ከ«አለቃ አያሌው ታምሩ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 1፦ መስመር፡ 1፦
[[Image:Aleqa_ayalew_tamiru.jpg|thumb|አለቃ አያለው ታምሩ]]
[[Image:Aleqa_ayalew_tamiru.jpg|thumb|አለቃ አያለው ታምሩ]]
'''አለቃ አያሌው ታምሩ''' ከአባታቸው ከአቶ ታምሩ የተመኝና ከእናታቸው ከወይዘሮ አሞኘሽ አምባዬ፤ በ[[ጎጃም]] ክፍለ ሀገር በብቸና አውራጃ በእነማይ ወረዳ በታላቁ ደብር ወገዳም [[በደብረ ድማኅ ቅዱስ ጊዮርጊስ]] ልዩ ስሙ ቤተ ንጉሥ
'''አለቃ አያሌው ታምሩ''' ከአባታቸው ከአቶ ታምሩ የተመኝና ከእናታቸው ከወይዘሮ አሞኘሽ አምባዬ፤ በ[[ጎጃም]] ክፍለ ሀገር በብቸና አውራጃ በእነማይ ወረዳ በታላቁ ደብር ወገዳም [[በደብረ ድማኅ ቅዱስ ጊዮርጊስ]] ልዩ ስሙ ቤተ ንጉሥ
በተባለ ቦታ [[መጋቢት ፳፫]] ቀን [[1915|፲፱፻፲፭]] ዓመተ ምሕረት በዕለተ ሆሣዕና ተወለዱ። ዕድሜአቸው ለትምህርት ሳይደርስ ገና የሦስት ዓመት ተኩል ሕፃን ሳሉ በፈንጣጣ ሕመም ምክንያት የዐይናቸውን ብርሃን አጥተዋል። የስምንት ዓመት ዕድሜ ልጅ ሳሉ በዓለ ተክለ አልፋን ለማክበር ከአባታቸው ጋር ወደ ዲማ እንደ ሄዱ በዚያው ትምህርታቸውን ለመቀጠል ቀሩ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮም በቅርብ ቤተ ዘመድ እየተረዱ ለአንድ ዓመት ያህል ሲማሩ ከቈዩ በኋላ አባታቸው ስላረፉ ኑሮአቸው በትምህርት ቤት ብቻ ስለ ተወሰነ ከቤተ ሰብእ ጋር የነበራቸው ግንኙነት እየቀነሰ መጣ። ይህም ሁኔታ የሚፈልጉትን ትምህርት በአንድ ልብ ለመቀጠል ግድ ሆኖባቸዋል።
በተባለ ቦታ [[መጋቢት 23|መጋቢት ፳፫]] ቀን [[1915|፲፱፻፲፭]] ዓመተ ምሕረት በዕለተ ሆሣዕና ተወለዱ። ዕድሜአቸው ለትምህርት ሳይደርስ ገና የሦስት ዓመት ተኩል ሕፃን ሳሉ በፈንጣጣ ሕመም ምክንያት የዐይናቸውን ብርሃን አጥተዋል። የስምንት ዓመት ዕድሜ ልጅ ሳሉ በዓለ ተክለ አልፋን ለማክበር ከአባታቸው ጋር ወደ ዲማ እንደ ሄዱ በዚያው ትምህርታቸውን ለመቀጠል ቀሩ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮም በቅርብ ቤተ ዘመድ እየተረዱ ለአንድ ዓመት ያህል ሲማሩ ከቈዩ በኋላ አባታቸው ስላረፉ ኑሮአቸው በትምህርት ቤት ብቻ ስለ ተወሰነ ከቤተ ሰብእ ጋር የነበራቸው ግንኙነት እየቀነሰ መጣ። ይህም ሁኔታ የሚፈልጉትን ትምህርት በአንድ ልብ ለመቀጠል ግድ ሆኖባቸዋል።


