ከ«እንግሊዝኛ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
r2.7.3) (ሎሌ መጨመር: min:Bahaso Inggirih
መስመር፡ 154፦ መስመር፡ 154፦
[[mhr:Англичан йылме]]
[[mhr:Англичан йылме]]
[[mi:Reo Pākehā]]
[[mi:Reo Pākehā]]
[[min:Bahaso Inggirih]]
[[mk:Англиски јазик]]
[[mk:Англиски јазик]]
[[ml:ഇംഗ്ലീഷ് (ഭാഷ)]]
[[ml:ഇംഗ്ലീഷ് (ഭാഷ)]]

እትም በ22:47, 8 ፌብሩዌሪ 2013

እንግሊዝኛ መደበኛ የሆነባቸው አገሮች

እንግሊዝኛ የምዕራብ-ጀርመናዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ቋንቋ ነው። በዓለም ላይ በብዙ አገራት ውስጥ ይነገራል። የመጀመሪያ ተናጋሪዎቹ ቁጥር 380 ሚሊዮን ያሕል ሲሆን በብዛት የምድር 3ኛው ቋንቋ ነው። ከዚህ በላይ እስከ 1 ቢሊዮን ሰዎች እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ይችሉታል።

እንግሊዝኛ በእንግሊዝ አገር ጀመረ። አንግል እና ሴያክስ የተባሉ ጀርመናዊ ጐሣዎች መጀመርያ የተናገሩት ጥንታዊ እንግሊዝኛ ይባላል። ነገር ግን ይህ እንደ ዛሬው እንግሊዝኛ በጣም አልመሰለም። በ441 አ.ም. ጀምረው እነዚህ ጐሣዎች ከጀርመን ወጥተው በብሪታኒያ ደሴት ሰፈሩ። ቋንቋቸውም የተጻፈበት «ሩን» በተባለው ጽሕፈት ነበር። በ7ኛ መቶ ዘመን ክርስትና ከተቀበሉ በኋላ ግን ቋንቋው በላቲን ፊደል ሊጻፍ ጀመረ።

ከ9ኛ መቶ ዘመን ጀምሮ ብዙ ሠራዊት ከዴንማርክና ከኖርዌ ወደ እንግሊዝ ስለ መጡ ተመሳሳይ ቋንቋ ስለነበራቸው ያን ጊዜ እንግሊዝኛ ከጥንታዊ ኖርስ አያሌ ቃሎች ተበደረ።

1058 ዓ.ም. ዊሊያም 1 «አሸናፊ» ከነሠራዊቱ እንግሊዝ አገርን ወርሮ ንጉስ ከሆነ በኋላ አዲስ መንግሥት ለማቆም መኳንንቶቹን ከፈረንሳይ ከሱ ጋራ አመጣ። የእንግሊዝ መንግሥት ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን ለረጅም ጊዜ (300 አመቶች) እንግሊዝኛ ከትምህርት በቶች ተከለክሎ ቋንቋው ለጽሑፍ ሳይሆን እንደ መነጋገርያ ብቻ ስለ ቀረ በዚያን ጊዜ ብዙ ተለወጠ። እንግሊዝኛ በዚሁ ዘመን እጅግ ብዙ ቃላት ከፈረንሳይኛ ስለተበደረ በፍጹም ሌላ መልክ ይዞ አሁን መካከለኛ እንግሊዝኛ ይባላል። ቻውሰር አንድ ስመ ጥሩ የመካከለኛ እንግሊዝኛ ጸሐፊ ነበር።

በ15ኛ መቶ ዘመን «ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅ» በሚባለው ለውጥ አናባቢዎቹ ተለውጠው የቋንቋው ድምጽ እንደገና ሌላ መልክ ያዘና ከዊሊያም ሼክስፒር ዘመን ጀምሮ «ዘመናዊ እንግሊዝኛ» ተብሏል።

እንግሊዝኛ ከሌሎቹ ልሣናት ለምሳሌ ከቻይንኛ፥ ከህንዲ፥ ከጃፓንኛ እና ከእስፓንኛ አንዳንድ አዲስ ቃላት ከመውሰድ አላቋረጠም። ከተለያዩ አገሮች የነበሩት ሊቃውንት እርስ በርስ ለመነጋገር የቻሉ የጋራ ካወቁት ልሳናት ከሮማይስጥና ከግሪክ የጥናቶቻቸው ቃሎች በመምረጥ ነበር። እነዚያ የተክኖሎጂ ቃሎች ደግሞ ወደ እንግሊዝኛ ገቡ፤ ለምሳሌ፣ photograph (ፎቶግራፍ) ከግሪክ photo- ፎቶ (ብርሀን) እና -graph ግራፍ (ሰዕል)፤ ወይም telephone (ተለፎን) ስልክ። ስለዚህ እንግሊዝኛ ከብዙ ቋንቋዎች ይሠራል ሊባል ይችላል።

Wikipedia
Wikipedia

መለጠፊያ:Link FA መለጠፊያ:Link FA መለጠፊያ:Link GA ak:English