ከ«በር:ፍልስፍና» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ ልሳናት አሁን በ Wikidata ገጽ d:q3290113 ስላሉ ተዛውረዋል።
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ ልሳናት አሁን በ Wikidata ገጽ d:q3290113 ስላሉ ተዛውረዋል።
መስመር፡ 126፦ መስመር፡ 126፦
[[መደብ:ፍልስፍና]]
[[መደብ:ፍልስፍና]]
[[መደብ:በር]]
[[መደብ:በር]]

[[zh-classical:門:子]]

እትም በ18:56, 23 ኦገስት 2013



ፈላስፋው
THE THINKER
ፍልስፍና የሚለው ቃል ከግሪኩ φιλοσοφία (ፊሎዞፊያ) የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ፊል መውደድ፣ ሶፊያ ጥበብ ማለት ነው። ሲጋጠም ፍልስፍና ማለት የዕውቀት ፍቅር ማለት ነው።

ጥንታዊ ግሪክ ፍልስፍና ትኩረት አጠቃላይ የሰው ልጅ ዕውቀትን መመርመር ነበር። እንደ ሂሳብ፣ ሳይንስ ያሉ ነጠላ ዕውቀቶች የመጡት ከዚህ አጠቃላይ ዕውቀት ነው። እኒህ ነጠላ ዘርፎች ማጥናት የማይችሏቸውን ሃስቦች ፍልስፍና አሁን ድረስ ያጠናል።

የፍልስፍና ጥናት ዘርፎች

ሥነ ውበት (ኤስተቲክስ) | ሥነ ዕውቀት (ኤፒስቲሞሎጂ)

ሥነ ኑባሬ (ኦንቶሎጂ) | ሥነ አምክንዮ(ሎጂክ)

ሥነ ምግባር (ኤቲክስ) | ሜታፊዚክስ| ኅልውነት

የሳይንስ ፍልስፍና | ቀልበኝነት|መዋቅራዊነት

ቁስ አካላዊነት|ማኅበረሰባዊ ፍልስፍና |አዕምሮና አንጎል

የፍልስፍና ዋና ሁለት ክፍሎች
ቁሳዊነት (ቁስ አካላዊነት)የዋህ ቁሳዊነትየቁሳዊነት ሜታፊዚክዳያሌክቲካዊ ቁሳዊነት
ሐሳባዊነት(አይዲያሊዝም)ነባራዊ ሐሳባዊነት (ኦብጀክቲቭዝም)ኅሊያናዊነት


ፍልስፍና

ፍልስፍና በተለያዩ ሰወች የተለያየ ግንዛቤና መረዳት አለው። ሆኖም ከሞላ ጎደል የፍልስፍና ዘርፎችና የሚያነሷቸው ጥያቄዎች እንዲህ ይቀርባሉ፡

  • ሜታፊዚክስ : እውንነት ምንድን ነው? እውን የሆነ/የሆኑ ምን ነገሮች አሉ? ከምናስተውለው ዓለም ውጭ ሌላ ዓለም አለ?
  • ሥነ ዕውቀት: አለምን መረዳት እንችላለን? እንዴት ማወቅ እንችላለን? ከራሳችን ውጭ ሌላ ሃሳብ እንዳለ እንዴት እናውቃለን?
  • ሥነ ምግባር: ሰናይዕኩይ (ጥሩና መጥፎ) ልዩነት አላቸው? ካላቸው እንዴት ልንለያቸው እንችላለን? ምን አይነት ምግባር ሰናይ (ጥሩ) ነው? ለአንድ ምግባር ዋጋ ለመስጠት የዋጋ ስርዓት መኖር አለበት፣ ይህ የዋጋ ስርዓት ከየት ይመነጫል? ከአምላክ? ወይስ ከየት? አንድ ምግባር ፍጹም ጥሩ ወይም ፍጹም መጥፎ ሊባል ይችላል? የራበው ሰው ቢሰርቅ ስርቆቱ ዕኩይ ነው? ወይንስ ሥነ ምግባር አንጻራዊ ነው? እንዴት ህይወቴን መምራት አለብኝ? ሁላችንስ እንዴት እንኑር?
  • ሥነ አምክንዮ፡ ትክክለኛ ሃሳብ እንዴት እናመነጫለን? አንድ ሃሳብ ስሜት የማይሰጥ መሆኑን እንዴት ማወቅ እችላለሁ? የክርክርን አሸናፊ እንዴት መለየት ይቻላል?
  • ሥነ ውበት፡ ኪነት ምንድን ነው? ውበት ምንድን ነው? የውበት ቋሚ መስፈርት አለው? ኪነት መስፈርቱ ነው? እንግዲያስ የውበት ትርጉሙ ምንድን ነው? የኪነት አላማ ምንድን ነው? ኪነት እኛን እንዴት ይነካናል?ኪነት ዕኩይ ሊሆን ይችላል?ኪነት የህብረተሰብን ኑሮ ይሸረሽራል ወይስ ያሻሽላል? አንድ ከዋኝ የሚሰራውን ያውቃል? ለምሳሌ ድራማ ላይ ፕሬዜዳንት የሆነ ከዋኒ ዕውን ፕሬዜዳንት ሆኖ ሊሰራ ይችላል? የኪነት ተግባር የውኑን አለም መኮረጅ ነው? በመኮረጁ የቱን ያክል ነባራዊውን አለም ያጣምማል?


  

ዕውቅ የምዕራቡ አለም ፈላስፋዎች


ፍልስፍና ካሳለፈው ዘመንና እንዲሁም ከጥናቱ ስፋት የተነሳ ብዙ ጊዜ በአንድ ሃሳብ ላይ የተለያዩ አቋሞች ይንጸባረቃሉ። ስለሆነም ፍልስፍናን በሃሳብ ደረጃ ከማጥናት ይልቅ "የዋና ዋናዎቹ ፈላስፋወች ሃሳብ ምን ነበር?" በማለት ማጥናት ለቀል ይችላል። የሚቀጥሉት ሰዎች ከሞላ ጎደል ዋና ዋናወቹ የምዕራቡ አለም ፈላስፋወች ናቸው። እያንዳንዳቸው ለአሁኑ የምዕራቡ አለም ፍልስፍና ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርገው አልፈዋል፦



ፓይታጎረስ


ሶቅራጠስ


ፕላቶ


አሪስጣጣሊስ


ሴኔካ


ኦግስጢን


አኩናስ


ደካርት


ሆብስ


ስፒኖዛ


ሎክ


ሌብኒዝ


ሁም


ካንት


ቤንታም


ሄግል


ሾፐናውር


ኬርክጋርድ


ማርክስ


ኒሺ


ኸስረል


ሄድጋ


ሳትራ


የዕለቱ ምርጥ የፍልስፍና ጽሑፍ

ፍልስፍና ማለት እንደኔ ፍልስፍና የገምት ወይም የጥየቄ ኪነ ጥበብ ማለት ነው ። ማለትም የፍልስፍና ውጤት በኅይወታችን ላይ ተግብርነት የለውም...።