ከ«ኤንመባራገሲ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
r2.6.5) (ሎሌ ማስተካከል: hu:Mebarageszi
r2.7.3) (ሎሌ መጨመር: lt:Enmebaragesis
መስመር፡ 26፦ መስመር፡ 26፦
[[ka:ენ-მებარაგესი]]
[[ka:ენ-მებარაგესი]]
[[ko:엔메바라게시]]
[[ko:엔메바라게시]]
[[lt:Enmebaragesis]]
[[nl:Enmebaragesi]]
[[nl:Enmebaragesi]]
[[pl:Enmebaragesi]]
[[pl:Enmebaragesi]]

እትም በ09:42, 29 ዲሴምበር 2012

ኤንመባራገሲ (ወይም መ-ባራገሲ፣ ኤን-መን-ባራገ-ሲ፣ ኤንመባራጊሲ) በ24ኛው ክፍለ ዘመን አክልበ. ግድም የኪሽ ንጉሥ በሱመር ነበረ። በሱመር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ፣ «የኤላምን ጦር ያጠፋው» ሲባል 900 ዓመታት (?) ከነገሠ በኋላ በኡሩክ ንጉሥ በዱሙዚድ፣ አሣ አጥማጁ እጅ እንደ ተማረከ ይላል።

የኤንመባራገሲ መንግሥት መጀመርያው በሥነ ቅርስ የተረጋገጠው ነው። በኒፑር ከተማ ፍርስራሽ ስሙ በሁለት የአልቤስጥሮስ ስብርባሪ ላይ ተገኝቷል፤ እርሱም በዚያ ከተማ መጀመርያውን ቤተ መቅደስ እንዳሠራ የቱማል ዜና መዋዕል የተባለው ሱመርኛ ሰነድ ይለናል።[1]

የኤንመባራገሲ ስም እንደገና በ«ቢልጋመሽና አጋ» (ከሱመርኛው የጊልጋመሽ ትውፊት አንድ ምዕራፍ) ይገኛል፤ በዚህ ጽላት ኡሩክን የከበበው የኪሽ ንጉሥ አጋ አባት ይባላል። የአጋ መንግሥት ደግሞ ከሥነ ቅርስ ተረጋግጧል። የሱመር ነገሥታት ዝርዝር እና የቱማል ዜና መዋዕል በዚህ ይስማማሉ፤ በሁላቸው ዘንድ የኤንመባራገሲ ተከታይ ልጁ አጋ ነው ይላሉ። የኪሽ ንጉሥ ኤንመባራገሲ በኡሩክ ንጉሥ በዱሙዚድ እጅ ከተማረከ፣ ከዚያም የዱሙዚድ ተከታይ ጊልጋመሽ ከልጁ ከአጋ ጋር ከታገለ፣ እንግዲህ የኡሩክ ነገሥታት ዱሙዚድና ጊልጋመሽ ታሪካዊ ኅልውና እንደነበራቸው መገመት ይቻላል።

በኋላ ዘመን፣ የኡር ንጉሥ ሹልጊ በጻፈ መዝሙር ጊልጋመሽን በማመስገን ሲሄድ፣ ጊልጋመሽ እራሱ ኤንመባራገሲን የማረከውና ያሸነፈው ነበር ይላል። ይህ ግን ከሌላው ምንጭ ጋር አይስማማም፤ ኤንመባራገሲ የተማረከው ጊልጋመሽን በቀደመው በዱሙዚድ መሆኑ ስለሚባል።

ጊልጋመሽ ትውፊት በሌላ ምዕራፍ፣ ጊልጋመሽ «እኅቱን» ኤንመባራገሲ ለአስፈሪው አውሬ ለሁምባባ እንደ ሚስት ያቀርባል። ስለዚህ ስለ ኤንመባራገሲ ጾታ ትንሽ ክርክር ቢነሣም፣ በአብዛኛው ዘንድ ይህ ለቀልድ የተጻፈው አይቀርም።

የውጭ መያያዣዎች

  1. ^ "The Electronic Text Corpus of Sumerian Literature; ETCSLtranslation : t.2.1.3; The history of the Tummal". በ2008-04-22 የተወሰደ. የቱማል ዜና መዋዕል (እንግሊዝኛ)