ከ«ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
ሀይለ ስላሴ
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
የሺበሺን ለውጦች ወደ 197.156.77.138 እትም መለሰ።
Tag: Rollback
መስመር፡ 2፦ መስመር፡ 2፦
| ስም = ቀዳማዊ ፡ ዓፄ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ
| ስም = ቀዳማዊ ፡ ዓፄ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ
| ርዕስ = [[ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ|ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ዘኢትዮጵያ]]
| ርዕስ = [[ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ|ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ዘኢትዮጵያ]]
የስዕል_መግለጫ =በ ፲፱፻፷፱ (1969) እ.ኤ.አ.
| ስዕል = Haile Selassie (1969).jpg
| የስዕል_መግለጫ = በ ፲፱፻፷፱ (1969) እ.ኤ.አ.
| ግዛት = ከ[[ጥቅምት ፳፫]] ቀን [[1923|፲፱፻፳፫]] እስከ ፡ [[መስከረም ፪]] ፡ ቀን ፡ [[1967|፲፱፻፷፯]] ዓ.ም.
| ግዛት = ከ[[ጥቅምት ፳፫]] ቀን [[1923|፲፱፻፳፫]] እስከ ፡ [[መስከረም ፪]] ፡ ቀን ፡ [[1967|፲፱፻፷፯]] ዓ.ም.
| በዓለ_ንግሥ = ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ ዓ.ም.
| በዓለ_ንግሥ = ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ ዓ.ም.

እትም በ01:40, 1 ጃንዩዌሪ 2019

ቀዳማዊ ፡ ዓፄ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ
በ ፲፱፻፷፱ (1969) እ.ኤ.አ.
በ ፲፱፻፷፱ (1969) እ.ኤ.አ.
ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ዘኢትዮጵያ
ግዛት ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ እስከ ፡ መስከረም ፪ ፡ ቀን ፡ ፲፱፻፷፯ ዓ.ም.
በዓለ ንግሥ ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ ዓ.ም.
ቀዳሚ ንግሥት ፡ ዘውዲቱ
ተከታይ ዓፄ ፡ አምሃ ፡ ሥላሴ (በስደት)
ባለቤት እቴጌ ፡ መነን
ልጆች ልዕልት ፡ ሮማንወርቅ
ልዕልት ፡ ተናኜወርቅ
ዓፄ ፡ አምሀ ፡ ሥላሴ
ልዕልት ፡ ዘነበወርቅ
ልዕልት ፡ ፀሀይ
ልዑል ፡ መኮንን
ልዑል ፡ ሣህለ ፡ ሥላሴ
ሙሉ ስም ራስ ፡ ተፈሪ ፡ መኮንን
ሥርወ-መንግሥት ሰሎሞን
አባት ራስ ፡ መኮንን ፡ ወልደ ሚካኤል ፡ ወልደ መለኮት
እናት ወ/ሮ ፡ የሺመቤት ፡ አሊ
የተወለዱት ሐምሌ ፲፯ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም.
የሞቱት ነሐሴ ፳፩ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም.
ሀይማኖት የኢትዮጵያ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ክርስትና

ቀዳማዊ ፡ ዓፄ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ (ቀ.ኃ.ሥ.) ከጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ እስከ መስከረም ፪ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. ፡ የኢትዮጵያ ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ነበሩ። ተፈሪ ፡ መኰንን ፡ ሐምሌ ፲፮ ፡ ቀን ፡ ፲፰፻፹፬ ዓ.ም. ፡ ከአባታቸው ፡ ከልዑል ፡ ራስ መኰንን ፡ እና ፡ ከእናታቸው ፡ ከወይዘሮ ፡ የሺ ፡ እመቤትኤጀርሳ ፡ ጎሮ ፡ በተባለ ፡ የገጠር ፡ ቀበሌ ፡ ሐረርጌ ፡ ውስጥ ፡ ተወለዱ።

