ከ«አቡነ ቴዎፍሎስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ 3 ልሳናት አሁን በWikidata ገጽ d:q3381339 ስላሉ ተዛውረዋል።
Bot: Changing ክርስትና to
መስመር፡ 37፦ መስመር፡ 37፦




[[መደብ: ክርስትና]]
[[መደብ:ተዋህዶ]]

እትም በ18:04, 21 ኤፕሪል 2017

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ

አቡነ ቴዌፍሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለተኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወፓትርያርክ ጎጃም በሚገኝው በዝነኛው ደብረ ኤሊያስ አካባቢ ከአባታቸው ከአቶ ወልደ ማርያም ውቤ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ዘርትሁን አደላሁ ሚያዝያ ፲፮ ቀን ፲፱፻፪ ዓ/ም ተወለዱ። ሲወለዱም የተሰጣቸው ስም መልእክቱ ወልደ ማርያም ነበር።

በልጅነታቸው ንባብ እና ዜማን በመምህር መሪ ጌታ ረዳኸኝ እና ግራ ጌታ ሣህሉ እዚያው የተወለዱበት አካባቢ ተምረዋል። ኋላ የቅኔ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ዝንባሌ ስላደረባቸው እዚያው ደብረ ኤሊያስ ደብር መምህር ገብረ ሥላሴ በሚባሉ ሊቅ ሥር መማር ጀመሩ።

፲፱፻፻፳ ዓ/ም ወደ አዲስ አበባ መጥተው ፍትሐ ነገሥትአዲስ ኪዳንን በመምህር ተክሌ (ነቡረ ዕድ በኋላ ቢትወደድ አቡነ ዮሐንስ) በመባል የሚታወቁት መሪነት ሲከታተሉ ቆይተዋል። በዚህ ጊዜ ውስጥ የኃይማኖት ችግሮችን ለማወቅ ይፈልጉ እንደነበርና ሰፋ ያለ ዕውቀት እንደነበራቸው ይነገራል። በተጨማሪ የኃይማኖት ችግሮችን የሚመለከቱ መጻሕፍትን ሳይታክቱና ሳይሰለቹ ያነቡም ነበር።

መልእክቱ ወልደ ማርያም በ፲፱፻፴ ዓ/ም ይህን ዓለም በቃኝ ብለው ደብረ ሊባኖስ ገዳም መንኩሰው ገቡ። ከጠላት ወረራ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቀሳውስቱ በዘመናዊ የኃይማኖት ትምህርት እንዲሠለጥኑ በነበራቸው ሀሳብ መሠረት ፳ የሚሆኑ ሊቃውንት መርጠው በቤተ መንግሥቱ አካባቢ እንዲሰለጥኑ አድርገዋል። ከነኚህም አንዱ አባ መልእክቱ ወልደ ማርያም ናቸው።

ቀደም ብሎ በኢትዮጵያና በግብጽ በተደረገው ስምምነት መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያዊያን ጳጳሶች ሲሾሙ ሊቀ ሥልጣናት መልእክቱ ወልደ ማርያም ለሹመት ከተመረጡት አምስት አባቶች አንዱ ሲሆኑ ወደግብጽ ተጉዘው በእስክንድርያፓትርያርክ ዳግማዊ አቡነ ዮሳብ እጅ በካይሮ በትረ ካና ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን እሑድ ሐምሌ ፲፰ ቀን ፲፱፻፵ ዓ/ም ሊቀ ሥልጣናት መልእክቱ “ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ” ተብለው የሐረርጌ ጳጳስ ሆኑ።

ፓትርያርክነት

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወፓትርያርክ ዘ ኢትዮጵያ ካረፉ በኋላ ተከታዩን ፓትርያርክ ለመሾም በተደረገው ምርጫ በዕለቱ ተገኝተው የመረጡት ፻፵፮ አባላት ሲሆኑ ሦስቱ ዕጩዎች፦

፩) አቡነ ቴዎፍሎስ (የሐረርጌ ሊቀ ጳጳስ) - ፻፳፫ ድምጽ ፪) አቡነ ያዕቆብ (የወለጋ ሊቀ ጳጳስ) - ፰ ድምጽ ፫) አቡነ ጢሞቲዎስ (የሲዳሞ ሊቀ ጳጳስ - ፲፫ ደምጽ

አግኝተዋል። በዚህም መሠረት የፓትርያርኩ ስርዓተ ሲመት ግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፷፫ ዓ/ም በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናውኗል።

፲፱፻፷፮ ዓ/ም በኢትዮጵያ ወታደራዊው አብዮት ተለኩሶ ንጉሠ ነገሥቱ መስከረም ፪ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ/ም ከሥልጣን ሲወርዱ ወዲያው የቤተ ክርስቲያኗም ንብረት ተወረሰ። ፓትርያርኩንም ከሥልጣን ከማውረዱ በፊት ደርግ “የተሐድሶ ጉባዔ” የሚል ኮሚቴ አቋቁሞ በተለያየ ክፍል በሳቸው ላይ የማይገታ አመጽና አድማ መነሳሳት ጀመረ።

በዚህ ሁኔታ ለአንድ ዓመት ያኡል በትዕግስት ከቆዩ በኋላ በየካቲት ወር ፲፱፻፷፰ ዓ/ም የደርግ መንግሥት “ሲጠበቅ የቆየ ፍርድ” በሚል አዋጅ ከሥልጣን አውርዶ እሳቸውንና በመጨረሻ በእሳቸው የተሾሙትን ሦስት ጳጳሳት (ያሁኑ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ አንዱ ናቸው) አሰራቸው።

በኋላም ሐምሌ ፯ ቀን ፲፱፻፸፩ ዓ/ም እኒህ የቤተ ክርስቲያን መሪ፣ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ ርዕሰ ሊቃና ጳጳሳት ወፓትርያርክ ዘ ኢትዮጵያ በደርግ እጅ ተገደሉ። ቀደም ሲል “የተቀባ ፓትርያርክን ሞት ብቻ ነው የሚሽረው” የሚለውን እምነት በሚቃረን ሁኔታ ከሥልጣን አውርደው “የተቀባ ፓትርያርክ ሳይሞት በላዩ ላይ ሌላ ፓትርያርክ አይሾምም” የሚለውን ሁለተኛውን እምነት ጥሰው ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፷፰ ዓ/ም ሦስተኛው ፓትርያርክ እንዲሾሙ አደረጉ።

ዋቢ ምንጮች

  • አባ ማቴዎስ፣ “ደብረ ሥልጣን በኢየሩሳሌም” (፲፱፻፹፰ ዓ/ም)
  • ”የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እራሷን መቻል” ክፍል ፩፣ ክፍል ፪፣ ክፍል ፫

http://ethiopianorthodox.org/amharic/churchhistory/ethiopianhistory.html

  • ሰለ ቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የህይወት ታሪክ እና ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ አጭር ታሪክ(ከ፲፱፻፴ ወዲህ)

http://www.quatero.net/archives/457