ከ«ሴኔጋል» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
r2.7.1) (ሎሌ መጨመር: su:Sénégal
r2.6.5) (ሎሌ መጨመር: or:ସେନେଗାଲ
መስመር፡ 124፦ መስመር፡ 124፦


{{Link FA|af}}
{{Link FA|af}}

[[nso:Senegal]]


[[ace:Senegal]]
[[ace:Senegal]]
መስመር፡ 227፦ መስመር፡ 225፦
[[no:Senegal]]
[[no:Senegal]]
[[nov:Senegal]]
[[nov:Senegal]]
[[nso:Senegal]]
[[oc:Senegal]]
[[oc:Senegal]]
[[or:ସେନେଗାଲ]]
[[os:Сенегал]]
[[os:Сенегал]]
[[pa:ਸੇਨੇਗਲ]]
[[pa:ਸੇਨੇਗਲ]]

እትም በ13:14, 3 ፌብሩዌሪ 2012

የሴኔጋል ሪፐብሊክ
République du Sénégal

የሴኔጋል ሰንደቅ ዓላማ የሴኔጋል አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር Pincez Tous vos Koras, Frappez les Balafons
የሴኔጋልመገኛ
የሴኔጋልመገኛ
ሴኔጋል በቀይ ቀለም
ዋና ከተማ ዳካር
ብሔራዊ ቋንቋዎች ፈረንሳይኛ
መንግሥት
ፕሬዝዳንት
ጠቅላይ ሚኒስትር
ፕሬዝዳንታዊ-ረፐብሊክ
አብዱላዬ ዋዴ
ሼክ ሃጂቡ ሱማሬ
ዋና ቀናት
ነሐሴ 14 ቀን 1952
(ኦገስት 20, 1960 እ.ኤ.አ.)
 
ነፃነት ከፈረንሳይ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
196,723 (87ኛ)
2.1
የሕዝብ ብዛት
የ2005 እ.ኤ.አ. ግምት
 
11,658,000 (72ኛ)
ገንዘብ CFA ፍራንክ
ሰዓት ክልል UTC +0
የስልክ መግቢያ 221
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .sn

ሴኔጋል ወይም የሴኔጋል ሪፐብሊክምዕራብ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። ሴኔጋል ከምዕራብ በሴኔጋል ወንዝ፣ ከሰሜን በሞሪታንያ፣ ክምሥራቅ በማሊ እና ክደቡብ በጊኒጊኒ-ቢሳው ይዋሰናል። የጋምቢያ ግዛት እንዳለ በሴኔጋል ውስጥ ነው የሚገኘው። የሴኔጋል የቆዳ ስፋት 197,000 ካሬ ኪ.ሜ. የሚጠጋ ሲሆን የሕዝብ ብዛቱ ደግሞ ወደ 14 ሚሊዮን እንደሆነ ይገመታል። የሴኔጋል የአየር ሁኔታ የየምድር ወገብ ሲሆን ደረቅና ዝናባማ ወራት ተብሎ ወደ ሁለት ይከፈላል።

የሴኔጋል ርዕሰ ከተማ ዳካር በሀገሩ የምዕራብ ጫፍ በካፕ-ቨርት ልሳነ ምድር ላይ ይገኛል። ከባህር ጠረፍ ወደ ፭፻ ኪ.ሜ. ገደማ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የኬፕ ቨርድ ደሴቶች ይገኛሉ። በ፲፯ኛው ና ፲፰ኛው ክፍለ ዘመናት በቅኝ ገዢ መንግሥታት የተሠሩ የንግድ ተቋማት ከባህር ዳር ይገኛሉ።