፲፰፻፺፱ ፡ የሲዳሞ ፡ አውራጃ ፡ አገረ ፡ ገዥ ፡ ሆኑ። በ፲፱፻፫ ዓ.ም. ፡ የሐረርጌ ፡ አገረ ፡ ገዥ ፡ ሆኑ። የሐረርጌ ፡ አገረ ፡ ገዥ ፡ ሲሆኑ ፣ በጣም ፡ ብዙ ፡ ሺህ ፡ ተከታዮች ፡ ነበሩዋቸውና ፡ ልጅ ፡ እያሱን ፡ ከእንደራሴነት ፡ በኅይል ፡ እንዳያስወጡ ፤ እያሱም ፡ ተፈሪን ፡ ከሐረር ፡ አገረ ፡ ገዥነት ፡ እንዳይሽሯቸው ፡ የሚል ፡ ስምምነት ፡ ተዋዋሉ። ዳሩ ፡ ግን ፡ እያሱ ፡ ሃይማኖታቸውን ፡ ከክርስትና ፡ ወደ ፡ እስልምና ፡ እንደቀየሩ ፡ የሚል ፡ ማስረጃ ፡ ቀረበና ፡ ብዙ ፡ መኳንንትና ፡ ቀሳውስት ፡ ስለዚህ ፡ ኢያሱን ፡ አልወደዱዋቸውም ፡ ነበር። ከዚህም ፡ በላይ ፡ እያሱ ፡ ተፈሪን ፡ ከሐረር ፡ ከአገረ ፡ ገዥነታቸው ፡ ለመሻር ፡ በሞከሩበት ፡ ወቅት ፡ ስምምነታቸው ፡ እንግዲህ ፡ ተሠርዞ ፡ ተፈሪ ፡ ደግሞ ፡ ለወገናቸው ፡ ከስምምነቱ ፡ ተለቅቀው ፡ በዚያን ፡ ጊዜ ፡ እሳቸው ፡ እያሱን ፡ ከእንደራሴነት ፡ አስወጡ። እንግዲህ ፡ በ፲፱፻፱ ፡ ዓ.ም. ፡ መኳንንቱ ፡ ዘውዲቱን ፡ ንግሥተ ፡ ነገሥት ፡ ሆነው ፡ አድርገዋቸው ፡ ተፈሪ ፡ ደግሞ ፡ እንደራሴ ፡ ሆኑ። ከዚህ ፡ ወቅት ፡ ጀምሮ ፡ ተፈሪ ፡ በኢትዮጵያ ፡ ውስጥ ፡ ባለሙሉ ፡ ሥልጣን ፡ ነበሩ። በመስከረም ፳፯ ፡ ቀን ፡ ፲፱፻፳፩ ፡ ዓ.ም. ፡ የንጉሥነት ፡ ማዕረግ ፡ ተጨመረላችው። በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም ፡ ንግሥት ፡ ዘውዲቱ ፡ አርፈው ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ሆኑና ፡ ጥቅምት ፳፫ ፡ ቀን ፡ ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. ፡ ብዙ ፡ የውጭ ፡ ልዑካን ፡ በተገኙበት ፡ ታላቅ ፡ ሥነ-ሥርዓት ፡ ቅብዓ ፡ ቅዱስ ፡ ተቀብተው ፡ እሳቸውና ፡ ሚስታቸው ፡ እቴጌ ፡ መነን ፡ ዘውድ ፡ ጫኑ።

ቀዳማዊ ፡ ዓፄ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፤ ንጉሠ-ነገሥት ፲፱፻፳፫ - ፲፱፻፷፮

በንግሥ ፡ በዓሉ ፡ ዋዜማ ፡ ጥቅምት ፳፪ ፡ ቀን ፡ የትልቁ ፡ ንጉሠ-ነገሥት ፡ የዳግማዊ ፡ ዓፄ ፡ ምኒልክ ፡ ሐውልት ፡ በመናገሻ ፡ ቅዱስ ፡ ጊዮርጊስ ፡ ቤተ-ክርስቲያን ፡ አጠገብ ፤ ለዘውድ ፡ በዓል ፡ የመጡት ፡ እንግዶች ፡ በተገኙበት ፡ ሥርዐት ፣ የሐውልቱን ፡ መጋረጃ ፡ የመግለጥ ፡ ክብር ለብሪታንያ ፡ ንጉሥ ፡ ወኪል ፡ ለ(ዱክ ፡ ኦፍ ፡ ግሎስተር) ፡ ተሰጥቶ ፡ ሐውልቱ ፡ ተመረቀ።

