ከ«ግሪክ (አገር)» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት
ጥ ሎሌ መጨመር: rn:Grecia |
WikitanvirBot (ውይይት | አስተዋጽኦ) ጥ r2.7.1) (ሎሌ ማስተካከል: nah:Grecia |
||
መስመር፡ 164፦ | መስመር፡ 164፦ | ||
[[mzn:یونان]] |
[[mzn:یونان]] |
||
[[na:Greece]] |
[[na:Greece]] |
||
[[nah:Grecia |
[[nah:Grecia]] |
||
[[nap:Gracia]] |
[[nap:Gracia]] |
||
[[nds:Grekenland]] |
[[nds:Grekenland]] |
እትም በ11:03, 3 ጁን 2011
Ελληνική Δημοκρατία |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ዋና ከተማ | አቴና | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ግሪክ | |||||
መንግሥት ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር |
ካሮሎስ ፓፑሊያስ ኮስታስ ካራማንሊስ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) |
131,990 (96ኛ) |
|||||
ገንዘብ | ዩሮ | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +2 | |||||
የስልክ መግቢያ | +30 |
መልከዐምድር
ግሪክ ወደ ሜዴቴሪኒያን ባሕር የተዘረጋ አንድ ትንሽ ቁራጭ አገር ነው። ከምሥራቅ ወደ ትንሽ እስያ፤ ከምዕራብ ወደ ኢጣሊያ አገር ከሁለቱም ወገን ርቀቱ ትክክል ነው። ግሪክ በሰሜን ወገን ከመቄዶንያ ይዋሰናል። ግሪክ ዙሪያውን በባሕር የታጠረ ነው።
በደቡብና በምሥራቅ ወገን አያሎች ደሴቶች አሉ። ከነርሱም አያሎች መንደሮችና ከተሞች ተሠርተውባቸዋል። አንዱ አንቲፖሮስ ይባላል። በዚህም ስፍራ ያለው ታላቅ ያጌጠ ዋሻ የታወቀ ስመ ጥሩ ነው።
እኩሌቶቹም የግሪክ ደሴቶች ከባሕር ወደ ውጪ እየተወረወሩ የወጡ ይመስላሉ። እኩሌቶቹም ከጥንት ጀምረው ይታዩ የነበሩት ያሉበት አይታወቅም ጠፍተዋል። ይህ እንግዳ ነገር እንዲህ እንዲሆን ያደረገው ከባሕር በታች የተነሳው እሳተ ጎመራ ነው።
በደቡብ ግሪክ ወገን ባሉት ደሴቶች አየሩ በአሜሪካ እንዳለው እንደ ቨርጂኒያ ግዛት አየር ቀላል ነው። በዚህ አገር ብዙ አይነት ፍሬ ሁሉ ሞልቶዋል። በሰሜን በኩል ደግሞ አየሩ ቅዝቃዜ ያለበት ነው።
በየጠረፉ የመርከብ መቋሚያዎች ወደቦች ይገኛሉ። ብዙዎቹ የአገሩ ሰዎችም መርከበኞች ናቸው። በደኑም ፓይን (ጥድ) የተባለው ጠንካራ ዛፍ ይገኛል። በላይኛው አውራጃ ኦክ የተባለው ዛፍ ይገኛል። ወደታች ባለው ክፍልም ቸስትነትና ዋልነት የሚባሉት ዕንጨቶች ይገኛሉ።
በዚህ ስፍራ የሚገኘው ዋናው ነገር ደረቅ ፍራፍሬ፣ ዘቢብ፣ ጥጥ፣ ሐር ጠጉር፣ ሩዝ፣ ትንባሆና በቆሎ ነው። የእጅ ሥራ ጥቂት ነው። በቤት የተለመደ ሥራ እንደ ጥጥ እንደ ጠጉር እንደ ሐር የመሰለ ነገር ነው። ቀለም ማግባት ወይም መቀባት በጣም የተለመደ ከሆነ ብዙ ጊዜው ሆነው።
ከዛፎች ፍሬ ዋነኛው ወይራ ሲሆን በብዛት ይተከላል። ወይን፣ በኽረ? ሎሚ፣ በለስ፣ አልሞንድ (ለውዝ)፣ ተምር፣ ሴትሮን፣ ፓሜግራኔት (ሮማን)፣ ኩሬንትም ይበቅላሉ።
|
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |