King's School, Witney

ከውክፔዲያ

The King's School በራሱ የሚተዳደር ከፊል አለማዊ ትምህርት የሚሰጥበት የክርስትያን ትምህርት ቤት ነው። የሚገኘውም በWitney፣ Oxfordshire፣ እንግሊዝ ነው። የOxfordshire Community Churches (OCC) አባል ነው።[1] በመጨረሻ የBridge Schools Inspection ምርመራ ባደረገበት ጊዜ ትምህርት ቤቱ 163 ተማሪዎች ነበሩት።[2]

ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

The King’s School በ1984 እ.ኤ.አ. በOCC አብያተ ክርስትያናት ቡድኑ ተከፈተ፣ በመጀመሪያ የሰጠው ትምህርት Accelerated Christian Education (የተፈጠነ የክርስትና ትምህርት) ስርዓቱ ነበረ። ከ1984 ጀምሮ እስከ 1989 ድረስ ትምህርት ቤቱ በተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውሮ ነበር። ትምህርት ቤቱ በመጀመሪያ የተከፈተው Merrifield house ሲሆን በኋላ ወደ Scout Houses ቀየረ እንዲሁም Cotswold Wildlife Park ላይ ለትንሽ ጊዜ የነበረ ሲሆን አሁን ወደ አለበት ቦታ ተዘዋወረ። ትምህርት ቤቱ በWitney በሚገኘው New Yatt Road በተባለው መንገድ ላይ ይገኛል።

ከትምህርት ውጭ ተግባራት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ትምህርት ቤቱ ከሰጡት ትምህርቶች ውጭ የተለያዩ አሳታፊ ፕሮግራሞች ሲኖሩት እነርሱም Sports Day (የስፖርቶች ቀን) እና Expressive Arts Week (የገላጭ-ጥበባት ሳምንት) ናቸው።

የፋሲካ ትሪሜስተር መጨረሻ ላይ ሲኒየር ተማሪዎቹ ለዓመታዊው Expressive Arts Week ክስተቱ ለአንድ ሳምንት መደበኛ ትምህርት የላቸውም።

ተማሪዎቹ የተለያዩ ቋንቋዎችን እንዲማሩ ለመርዳት ትምህርት ቤቱ ወደ ጀርመን ወይም ወደ ፈረንሳይ ሊሄዱበት የሚችሉበት የጉዞ ዕድል ይሰጣል፣ እንዲሁም በY11 (መጨረሻው ክፍል) ጊዜ በተለያዩ ሀገራት እንደ ዛምቢያ ወይም ህንድ ተማሪዎቹ የበጎ ሥራ ሊሰጡ የሚችሉባቸው ጉዞዎች አሉ።

ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Oxfordshire Community Churches
  2. ^ "The King's School". Archived from the original on 2011-09-11. በ2017-03-25 የተወሰደ.