ከ«የኒካራጓ ምልክት ቋንቋ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
መስመር፡ 27፦ መስመር፡ 27፦
[[nl:Nicaraguaanse gebarentaal]]
[[nl:Nicaraguaanse gebarentaal]]
[[no:Nicaraguansk tegnspråk]]
[[no:Nicaraguansk tegnspråk]]
[[os:Никарагуæйы жестты æвзаг]]
[[pt:Língua de Sinais Nicaraguense]]
[[pt:Língua de Sinais Nicaraguense]]
[[scn:Linguaggiu dî signa nicaraguenzi]]
[[scn:Linguaggiu dî signa nicaraguenzi]]

እትም በ23:17, 26 ጃንዩዌሪ 2009


የኒካራጓ እጅ ቋንቋ (ISN, Idioma de Señas de Nicaragua ወይም Idioma de Signos Nicaragüense) በ1970ዎቹና በ1980ዎቹ በምዕራብ ኒካራጓ የጆሮ ድንቁርና ባለባቸው ተማሪዎች የተለማ የእጅ ምልክት ቋንቋ ነው። የተለማው ከቆዩት እጅ ቋንቋዎች ሳይሆን በተማሪዎች እራሳቸው በድንገት ነበር። ስለዚህ ለቋንቋ ሊቃውንት "የመነጋገር ልደት" ወይም የመንስኤው ሁኔታ ለማጥናት ያስችላል።

ከ1969 ዓ.ም. በፊት በኒካራጓ ድንቁርና ላለባቸው ሰዎች ኅብረተሠብ አልነበረባቸውም። ከቤተሠቦቻቸው ጋራ ለመነጋገር ይቻሉ ቀላል በሆነ እጅ ንቅናቄ ብቻ ነበር።

በ1969 ዓ.ም. ግን ጆሯቸው ለማይስማ ተማሪዎች ልዩ ተምህርት ቤት በዋና ከተማ በማናጓ ስለ ተመሠረተላቸው 50 ተማሪዎች ወዲያው ትምህርታቸውን ጀመሩ። የሳንዲኒስታ አብዮት በሆነበት ወቅት (1971 ዓ.ም.) መቶ ተማሪዎች ነበሩ። በ1972 ሁለተኛ ልዩ ትምህርት ቤት ተከፍቶ በ1975 ዓ.ም. የተማሪዎች ቁጥር 400 ደረሰ።

በመጀመርያ ትምህርት ቤቶቹ የከንፈር ማንበብየጣት ፊደል ብቻ ለማስተማር አስበው ይህ ዘዴ ግን አልተከናወንም። ዳሩ ግን ተማሪዎቹ በትርፍ ጊዜያቸው በቤተሠቦቻቸው የተጠቀሙትን እጅ ምልክቶች እርስ በርስ ስለተማማሩ በትንሽ ጊዜ የራሳቸውን ቋንቋ ፈጠሩ።

የትምህርት ቤት አስተማሪዎች ግን ስለዚህ ልማት አላወቁም ነበር። የእጅ ምልክቶቻቸው እንደ ጨዋታ ብቻ መስሏቸው እስፓንኛ መማር ስለማይችሉ ይሆናል በማሰብ ገመቱ። እንዲግባቡ ከቶ ስላልቻሉ በመጨረሻ በ1978 ዓ.ም. ከአሜሪካ አንዲት የአሜሪካ እጅ ቋንቋ መምህር ጁዲ ኬግል አስመጥተው እሷ ምልክቶቻቸውን በድንብ ለማጥናት ወሰነች። ያልታወቀ አዲስ ቋንቋ መሆኑን የገለጠች እርሷ ሆነች።