ታሪክ

በአካባቢው ያሉ ግኝቶች ሴኔጋል ከጥንት ጀምሮ የሚኖርበት እንደነበረ ያሳያሉ። እስልምና የአካባቢው ዋና ሀይማኖት ሲሆን ወደ ሴኔጋል የተዋወቀውም በ11ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን እንደሆነ ይታመናል። በ13ኛውና 14ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን የማንዲንጎ ግዛት በአካባቢው ላይ ተጽኖ ያደርግ ነበር። በዚሁም ጊዜ ነው የጆሎፍ ግዛት የተመሠረተው። በ15ኛው ክፍለ-ዘመን ፖርቱጋልኔዘርላንድስ እና ኢንግላንድ በአካባቢው ለመነገድ ይወዳደሩ ነበር። በ1677 እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ጎሪ የሚባለውን ዋና የባሪያ ንግድ ደሴት ተቆጣጠረች። ከዛም በ1850ዎቹ እ.ኤ.አ. ፈረንሣይ ቁጥጥሩዋን ወደ መላው ሴኔጋል ማስፋፋት ጀመረች።

በጃኑዋሪ 1958 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋልና የፈረንሣይ ሱዳን ተቀላቅለው የማሊ ፌዴሬሽንን መሠረቱ። ይህም ፌዴሬሽን በአፕሪል 4፣ 1960 እ.ኤ.አ.ፈረንሣይ ጋር በተፈረመው የሥልጣን ዝውውር ስምምነት አማካኝ በጁን 20፣ 1960 እ.ኤ.አ. ነጻነቱን አውጀ። በውስጣዊ የፖለቲካ ውዝግቦች ምክኒያት ፌዴሬሽኑ ክሁለት ወር በኋላ ተከፈለ። ሴኔጋልም ነጻነቱን በድጋሚ አውጀ። ሊዎፖልድ ሴንግሆርም የመጀመሪያው ፕሬዘዳንት ሆኖ በኦገስት 1961 እ.ኤ.አ. ተመረጠ።

ፕሬዝዳንት ሊዎፖልድ ሴንግሆር ሀገሩን መምራት ከጀመረ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማማዱ ዲያ ጋር ባለው አለመስማማት ምክኒያት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ መፈንቅለ-መንግሥት በዲሴምበር 1962 እ.ኤ.አ. ተካሄደ። ይህ መፈንቅለ-መንግሥት ያለ ደም ፍስሻ የከሸፈ ሲሆን ማማዱ ዲያም ታሰረ። ከዛም ሴኔጋል የፕሬዝዳነንቱን ሥልጣን የሚያጠነክር አዲስ ሕገ-መንግሥት አሳለፈች። በ1980 እ.ኤ.አ. ፕሬዝዳንት ሴንግሆር በራሱ ፍቃድ ከሥልጣኑ የወረደ ሲሆን በ1981 እ.ኤ.ኣ. በራሱ በሊዎፖልድ ሴንግሆር የተመረጠው አብዱ ዲዮፍ ፕሬዝዳንት ሆነ።

ፌብሩዋሪ 1፣ 1982 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋል ከጋምቢያ ጋር ተዋሕዳ የሴኔጋምቢያ ኮንፌዴሬሽንን መሠረተች። ከስምንት ዓመት በኋላ ግን በ1989 እ.ኤ.አ. ኮንፌዴሬሽኑ ፈረሰ። ከ1982 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በደቡባዊ ሴኔጋል በካሳማንክ አካባቢ የሚገኙ አማጺዎች ከሴኔጋል መንግሥት ጋር በየጊዜው ተጋጭተዋል። ሴኔጋል ዓለም-አቀፍ ሰላም-አስከባሪ ሃይሎችን በመላክ ትታተወቃለች።

አብዱ ዲዮፍ ከ1981 እስከ 2000 እ.ኤ.አ. ድረስ ፕሬዝዳንት ነበረ። በሥልጣን ጊዜው አብዱ የፖለቲካ ተሳትፎን አበረታትቷል፣ መንግሥቱ በኤኮኖሚው ላይ ያለውን ቁጥጥር አሳንሷል፣ እና ሴኔጋል ክውጭ በተለይም ከታዳጊ ሀገሮች ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን አጠናክሯል። አብዱ ለአራት የሥራ-ጊዜዎች ፕሬዝዳንት ሆኖ አገልግሏል። በ2000 እ.ኤ.አ. በዓለም-አቀፍ ታዛቢዎች ነጻና ዲሞክራሲያዊ በተባለ ምርጫ የአብዱ ዲዮፍ ተቀናቃኝ አብዱላይ ዋዲ አሸንፎ ፕሬዝዳንት ሆኗል።