በዚሁ መሠረት በ፲፭ ዓመት ዕድሜአቸው የቅኔ መምህር ለመሆን በቅተዋል። ስለ ዐይናቸው ብርሃንና ስለ ትምህርታቸው፤ «ምልጃ ዕርቅና ሰላም፤» በተባለው መጽሐፋቸው ገጽ ፬ ላይ እንዲህ ሲሉ ገለጸዋል። «ይህ ሁሉ የተገኘው ገና በልጅነት ዕድሜዬ፤ በቅዱስ ሐዋርያ ያዕቆብ እንደ ተነገረው የምመራበት፣ የምኖረበት በወሰድከው በዐይኔ ፈንታ ዕውቀት ስጠኝ ብዬ የለመንኩት አምላኬ፤ «ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ሹ ታገኛላችሁ፤ በር ምቱ ይከፈትላችኋል፤ ለሚወደኝ እኔ ራሴን እገልጥለታለሁ፤»
በዚሁ መሠረት በ፲፭ ዓመት ዕድሜአቸው የቅኔ መምህር ለመሆን በቅተዋል። ስለ ዐይናቸው ብርሃንና ስለ ትምህርታቸው፤ «ምልጃ ዕርቅና ሰላም፤» በተባለው መጽሐፋቸው ገጽ ፬ ላይ እንዲህ ሲሉ ገለጸዋል። «ይህ ሁሉ የተገኘው ገና በልጅነት ዕድሜዬ፤ በቅዱስ ሐዋርያ ያዕቆብ እንደ ተነገረው የምመራበት፣ የምኖረበት በወሰድከው በዐይኔ ፈንታ ዕውቀት ስጠኝ ብዬ የለመንኩት አምላኬ፤ «ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ሹ ታገኛላችሁ፤ በር ምቱ ይከፈትላችኋል፤ ለሚወደኝ እኔ ራሴን እገልጥለታለሁ፤»

እትም በ15:17, 6 ኖቬምበር 2009

አለቃ አያለው ታምሩ

አለቃ አያሌው ታምሩ ከአባታቸው ከአቶ ታምሩ የተመኝና ከእናታቸው ከወይዘሮ አሞኘሽ አምባዬ፤ በጎጃም ክፍለ ሀገር በብቸና አውራጃ በእነማይ ወረዳ በታላቁ ደብር ወገዳም በደብረ ድማኅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዩ ስሙ ቤተ ንጉሥ በተባለ ቦታ መጋቢት ፳፫ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓመተ ምሕረት በዕለተ ሆሣዕና ተወለዱ። ዕድሜአቸው ለትምህርት ሳይደርስ ገና የሦስት ዓመት ተኩል ሕፃን ሳሉ በፈንጣጣ ሕመም ምክንያት የዐይናቸውን ብርሃን አጥተዋል። የስምንት ዓመት ዕድሜ ልጅ ሳሉ በዓለ ተክለ አልፋን ለማክበር ከአባታቸው ጋር ወደ ዲማ እንደ ሄዱ በዚያው ትምህርታቸውን ለመቀጠል ቀሩ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮም በቅርብ ቤተ ዘመድ እየተረዱ ለአንድ ዓመት ያህል ሲማሩ ከቈዩ በኋላ አባታቸው ስላረፉ ኑሮአቸው በትምህርት ቤት ብቻ ስለ ተወሰነ ከቤተ ሰብእ ጋር የነበራቸው ግንኙነት እየቀነሰ መጣ። ይህም ሁኔታ የሚፈልጉትን ትምህርት በአንድ ልብ ለመቀጠል ግድ ሆኖባቸዋል።

በዚሁ መሠረት በ፲፭ ዓመት ዕድሜአቸው የቅኔ መምህር ለመሆን በቅተዋል። ስለ ዐይናቸው ብርሃንና ስለ ትምህርታቸው፤ «ምልጃ ዕርቅና ሰላም፤» በተባለው መጽሐፋቸው ገጽ ፬ ላይ እንዲህ ሲሉ ገለጸዋል። «ይህ ሁሉ የተገኘው ገና በልጅነት ዕድሜዬ፤ በቅዱስ ሐዋርያ ያዕቆብ እንደ ተነገረው የምመራበት፣ የምኖረበት በወሰድከው በዐይኔ ፈንታ ዕውቀት ስጠኝ ብዬ የለመንኩት አምላኬ፤ «ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ሹ ታገኛላችሁ፤ በር ምቱ ይከፈትላችኋል፤ ለሚወደኝ እኔ ራሴን እገልጥለታለሁ፤» ሲል በሰጠው ተስፋና በለገሰኝ የአእምሮ ምጽዋት መሆኑን ስለምረዳ ነው፤» ብለዋል።

ክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፥ ትምህርት፥ ሥርዐትና አስተዳደር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለወጠና እየተበላሸ መሄዱ በእጅጉ ያሳዝናቸው ስለ ነበር፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሊቃውንት ጉባኤ ዋና ሰብሳቢ እንደ መሆናቸው መጠን፤ ጥፋቱ እንዲታረም ብዙ አቤቱታና ተማጽኖ ጉዳዩ ወደሚመለከተው ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ፤ ሲኖዶሱን በመሠረተና በሚመራው በመንፈስ ቅዱስ ስም ተማጽነው ቢያቀርቡም ሲኖዶሱ ጉዳዩን ለማፈን ከመሞከር በስተቀር ምንም እርምጃ ሳይወስድ ቀርቷል። እሳቸውም ያቀረቡት ጥያቄ መፍትሔ ባለማግኘቱ ጉዳዩን ለሚመለከተው ለኢተዮጵያ ሕዝበ ክርስቲያን ለማሳወቅና፤ በቤተ ክርስቲያን ላይ ዐመፅ የሚፈጽሙትን ፓትርያርኩንና የእሳቸው ተባባሪ የሆኑ ጳጳሳትን ባላቸው ከፍተኛ ኀላፊነተና ሥልጣነ ክህነት በሥልጣነ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፥ በሥልጣነ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ለማውገዝ ተገደዋል። ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ የዐመፀኛውን ፓትርያርክ ስም እንዳይጠሩ ውግዘት አስተላልፈዋል። ምእመናንም ከዐመፀኞች ካህናት ምንም ዐይነት አገልገሎት ማገኘት የማይችሉ መሆናቸውን ተገንዝበው ሕይወታቸውን በጥንቃቄ እንዲመሩ አሳስበዋል። በዚህም ምክንያት ከ፶ ዓመት በላይ ካገለገሉበት የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በሐሰት ክስና የእምነት ክሕደት ቃላቸውን ባልሰጡበት ሁኔታ ያለ ምንም ጡረታ ከሥራ ገበታቸው ላይ በግፍ እንዲነሡ በመደረጉ ከሚያዝያ ወር ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው በመኖሪያ ቤታቸው ተወስነው ኖረዋል። በነዚህ ዓመታትም በየዕለቱ ለጸሎት ባዘጋጇት አነስተኛ ክፍል በመገኘት ወደ ልዑል እግዚአብሔር በመጸለይና በማልቀስ ይተጉ ነበር። ምእመናንም በተኲላ እንዳይነጠቁ በተለያዩ ጋዜጦች ትምህርትና ማበረታቻ ሲሰጡ ኖረዋል።

የክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ የቀብር ሥነ ሥርዐት ነሐሴ ፲፯ ቀን ፲፱፻፺፱ ዓመተ ምሕረት ብዙ ዘመን ባገለገሉበት የአዲስ አበባው ደብረ አሚን ተክለ ኃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ብዙ ሕዝብ በተገኘበት ተፈጽሟል።

ክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ በቤተ ክርስቲያን ሥርዐት መሠረት በሥርዐተ ተክሊል ከወይዘሮ ርብቃ ልሳነ ወርቅ ጋር ሚያዝያ ፲፪ ቀን ፲፱፻፶ ዓመተ ምሕረት ጋብቻ ፈጽመው ፲፬ ልጆችና ፲፪ የልጅ ልጆች ለማፍራት ታድለዋል።

መንፈሳዊ አገልግሎትና አስተዳደር።

  • ወደ አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ ዛሬ የክቡር ዐፅማቸው ማረፊያ በሆነው ደብረ አሚን ተክለ ኃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የቅኔ መምህርነት አገልግሎታቸውን በ፲፱፻፴፱ ዓመተ ምሕረት ጀመሩ። በመቀጠልም በዚሁ ደብር፤ መጀመሪያ የሊቀ ጠበብትነት ማዕረግ አግኝተው ያገለገሉ ሲሆን ኋላም የዚሁ ደብር አስተዳዳሪ በመሆን ሰፊ አገልግሎት አበርክተዋል።
  • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሊቃውንት ጉባኤ ተመርጠው ከሰኔ ወር ፲፱፻፵፰ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ የስብከተ ወንጌል ክፍል አባል ሆነው አገልግለዋል።
  • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ አባልና ዋና ሰብሳቢ ሆነው ሠርተዋል። በዚህም የሥራ ዘመናቸው፤ የቤተ ክርስቲያን የወንጌል ትምህርት በመሆኑ ይህ አገልግሎት ሳይበረዝና ሳይከለስ እምነቱም፣ ትምህርቱም፣ ሥርዐቱም ተጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ የሚያስችለውን መንገድ ለመቀየስ በተሰጣቸው ኀላፊነት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሌት ተቀን ሠርተዋል።
  • አልፎ አልፎም ከውስጥም ሆነ ከውጪ ለሚነሡት መናፍቃን መልስ በመስጠት፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ በየጊዜው የሚታተሙትን መጻሕፍት በማረምና ለኅትመት እንዲበቁ በማድረግ፤ ስለ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ስለ ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት፤ በበዓላትም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች በራዲዮ፥ በቴሌቪዥን፥ በመጽሔቶችና በጋዜጦች ትምህርትና ምክር በማስተላለፍ ሀገራዊና ሃይማኖታዊ ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል።
  • ሐዲስ ኪዳንን በግእዝና በአማርኛ ፥ መጽሐፈ ግጻዌ፥ ሃይማኖተ አበው የተባሉትን መጻሕፍት ከሌሎች የጉባኤው አባላት ጋር ተርጉመው እንዲታተሙ አድርገዋል።
  • ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መንፈሳዊ ኰሌጅ ከ፲፱፻፶፬ እስከ ፲፱፻፷፬ ዓመተ ምሕረት፤ እንዲሁም በተግባረ እድ ትምህርት ቤትና በቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት መንፈሳዊ ትምህርት አስተምረዋል።
  • ከኢትዮጵያ ዓይነ ሥውራን ማኅበር መሥራቾች አንዱ ሲሆኑ፤ መጀመሪያ የማኅበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ኋላም የቦርድ ሊቀ መንበር በመሆን አገልግለዋል።

የአለቃ አያሌው መጻሕፍት

በመጽሐፍ ጥራዝ አዘጋጅተውና አሳትመው ለትውልድ ያስተላለፏቸው መጻሕፍት ዘጠኝ ሲሆኑ በይዘታቸው በሁለት የተከፈሉ ናቸው። በአንደኛው ክፍል ያሉት የቤተ ክርስቲያንንና የኢተዮጵያን ማንነት ለኢትዮጵያውያን ለማስተማር የተዘጋጁ ሲሆኑ፤ በሁለተኛው ክፍል ያሉት ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥም ሆነ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ለተነሡና ለሚነሡ መናፍቃን መልስ በመስጠት የምእመናንን ልቦና ለማጽናት የሚያስችል መልእክት የሚያስተላልፉ ናቸው። ከነዚህ መጻሕፍት ውስጥ ዐምስቱ በቤተ ክህነት አገልገሎት ላይ የተዘጋጁ ሲሆኑ፤ አራቱ ደግሞ ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በግፍ ከታገዱበት ከ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት በኋላ የተዘጋጁ ናቸው።

በቤተ ክህነት አገልገሎት ላይ በነበሩበት ጊዜ ያዘጋጇቸው፤

  • «መች ተለመደና ከተኲላ ዝምድና»፥
  • «የኢትዮጵያ እምነት በሦስቱ ሕግጋት»፥
  • «የኑሮ መሠረት ለሕፃናት»፥
  • «ወላዲተ አምላክ በኢትዮጵያ»፥
  • «የጽድቅ በር»

የተባሉት መጻሕፍት ሲሆኑ፣ ከሥራ ገበታ ከታገዱ በኋላ በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ያዘጋጇቸው፤

  • «ምልጃ፥ ዕርቅና ሰላም»፥
  • «ተአምርና መጽሐፍ ቅዱስ»፥
  • «መልእክተ መንፈስ ቅዱስ»፥
  • «ዜና ሕይወት ዘቅድስተ ቅዱሳን እመ አምላክ»

የተባሉት ናቸው።

ማስታወሻ

የኢትዮጵያ እምነት በሶስቱ ሕግጋት http://www.aleqayalewtamiru.org/files/yehiwot_tarik.pdf