Jump to content

ሃይማኖት

ከውክፔዲያ
የ«አብርሃማዊ» (ሮዝ) ወይንም የ«ዳርማዊ» (ቢጫ) ሃይማኖቶች ብዛት በየአገሩ

ሃይማኖት አንድ ሕብረተሠብ የሚያምንባቸው ጽኑ እምነቶች መሠረት ነው። በዓለም ውስጥ በርካታ ልዩ ልዩ ሃይማኖቶች አሉ።

ዋና ዓለማዊ ሃይማናቶች ክርስትናእስልምናአይሁድና፣ የሕንዱ ሃይማኖት እና ቡዲስም ናቸው። እነዚህ ሃይማኖቶች በአንዳንድ አገር በይፋ የመንግሥት ሃይማኖት ሁኔታ አላቸው። ከነዚህ መጀመርያ ሦስቱ. ክርስትና፣ እስልምናና አይሁድና፣ ሁላቸው ከአብርሐም ስለ ተነሡ፣ «አብርሃማዊ ሃይማኖቶች» ተብለዋል። ሒንዱኢዝምና ቡዲስም ግን ከሕንድ ተነሡና «ሕንዳዊ» ወይም «ዳርማዊ ሃይማኖቶች» ተብለዋል።

ሌሎች ሃይማኖቶች በአሁኑ ሰዓት በየትም አገር የመንግሥት ሃይማኖት ባይሆኑም፣ ባለፉት ዘመናት በታሪክ መንግሥታት ይኖራቸው ነበር፦ በተለይ ዛርጡሽናጃይኒስምሲኪስምዳዊስምየኮንግ-ፉጸ ትምህርትሺንቶና የተለያዩ ኗሪ ወይም አረመኔ ሃይማኖቶች የቀድሞ መንግሥታት ነበሯቸው፤ የጠፉት ሃይማኖቶች ማኒኪስም እና አሪያኒስም ደግሞ የቀድሞ መንግስታት ነበሯቸው።

በተጨማሪ መቸም መንግስት ያልነበረላቸው በርካታ ሌሎች አነስተኛ ሃይማኖቶች ወይም እምነቶች አሉ ወይም በታሪክ ተገኝተዋል።

በአንዳንድ አስተሳሰብ ማርክሲስም-ሌኒኒስም በሃይማኖት ፈንታ የአንዳንድ መንግሥት ፍልስፍና፣ ትምህርት ወይም ርዕዮተ ዓለም በመሆኑ በውኑ እንደ አንድ ሃይማኖት መቆጠሩ ተገቢ ነው።

: