ከ«ሰርጌይ ብሪን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
r2.6.5) (ሎሌ መጨመር: ur:سرگرے برین
r2.7.2) (ሎሌ ማስተካከል: ur:سرگرے برن
መስመር፡ 66፦ መስመር፡ 66፦
[[tr:Sergey Brin]]
[[tr:Sergey Brin]]
[[uk:Сергій Брін]]
[[uk:Сергій Брін]]
[[ur:سرگرے برین]]
[[ur:سرگرے برن]]
[[vi:Sergey Brin]]
[[vi:Sergey Brin]]
[[zh:谢尔盖·布林]]
[[zh:谢尔盖·布林]]

እትም በ13:55, 31 ኦክቶበር 2011

ሰርጌይ ብሪን

ሰርጌይ ሚካይሎቪች ብሪን (እንግሊዘኛ: Sergey Mikhailovich Brin፤ ሩስኛ: Сергей (/ሰርገይ/) Михайлович Брин) (ኦገስት 21, 1973 እ.ኤ.አ. ተወለደ) ሩሲያዊ-አሜሪካዊ ሲሆን ጉግልን በመፍጠሩ ይታወቃል።

ሩሲያ የተወለደ ሲሆን፥ ብሪን ከላሪ ፔጅ ጋር ጉግልን ከመጀመሩ በፊት ኮምፒዩተር ሳይንስሒሳብ አጥንቷል። ብሪን ባሁኑ ጊዜ የጉግል ቴክኖሎጂ ፕሬዝዳንት በመሆኑ ወደ 14.1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ገንዘብ አለው። ይህም ከዓለም 26ኛ እና ከአሜሪካ 12ኛው ሀብታም ሰው ያደርገዋል።

የመጀመሪያ ዓመታት

ሰርጌይ በሞስኮሩሲያ ለየይሁዳ ቤተሰብ ተወለደ። 6 ዓመቱ ሲሆን ሰርጌይና ቤተሰቡ ወደ አሜሪካ መጡ። አባቱ ሚካኤል በሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ ማቲማቲሻን ሆኖ እስክ ዛሬ ድረስ ያስተምራል። የስርጂ እናት ዩጂኒያ ብሪን ማቲማቲሻንና ሲቭል ኢንጅነር ሆና ለናሳ ትሰራለች። ሳሙኤል የሚባል ታናሽ ወንድምም አለው።

ሰርጌይ በኮምፒዩተር ዕድገት ጊዜ በማደጉ የኮምፒዩተር ፍላጎቱ ከልጅነቱ ነው የጀመረው። መጀመሪያው ያገኘው ኮምፒዩተር አንድ ኮሞዶር 64 ሲሆን ይህንንም ከአባቱ ዘጠነኛው ልደት በዓሉ ላይ ነው ያገኘው። በሒሳብና ኮምፒዩተር ያለውን ተስዕጦም ገና ትንሸ እያለ ነው ያሳየው።

ትምህርት

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በፔንት ብራንች ሞንቴሶሪ ትምህርት ቤት የወሰደ ሲሆን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በኤላኖር ሩዝቬልት ትምህርት ቤት አጠናቋል። ቤተስቡም የሒሳብ ዕውቀቱንና ሩሲያኛው በማዳበር ረድተውቷል። በሴፕቴምብር 1990 እ.ኤ.አ.፣ ሰርጌይ ሒሳብና ኮምፒዩተር ሳይንስ ለማጥናት ሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ፣ ኮሌጅ ፓርክ ገባ። በሜይ 1993 እ.ኤ.አ. የባችለር ሳይንስ ካማግኘቱ በኅላ በስኮላርሺፕ ኮምፒዩተር ሳይንስን ለማጥናት ወደ ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ሄደ። ከዛም ከታሰበው ጊዜ በፊት በኦገስት 1995 እ.ኤ.አ. የማስተርስ ዲግሪውን ተቀበለ። ባሁኑ ጊዜ ግን የፒ.ኤች.ዲ. ጥናቱን ላልተወስነ ጊዜ አቋርጦ ጉግል ውስጥ እየሰራ ይገኛል።