ከ«መስ-አኔ-ፓዳ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 3፦ መስመር፡ 3፦
እስከዚህ ድረስ፣ ለ[[ሱመር]] ላዕላይነት ዋና ተዋዳዳሪዎች ኡሩክና [[ኪሽ]] ነበሩ። [[ጊልጋመሽ]] የኪሽን ንጉሥ [[አጋ]]ን አሸንፎ [[ኒፑር]]ንም ከተማ ይዞ ላዕላይነቱን ለኡሩክ መሠርቶ ነበር። አሁን ግን ይህ ሁኔታ ተቀየረ፤ የኡርም ንጉሥ መስ-አኔ-ፓዳ ተነሥቶ ኡሩክን፣ ኪሽን፣ ኒፑርንና መላ ሱመርን ያዘ። ከዚያ በኋላ «የኪሽ ንጉስ» የሚለው ማዕረግ ወሰደ።

''ቱማል ጽሑፍ'' በተባለው ጽላት፣ ከጊልጋመሽ ልጅ [[ኡር-ኑንጋል]] ቀጥሎ መስ-አኔ-ፓዳ የኒፑርን ዋና መቅደስ ጠባቂ ነበረ።
''[[ቱማል ጽሑፍ]]'' በተባለው ጽላት፣ ከጊልጋመሽ ልጅ [[ኡር-ኑንጋል]] ቀጥሎ መስ-አኔ-ፓዳ የኒፑርን ዋና መቅደስ ጠባቂ ነበረ።

መስ-አኔ-ፓዳ ለ[[ማሪ]] ንጉሥ (በ[[ሶርያ]]) ስጦታ እንደ ላከ ከሥነ ቅርስ ይታወቃል፤ አንድ ዶቃ እዚያ ተገኝቶ በጽሕፈቱ መስ-አኔ-ፓዳ የ[[መስካላምዱግ]] ልጅ ይባላል። እንዲሁም በኡር በንጉሣዊ መቃብሮች የመስ-አኔፓዳና ቀዳሚዎቹ የመስካላምዱግ፣ የ[[አካላምዱግ]]ና የንግሥት [[ፑአቢ]] ስሞች ሁሉ ተመዘገቡ። የመስ-አኔ-ፓዳ ንግሥት ኒን-ባንዳ ተባለች።

እትም በ21:31, 2 ኦገስት 2015

መስ-አኔ-ፓዳሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ላይ የኡር መጀመርያው ንጉሥ ነበረ። በዚያው ዝርዝር ዘንድ የኡሩክን ንጉሥ ሉጋል-ኪቱንን አገልብጦ ለ80 ዓመታት ነገሠ። ከሥነ ቅርስ በዕውኑ እንደ ነገሠ እርግጥኛ ቢሆንም፣ እንዲህ ያለ ረጅም ዘመን እንደ ገዛ ግን አጠያያዊ ነው።

እስከዚህ ድረስ፣ ለሱመር ላዕላይነት ዋና ተዋዳዳሪዎች ኡሩክና ኪሽ ነበሩ። ጊልጋመሽ የኪሽን ንጉሥ አጋን አሸንፎ ኒፑርንም ከተማ ይዞ ላዕላይነቱን ለኡሩክ መሠርቶ ነበር። አሁን ግን ይህ ሁኔታ ተቀየረ፤ የኡርም ንጉሥ መስ-አኔ-ፓዳ ተነሥቶ ኡሩክን፣ ኪሽን፣ ኒፑርንና መላ ሱመርን ያዘ። ከዚያ በኋላ «የኪሽ ንጉስ» የሚለው ማዕረግ ወሰደ።

ቱማል ጽሑፍ በተባለው ጽላት፣ ከጊልጋመሽ ልጅ ኡር-ኑንጋል ቀጥሎ መስ-አኔ-ፓዳ የኒፑርን ዋና መቅደስ ጠባቂ ነበረ።

መስ-አኔ-ፓዳ ለማሪ ንጉሥ (በሶርያ) ስጦታ እንደ ላከ ከሥነ ቅርስ ይታወቃል፤ አንድ ዶቃ እዚያ ተገኝቶ በጽሕፈቱ መስ-አኔ-ፓዳ የመስካላምዱግ ልጅ ይባላል። እንዲሁም በኡር በንጉሣዊ መቃብሮች የመስ-አኔፓዳና ቀዳሚዎቹ የመስካላምዱግ፣ የአካላምዱግና የንግሥት ፑአቢ ስሞች ሁሉ ተመዘገቡ። የመስ-አኔ-ፓዳ ንግሥት ኒን-ባንዳ ተባለች።

ከመስ-አቤ-ፓዳ በኋላ ልጁ መስኪአጝ-ኑና እንደተከተለው በማለት የነገሥታት ዝርዝርየቱማል ጽሑፍ ይስማማሉ። ሌላ የመስ-አኔ-ፓዳ ልጅ አ-አኔ-ፓዳ ቤተ መቅደስ በኡር አካባቢ እንዳሠራ ይታወቃል።

በመምህሩ ኤድመንድ ጎርዶን (በ1950ዎቹ) አስተሳሰብ፣ መስ-አኔ-ፓዳ እና ከሥነ ቅርስ ሌላ የታወቀ «የኪሽ ንጉስ» መሲሊም መታወቂያ አንድላይ ነበር። ምክንያቱም አንድ ተረት ወይም ምሳሌ በሱመርኛ መሲሊም ሲል፣ በአካድኛ የሆነ ተመሳሳይ ተረት የመስ-አኔ-ፓዳ ስም አለው። ነገር ግን መሲሊምና መስ-አኔ-ፓዳ በውኑ አንድ እንደነበሩ እስካሁን ምንም ማረጋገጫ ቅርስ አልተገኘም።

ቀዳሚው
መስካላምዱግ
ዑር ንጉሥ (ሉጋል)
2345-2314 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
መስኪአጝ-ኑና
ቀዳሚው
ኡሩክ ንጉሥ ኡር-ኑንጋል
ሱመር (ኒፑር) አለቃ
2345-2314 ዓክልበ. ግድም