቅላላው ፹፪ መንገደኞችንና ፰ አብራሪዎችና አስተናጋጆችን ጭኖ ነበር። በአደጋው ፺ዎቹም ተሳፋሪዎች በሙሉ ሕይወታቸው አልፏል። ከነዚህ መኀል ፴፩ ኢትዮጵያውያን ነበሩ።