ከ«ኢንዳክተር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ 69 ልሳናት አሁን በWikidata ገጽ d:q5325 ስላሉ ተዛውረዋል።
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ 1 ልሳናት አሁን በWikidata ገጽ d:q5325 ስላሉ ተዛውረዋል።
መስመር፡ 22፦ መስመር፡ 22፦


{{Link FA|tt}}
{{Link FA|tt}}

[[th:ตัวเหนี่ยวนำ]]

እትም በ14:24, 8 ማርች 2013

የተለያዩ የኢንደክተሮች ዓይነቶች

ኢንዳክተር ብዙ ጊዜ ከኤሌክትሪክ አሳላፊ ነገር ጥምጥም የሚሰራ የኤሌክትሪክ መሳሪያ ነው። ለምሳሌ በብረት ዘንግ ላይ የተጠመጠመ የመዳብ ሽቦ ኢንደክተር ይፈጥራል። ለነገሩ የግዴታ በብረት ዙሪያ ሽቦው መጠምጠም የለበትም፣ ውስጡ አየር ሊሆንም ይችላል። ሆኖም የተጠመጠመበት ነገር የበለጠ መግነጢሳዊ እየሆነ በሄደ ቁጥር በኢንደክተሩ ዙሪያ የሚፈጠረው መግነጢሳዊ መስክ የበለጠው ወደ ዘንጉ ውስጥ ስለሚገባ እልከኝነቱ እያደገ ይሄዳል[1]

ኢንደክተሮች እንዴት ነው ሚሰሩ?

ካፓሲተሮችቮልቴጅ ለውጥን እንደሚጠሉ ሁሉ ኢንደክተሮች በተራቸው የኤሌክትሪክ ጅረትን ለውጥ ይጠላሉ። ባጠቃላይ መልኩ ፣ በጊዜ የሚለዋወጠው የኢንደክተሩ ቮልቴጅ v(t) እና እልክኝነቱ L እና በውስጡ የሚያልፈው ተለዋዋጭ የኤሌክትሪክ ጅረት i(t) ዝምድና በሚከተለው የለውጥ እኩልዮሽ ይገለጻል:

በምሳሌ ለመረዳት፣ አንድ በጣም ከባድ የውሃ ተሽከርካሪ ከወንዝ ዳርቻ ቢሰራ፣ ወንዙ በስሩ ሲያልፍ ከክበደቱ አንጻር ለመሽከርከር መጀመሪያ እምቢ ይላል። አንዴ መሽከርከር ከጀመረ በኋላ ደግሞ፣ የወንዙ ፍሰት ሲቋረጥ እርሱ ግን መሽከርከሩን ባለማቋረጥ ውሃው እንዲፈስ ያደርጋል፣ በስብቀት ምክንያት ሃይሉ ተሟጦ እስካቆመ ድረስ። ኢንደክተርም እንዲሁ ነው። መጀመሪያ የኤሌክትሪክ ጅረት ሲገጥመው አላሳልፍም በማለት እልክ ይገባል። ሆኖም ቀስ ብሎ እየተላመደ ይሄድና በኋላ የኤሌክትሪክ ጅረቱ ምንጭ ሲቋረጥ እርሱ እራሱ ጅረቱን በመግፋት የኤሌክትሪክ ጅረቱ እንዲቀጥል ያደርጋል።

የኢንደክተሮች ተግባራዊ አጠቃቀም

ኢንደክተሮች ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉት በአናሎግ ዑደቶች ውስጥ ነው። የመግነጢስ ፍሰታቸው የተጣመሩባቸው ኢንደክተሮች በጣም ጠቃሚ የሆነውን ትራንስፎርመር የሚባለውን የኤሌክትሪክ መሳሪያ ይፈጥራሉ። ኢንዳክተሮች በኤሌክትሪክ ስርጭት መስመሮች ላይም እንዲሁ የሚፈጠሩ ቮልቴጆችን ለመቀነስና የተሳሳቱ ጅረቶችን ለማስተካከል ይረዳሉ።

ማጣቀሻ

  1. ^ "Inductors 101". Vishay Intertechnology, Inc. (2008-08-12). በ2010-10-02 የተወሰደ.

ተጨማሪ ንባብ

መለጠፊያ:Link FA