ከ«ሆሣዕና በዓል» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
መስመር፡ 21፦ መስመር፡ 21፦
* http://hohitebirhan.org
* http://hohitebirhan.org


[[መደብ:ክርስትና]]
[[መደብ:ተዋህዶ]]
[[መደብ:የኢትዮጵያ በዓላት]]
[[መደብ:የኢትዮጵያ በዓላት]]

እትም በ18:21, 21 ኤፕሪል 2017

የሆሣዕና በዓል

ሆሣዕና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው።

ሆሣዕና አስቀድሞ ካለው ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን ሲሆን በዚሁ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ ሆሣዕናሁ አርዓየ… ‘ ወዘተ. በማለት ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና ሌሎችም አባቶች በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘመር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በክብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው።

አስቀድሞም በነቢየ እግዚአብሔር ዘካርያስ እንደተነገረው

‘አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበለሽ ፣አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም ሆኖ በአህያም በአህያያቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል… ሰላምን ይናገራል’’

ትንቢተ ዘካርያስ ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፱። በማለት እንደሚመጣና የሠላምንም ብሥራት እንደሚያበሥር ተናገሮ ነበር። ሲመጣም

‘‘ሁሉም ፈጥነው ልብሳቸውን ወሰዱ በሰገነቱም መሰላል እርከን ላይ ከእግሩ በታች አነጠፉት።ቀንደ መለከትም እየነፉ፣ - እዩ ነግሦአል አሉ።’’

በማለት ሊደረግለት የሚገባውን ገልጿል። መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ፣ ምዕራፍ ፱፣ ቁጥር ፲፫ ።

የሆሣዕና በዓል የቤተክርስቲያን ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሲገባ ሕዝቡ ፀበርት ወይም ዘንባባ በመያዝ ‘ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር - በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረክ ነው።’’ (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፲፯ ቁጥር ፳፮) በማለት ስለተቀበሉት ይህን በማሰብና በማድረግ ቤተክርስቲያናችን ዘንባባ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ይታደላል። በቤተክርስቲያን በአራቱም ማዕዘናት ይህን በዓል የሚጠቅሱት የቅዱስ ማቴዎስ (ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፩–፲፯)፤ የቅዱስ ማርቆስ (ምዕራፍ ፲፩ ቁጥር ፩–፲)፣ የ[ቅዱስ ሉቃስ]] (ምዕራፍ ፲፱ ቁጥር ፳፱–፴፰) እና ፤ የ[[ቅዱስ ዮሐንስ] (ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ፲፪–፲፭) ወንጌላት ይነበባሉ ።

በሆሣዕና ዕለት ከሌሎች እንስሳት ይለቅ ጌታን ለመሸከም ለክብር የተሸከመችው አህያ ናት። ጌታን የተሸከመችው አህያ ከዚያ በፊት ያላየችውና ያልተደረገላት ክብር ተደርጎላታል። አህያ ከዚህ በፊት ለኛ እህል ተሸክማ ስትሄድ ሂጂ እያልን በዱላ እንደበድባት ነበር፡ ነውም። ነገር ግን በሆሣዕና ዕለት እንኳን በዱላ ልትደበደብ ቀርቶ ሰዎች በእርሷ ላይ ለተቀመጠው ጌታ ሲሉ ልብሳቸውን ሁሉ እያነጠፉላት በንጣፍ ላይ ተራምዳለች ። ኢየሩሳለሌም ሲደርስ ከገጹ ብርሃን የተነሣ ከተማዋ ብርህት ሆነች፡፡ ሕዝቡ የሆነውን ሊያዩ ወጡ፡፡ ሕፃናት ፀሐይ ስትሰግድለት መላእክት ከበው ሲያመሰግኑት አይተው በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው የሰሌን ዝንጣፊ ይዘው ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር እያሉ አመስግነዋል፡፡ ሆሣዕና ማለት በልዕልና ጸንቶ የሚኖር መድኃኒት ማለት ነው፡፡

ዋቢ ምንጮች