ከ«ግሪክ (አገር)» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
r2.7.1) (ሎሌ ማስተካከል: nah:Grecia
ሎሌ መጨመር: mg:Grisy
መስመር፡ 153፦ መስመር፡ 153፦
[[lv:Grieķija]]
[[lv:Grieķija]]
[[mdf:Грекмастор]]
[[mdf:Грекмастор]]
[[mg:Grisy]]
[[mhr:Греций]]
[[mhr:Греций]]
[[mi:Kirihi]]
[[mi:Kirihi]]

እትም በ03:22, 12 ጁን 2011

Ελληνική Δημοκρατία
የግሪክ ዲሞክራሲ

የግሪክ ሰንደቅ ዓላማ የግሪክ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
የግሪክመገኛ
የግሪክመገኛ
ዋና ከተማ አቴና
ብሔራዊ ቋንቋዎች ግሪክ
መንግሥት
ፕሬዝዳንት
ጠቅላይ ሚኒስትር
 
ካሮሎስ ፓፑሊያስ
ኮስታስ ካራማንሊስ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
131,990 (96ኛ)
ገንዘብ ዩሮ
ሰዓት ክልል UTC +2
የስልክ መግቢያ +30


መልከዐምድር

ግሪክ ወደ ሜዴቴሪኒያን ባሕር የተዘረጋ አንድ ትንሽ ቁራጭ አገር ነው። ከምሥራቅ ወደ ትንሽ እስያ፤ ከምዕራብ ወደ ኢጣሊያ አገር ከሁለቱም ወገን ርቀቱ ትክክል ነው። ግሪክ በሰሜን ወገን ከመቄዶንያ ይዋሰናል። ግሪክ ዙሪያውን በባሕር የታጠረ ነው።

በደቡብና በምሥራቅ ወገን አያሎች ደሴቶች አሉ። ከነርሱም አያሎች መንደሮችና ከተሞች ተሠርተውባቸዋል። አንዱ አንቲፖሮስ ይባላል። በዚህም ስፍራ ያለው ታላቅ ያጌጠ ዋሻ የታወቀ ስመ ጥሩ ነው።

እኩሌቶቹም የግሪክ ደሴቶች ከባሕር ወደ ውጪ እየተወረወሩ የወጡ ይመስላሉ። እኩሌቶቹም ከጥንት ጀምረው ይታዩ የነበሩት ያሉበት አይታወቅም ጠፍተዋል። ይህ እንግዳ ነገር እንዲህ እንዲሆን ያደረገው ከባሕር በታች የተነሳው እሳተ ጎመራ ነው።

በደቡብ ግሪክ ወገን ባሉት ደሴቶች አየሩ በአሜሪካ እንዳለው እንደ ቨርጂኒያ ግዛት አየር ቀላል ነው። በዚህ አገር ብዙ አይነት ፍሬ ሁሉ ሞልቶዋል። በሰሜን በኩል ደግሞ አየሩ ቅዝቃዜ ያለበት ነው።

በየጠረፉ የመርከብ መቋሚያዎች ወደቦች ይገኛሉ። ብዙዎቹ የአገሩ ሰዎችም መርከበኞች ናቸው። በደኑም ፓይን (ጥድ) የተባለው ጠንካራ ዛፍ ይገኛል። በላይኛው አውራጃ ኦክ የተባለው ዛፍ ይገኛል። ወደታች ባለው ክፍልም ቸስትነትዋልነት የሚባሉት ዕንጨቶች ይገኛሉ።

በዚህ ስፍራ የሚገኘው ዋናው ነገር ደረቅ ፍራፍሬ፣ ዘቢብጥጥሐር ጠጉርሩዝትንባሆበቆሎ ነው። የእጅ ሥራ ጥቂት ነው። በቤት የተለመደ ሥራ እንደ ጥጥ እንደ ጠጉር እንደ ሐር የመሰለ ነገር ነው። ቀለም ማግባት ወይም መቀባት በጣም የተለመደ ከሆነ ብዙ ጊዜው ሆነው።

ከዛፎች ፍሬ ዋነኛው ወይራ ሲሆን በብዛት ይተከላል። ወይን፣ በኽረ? ሎሚበለስ፣ አልሞንድ (ለውዝ)፣ ተምርሴትሮን፣ ፓሜግራኔት (ሮማን)፣ ኩሬንትም ይበቅላሉ።


መለጠፊያ:Link FA