ፖለቲካ

ሴኔጋል ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ናት። ከ2001 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ፕሬዝዳንቷ በየአምስት ዓመት የሚመረጥ ሲሆን ከዛ በፊት ደግሞ በየሰባት ዓመት ነበር። ያሁኑ ፕሬዝዳንት አብዱላዬ ዋዴ ሲሆኑ በማርች 2007 እ.ኤ.አ. እንደገና ተመርጠዋል።

ሴኔጋል ከ፹ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሏት። ፓርላማዋ ሁለት ምክር ቤቶች አሉት። አንዱ ፻፳ መቀመጫዎች ያሉት የብሔራዊ ስብሰባ (እንግሊዝኛ፦ National Assembly) ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ፻ መቀመጫዎች ያሉት ሴኔት ነው። ሴኔጋል ራሱን የቻለ ህግ ተርጓሚ አካል አላት። ዳኛዎቹ የሚሾሙት በፕሬዝዳንቱ ነው።

በአሁኑ ጊዜ ሴኔጋል የዴሞክራሲ ሂደት ስኬታማ ነው ከሚባሉት የቀድሞ ቅኝ ተገዢ ሀገራት መካከል የምትጠቀስ ናት። የአካባቢ አስተዳዳሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚሾሙት። ማራባውት የሚባሉ የእስልምና ሃይማኖት መሪዎችም በሴኔጋል ጠንካራ የፖለቲካ ተፅእኖ አላቸው፡

የአመራር ክፍሎች

ሴኔጋል ወደ 14 ክልሎች ትከፈላለች። የክልሎችና የክልሎች ዋና ከተማዎች ስም ተመሳሳይ ነው።





ትላልቅ ከተማዎች

የሴኔጋል ትላልቅ ከተማዎች

ከ፪ ሚሊዮን ነዋሪዎች ያሉበት የሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር የሀገሩ ትልቁ ከተማ ነው።[1] ሁለተኛው ፭፻ ሺህ ሰዎች የሚኖሩበት ቱባ ከተማ ነው።[1][2]


ከተማ የሕዝብ ብዛት (2005 እ.ኤ.አ.)
ዳካር (ዋና ዳካር, ጉዌዲያዋዬ እና ፒኪኔ[2]) 2,145,193[1]
ቱባ (ቱባ ሞስኪ[2]) 475,755[1]
ቲዬስ 240,152[1]
ካኦላክ 181,035[1]
ምቦር 170,875[1]
ሴንት ሉዊ 165,038[1]
ሩፊስክ 154,975[1]
ዚጉዊንቾር 153,456[1]

ሕዝብ

ሴኔጋል ከ12.5 ሚልዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ አላት። ከዚህ ውስጥም ወደ ፵፪ ከመቶ በገጠር ነው የሚኖረው።

የአሜሪካ የስደተኖች ኮሚቴ ባቀረበው የ2008 እ.ኤ.አ. የዓለም ስደተኞች አጠቃላይ ቅኝት መሠረት ሴኔጋል በ2007 እ.ኤ.አ. ወደ 23,800 የሚገመቱ ስደተኞች ይኖሩባታል። ከዚህ አብዛኛዎቹ የመጡት ከሞሪታኒያ ነው። ስደተኞቹ በንድዮምዶዴል እና በሴኔጋል ወንዝ አቅራቢያ በሚገኙ ሠፈሮች ይኖራሉ።[3]

ማመዛገቢያ

  1. ^ Agence Nationale de la Statistique et de la Démographie (2005 እ.ኤ.አ.). "Situation économique et sociale du Sénégal" (PDF) (በፈረንሳይኛ). Government of Senegal. Archived from the original on 2008-06-25. በ2008-11-18 የተወሰደ.
  2. ^ Forsberg, Jan. "Cities in Senegal" (በእንግሊዝኛ). በ2008-11-18 የተወሰደ.
  3. ^ "World Refugee Survey 2008" (in እንግሊዝኛ). U.S. Committee for Refugees and Immigrants. 2008-06-19. http://www.refugees.org/survey. 
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ ሴኔጋል የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።


መለጠፊያ:Link FA