ከ«እግዚአብሔር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
ለውጥ ከ95.184.101.212 ገለበጠ - የዚህ አይነት ጥያቄ ምናልባት በውይይት ገጹ ላይ ይገባ ነበር እንጂ እዚህ ዓረፍተ ነገር መሃል አይገባም
No edit summary
መስመር፡ 6፦ መስመር፡ 6፦


[[መደብ:ሃይማኖት]]
[[መደብ:ሃይማኖት]]

እዚህ ዓረፍተ ነገር መሃል አይገባም።

እትም በ15:42, 31 ኦክቶበር 2017

እግዚአብሔርግዕዝ ቋንቋ ቃል ሲሆን ትርጓሜውም እግዚእ ማለት ገዢ ወይም ጌታ ሲሆን፤ ብሔር ማለት ደግሞ የሰው ስብስብ ወይም አገር ማለት ነው። የተሟላ ትርጉም ፡ የብሔር ገዢ ከሁሉ በላይ የሆነ ፡ ዓለምን የፈጠረ ፡ ብቸኛ አለቃ ማለት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የተጻፉት በሶስት ቋንቋዎች ሲሆን የመጀመሪያው ክፍል በዕብራይስጥና በአረማይክ እንዲሁም የኋለኛው በግሪክ መሆኑ ይታወቃል። እግዚአብሔር በሚለው የግዕዝ ቃል የተተካው ስም በዋነኞቹ እና በመጀመሪያዎቹ ቅጅዎች የፈጣሪን ስም የሚወክሉት አራት የእብራይስጥ ፊደላት (יהוה) ተጽፎ የነበረ ሲሆን አጠራራቸውም ዮድ ሄ ዋው ሄ ነው። በቀድሞ ዘመን ተነባቢዎች ብቻ የሚጻፉ ሲሆን አናባቢዎችን የሚጨምረው አንባቢው በመሆኑ በዘመናችን የእነዚህን አራት ፊደላት ትክክለኛ አነባበብ በእርግጠኛነት የሚያውቅ የለም። ሆኖም ወደ ትክክለኛው በእጅጉ የሚቀርቡ ሁለት የአማርኛ አጠራሮች ይገኛሉ። እነሱም ይሖዋ እና ያህዌህ የሚሉት ሲሆኑ በ1879 የአማርኛ ትርጉም መፅሓፍ ቅዱስ አንድ ጊዜ (ይሆዋ)፣ በ1941 ትርጉም ሁለት ጊዜ (ያህዌ) አንዲሁም በአዲሱ መደበኛ ትርጉም እጅግ በርካታ ቦታ ላይ (ያህዌ) በሚል ተጽፈው ይገኛሉ።

ግዕዝ ፍልስፍና B-H-R (𐩧𐩢𐩨) የሚለው ሥር ብሔር ወይም ባሕር ከመስጠት በላይ ትርጉሙ ማናቸውም ባሕር ዓይነት፣ የዓለም፣ የሀሣብ፣ የድምጽ፣ የጠፈር፣ ወይም የመንፈስ ባሕር ቢሆን፤ ባሕሩ የባሕሩም ክፍሎች ሁሉ ወሰኖች እንዳሉባቸው በቀላል ሊገለጽ የሚችል ነው። እንግዲህ ወሰኖቹን የሚወስነው አወሳኝ ወይም ገዢው ኃይል «ብሔሩን የሚገዛ» ወይም በግዕዝ «እግዚአብሔር» በመባል ሊታወቅ ይቻላል። ይህ ላይኛ ፈቃድ ፈጣሪው ጸባይ የሰማዩ አባታችን ሲሆን ያለ እርሱ ረድኤት ምንም አለመቻሉን የሚል ግንዛቤ ነው። ስለዚህ የማናቸውም ተቃዋሚ ወይም ጋኔን ፈቃድ ቢኖር በእግዚአብሔር ፈቃድና ትግዕስት ብቻ ነው ስንኳ ለጊዜው ሊቃወሙት የሚቻለው (ኩፋሌ 10:5-7)።