ከ«መስ-አኔ-ፓዳ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
No edit summary
r2.7.1) (ሎሌ መጨመር: he:מש-אנה-פדה
መስመር፡ 20፦ መስመር፡ 20፦
[[es:Mesanepada]]
[[es:Mesanepada]]
[[fr:Mesannepada]]
[[fr:Mesannepada]]
[[he:מש-אנה-פדה]]
[[ko:메산네파다]]
[[it:Mesannepada]]
[[hu:Meszannepadda]]
[[hu:Meszannepadda]]
[[it:Mesannepada]]
[[ja:メスアンネパダ]]
[[ja:メスアンネパダ]]
[[ko:메산네파다]]
[[pl:Mesanepada]]
[[pl:Mesanepada]]
[[ru:Месанепада]]
[[ru:Месанепада]]

እትም በ20:40, 10 ኦገስት 2011

መስ-አኔ-ፓዳሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ላይ የኡር መጀመርያው ንጉሥ ነበረ። በዚያው ዝርዝር ዘንድ የኡሩክን ንጉሥ ሉጋል-ኪቱንን አገልብጦ ለ80 ዓመታት ነገሠ። ከሥነ ቅርስ በዕውኑ እንደ ነገሠ እርግጥኛ ቢሆንም፣ እንዲህ ያለ ረጅም ዘመን እንደ ገዛ ግን አጠያያዊ ነው።

እስከዚህ ድረስ፣ ለሱመር ላዕላይነት ዋና ተዋዳዳሪዎች ኡሩክና ኪሽ ነበሩ። ጊልጋመሽ የኪሽን ንጉሥ አጋን አሸንፎ ኒፑርንም ከተማ ይዞ ላዕላይነቱን ለኡሩክ መሠርቶ ነበር። አሁን ግን ይህ ሁኔታ ተቀየረ፤ የኡርም ንጉሥ መስ-አኔ-ፓዳ ተነሥቶ ኡሩክን፣ ኪሽን፣ ኒፑርንና መላ ሱመርን ያዘ። ከዚያ በኋላ «የኪሽ ንጉስ» የሚለው ማዕረግ ወሰደ።

ቱማል ጽሑፍ በተባለው ጽላት፣ ከጊልጋመሽ ልጅ ኡር-ኑንጋል ቀጥሎ መስ-አኔ-ፓዳ የኒፑርን ዋና መቅደስ ጠባቂ ነበረ።

መስ-አኔ-ፓዳ ለማሪ ንጉሥ (በሶርያ) ስጦታ እንደ ላከ ከሥነ ቅርስ ይታወቃል፤ አንድ ዶቃ እዚያ ተገኝቶ በጽሕፈቱ መስ-አኔ-ፓዳ የመስካላምዱግ ልጅ ይባላል። እንዲሁም በኡር በንጉሣዊ መቅብሮች የመስ-አኔፓዳና ቀዳሚዎቹ የመስካላምዱግ፣ የአካላምዱግና የንግሥት ፑአቢ ስሞች ሁሉ ተመዘገቡ።

ከመስ-አቤ-ፓዳ በኋላ ልጁ መስኪአጝ-ኑና እንደተከተለው በማለት የነገሥታት ዝርዝርየቱማል ጽሑፍ ይስማማሉ። ሌላ የመስ-አኔ-ፓዳ ልጅ አ-አኔ-ፓዳ ቤተ መቅደስ በኡር አካባቢ እንዳሠራ ይታወቃል።

በመምህሩ ኤድመንድ ጎርዶን (በ1950ዎቹ) አስተሳሰብ፣ መስ-አኔ-ፓዳ እና ከሥነ ቅርስ ሌላ የታወቀ «የኪሽ ንጉስ» መሲሊም መታወቂያ አንድላይ ነበር። ምክንያቱም አንድ ተረት ወይም ምሳሌ በሱመርኛ መሲሊም ሲል፣ በአካድኛ የሆነ ተመሳሳይ ተረት የመስ-አኔ-ፓዳ ስም አለው። ነገር ግን መሲሊምና መስ-አኔ-ፓዳ በውኑ አንድ እንደነበሩ እስካሁን ምንም ማረጋገጫ ቅርስ አልተገኘም።