ከ«ቡና» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
Carte Coffea robusta arabica 2
ሎሌ መጨመር: wuu:咖啡
መስመር፡ 139፦ መስመር፡ 139፦
[[vls:Kaffie]]
[[vls:Kaffie]]
[[war:Kape]]
[[war:Kape]]
[[wuu:咖啡]]
[[yi:קאווע]]
[[yi:קאווע]]
[[zh:咖啡]]
[[zh:咖啡]]

እትም በ11:19, 2 ጁላይ 2010

ቡና
ቡና
ቡና

ቡና የተክል አይነትና ከዚህ ተክል ቡን የሚወጣው መጠጥ ነው። መጀመርያ የታወቀው በኢትዮጵያ ሲሆን በዓለሙ ልሳናት ስሙ የተነሣ (ለምሳሌ እንግሊዝኛcoffee /ኮፊ/) ምናልባት ከድሮው ከፋ መንግሥት ሊሆን ይቻላል። በአንድ ትውፊት መሠረት በመጀመርያ ያገኘው ሰው ካልዲ የተባለ አንድ ኢትዮጵያዊ እረኛ ፍየሎቹ ፍሬውን በልተው ሲጨፍሩበት ነበረ።

የቡናው የስን ፍጥረት ስሙ Coffea arabica (ካፊ ኣራቢካ) ሲሆን የዚህ የኢትዮጵያ ቡና ዘር በጣዕሙ ጥሩነት የተነሳ በጣም ተወዳጅ ነው።

በደራሲው ዊሊያም ኡከርስ መጽሐፍ 'ኦል አባውት ኮፊ' (ሁሉ ስለ ቡና) ኅልዮ ቡና ወደ የመን የገባው በአክሱም መንግሥት ዘመን በ517 ዓ.ም. አካባቢ ነበር። የፋርስ ሃኪም አል-ራዚ (857-917 ዓ.ም. የኖሩ) ተክሉን «ቡንቹም» ብሎት ምናልባት በታሪክ አንደኛው ስለ ቡና መግለጫ የመዘገበው ጸሐፊ ይሆናል። ደግሞ ሌላ ፋርስ ሀኪም እብን-ሲና (972-1029 ዓ.ም.) ስለ «ቡንቹም» ጥቅም ጽፏል። የሞሮኮ ደርቡሽ ሼክ አቡል-ሀሳን አሽ-ሻዲሊ (1167-1250 ዓ.ም.) በአሠብ ዙሪያ ሲጓዙ ኗሪዎች ስለ ቡና መጠጥ እንዳሳወቁት ይባላል። የአደን ሙፍቲ ሼክ ጃማል-አል-ዲን አል-ዳባኒ በ1446 ዓ.ም. ገዳማ መጀመርያ መጠቱን እንዳስገባ ይመዘገባል። በ1449 ዓ.ም. መጀመርያው ቡና ቤት «ኪቫ ሃን» በኢስታንቡል ቱርክ ተከፈተ።

ሆኖም በ1503 ዓ.ም. የማካህ ይማሞች ቡና ቤት ስላልወደዱ መጠጡን ሃራም (እርም) አሉት[1]። ነገር ግን የኦቶማን ቱርክ ሡልጣን 1 ሰሊም1509 ዓ.ም. ማካህን ይዘውት በ1516 ዓ.ም. ይህን ድንጋጌ ገልብጠው የተቀደሰ መጠት አደረገው። ከዚያ በኋላ እስላሞች በተለይ ቡናን ስለወደዱት፣ ለኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እስከ 1881 ዓ.ም. ድረስ እንደ ተከለከለ ዛሬ በሰፊ አይታወቅም። ከ1872 እስከ 1878 ድረስ ቡና መጠጥ በኢትዮጵያ ቶሎ ስለ ተስፋፋ አጼ ምኒልክ ቢሆኑም ስለ ጠጡት በ1881 ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ሆነው አቡነ ማቴዎስ 10ኛ ቡናን አጸደቁት።

ቡና ወደ አውሮፓ መጀመርያ በ16ኛ ክፍለ ዘመን ያስገቡት ነጋዴዎች ከቬኒዝ ጣልያ ነበሩ። በ1592 ዓ.ም. የሮማ ፓፓ 8 ቄሌምንጦስ ስላጸደቁት በቶሎ ዘመናዊ መጠት ሆነ። መጀመርያው ቡና ቤት በአውሮፓ በጣልያ1637 ዓ.ም. ተከፈተ።

አረቦች ግን አጥብቀው ለምለሙን ተክል ከአረብ ዓለም እንዲወጣ ምንም ባይፈቅዱም፣ በ1600-1650 ዓ.ም. ገዳማ አንድ ሃጂ እስላም ከሕንድ ስሙም ባባ ቡዳንሞቃ የመን ወጥቶ በስውር የቡና ዘር ይዞ ወደ ሚሶር ሕንድ አገር ተመለሰና ተክሉን እዚያ አበቀለው። በ1608 ዓ.ም. የሆላንድ ሰዎች ወደ አደን መጥተው ለምለም የቡና ዘር ይዘው ወደ አገራቸው ተመለሡ። በ1690ዎቹ በሆላንድ ቅኝ አገሮች በጃቫ (ዛሬ ኢንዶኔዥያ) እና በሱሪናም (ደቡብ አሜሪካ) ያስፋፉት ጀመር።

በኣሁኑ ጊዜ ቡና በዓለም ላይ ከሚጠጡ መጠጦች ኣንደኛን ስፍራ ይዟል። በተጨማሪም የቡና ቅጠል በወተት ተፈልቶ ቁጢ እንዲሁም የቡና ዘር ቀፎው ተፈልቶ የሚጠጣው ኣሻራ ተወዳጆች ናቸው። ቁጢና ኣሻራ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚታውቁ ኣይመስልም።

  1. ^ http://www.hoboes.com/Politics/Prohibition/Notes/Coffee/

የውጭ መያያዣ


መለጠፊያ:Link FA መለጠፊያ:Link FA መለጠፊያ:Link FA መለጠፊያ:Link FA