ለንግሥ ፡ ስርዐቱ ፡ ጥሪ ፡ የተደረገላቸው ፡ የውጭ ፡ አገር ፡ ልኡካን ፡ ከየአገራቸው ፡ ጋዜጠኞች ፡ ጋር ፡ ከጥቅምት ፰ ፡ ቀን ፡ ጀምሮ ፡ በየተራ ፡ ወደ ፡ አዲስ ፡ አበባ ፡ ገብተው ፡ ስለነበር ፡ ሥርዓቱ ፡ በዓለም ፡ ዜና ፡ ማሰራጫ ፡ በየአገሩ ፡ ታይቶ ፡ ነበር። በተለይም ፡ በብሪታንያ ፡ ቅኝ ፡ ግዛት ፡ በጃማይካ ፡ አንዳንድ ፡ ድሀ ፡ ጥቁር ፡ ሕዝቦች ፡ ስለ ፡ ማዕረጋቸው ፡ ተረድተው ፡ የተመለሰ ፡ መሢህ ፡ ነው ፡ ብለው ፡ ይሰብኩ ፡ ጀመር። እንደዚህ ፡ የሚሉት ፡ ሰዎች ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ ስለ ፡ ፊተኛው ፡ ስማቸው ፡ «ራስ ፡ ተፈሪ» ፡ ትዝታ ፡ ራሳቸውን ፡ «ራስታፋራይ» ፡ (ራሰተፈሪያውያን) ፡ ብለዋል።

ዓጼ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ ዘውድ ፡ እንደጫኑ ፡ የአገሪቱን ፡ የመጀመሪያ ፡ ሕገ-መንግሥት ፡ እንዲዘጋጅ ፡ አዝዘው ፡ በዘውዱ ፡ አንደኛ ፡ ዓመት ፡ በዓል ፡ ጥቅምት ፳፫ ፡ ቀን ፡ ፲፱፻፳፬ ፡ ዓ.ም. ፡ በአዲሱ ፡ ምክር ፡ ቤት ፡ (ፓርላማ) ፡ ለሕዝብ ፡ ቀረበ። ከዚህም ፡ በላይ ፡ ብዙ ፡ የቴክኖዎሎጂ ፡ ስራዎችና ፡ መሻሻያዎች ፡ ወደ ፡ ኢትዮጵያ ፡ ከውጭ ፡ አገር ፡ አስገቡ።

፲፱፻፳፰ ዓ.ም. ፡ የሙሶሊኒፋሺስት ፡ ሠራዊት ፡ ኢትዮጵያን ፡ በወረረ ፡ ጊዜ ፡ ጃንሆይ ፡ ሕዝባቸውን ወራሪውን በሙሉ ለመቃወም እንዳስነሡና የከተት ዐዋጆቻቸው በታሪክ ገጾች ይዘገባሉ። በዐዋጅ መሠረት የዘመቻው ጊዜ እስቲያልቅ ድረስ ለሚታግሉ ነጋዶች ከቀረጥ አስተስርየት ሰጣቸው። እራሳቸው በቆራጥነት ፡ ከታገሉ ፡ በኋላ ፡ የጠላቱ ፡ ጦር ፡ ኅይል ፡ ግን ፡ በመጨረሻ ፡ ወደ ፡ እንግሊዝ ፡ አገር ፡ ለጊዜው ፡ አሰደዳቸው። ወደ ፡ ጄኔቭስዊስ ፡ ወደ ፡ ዓለም ፡ መንግሥታት ፡ ማኅበር ፡ ሄደው ፡ ስለ ፡ ጣልያኖች ፡ የዓለምን ፡ እርዳታ ፡ በመጠየቅ ፡ ተናገሩ። የዓለም ፡ መንግሥታት ፡ ግን ፡ ብዙ ፡ አላደረጉም። በ፲፱፻፴፪ ዓ.ም. ፡ ግን ፡ አውሮፓ ፡ ሁሉ ፡ በሁለተኛው ፡ የዓለም ፡ ጦርነት ፡ ተያዘ። የእንግሊዝ ፡ ሠራዊቶች ፡ ለኢትዮጵያ ፡ አርበኞች ፡ እርዳታ ፡ በመስጠት ፡ ጣልያኖች ፡ ተሸንፈው ፡ በ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. ፡ ኢትዮጵያን ፡ ተዉ። ዓፄ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ አዲስ ፡ አበባን ፡ እንደገና ፡ የገቡበት ፡ ቀን ፡ ከወጡበት ፡ ቀን ፡ በልኩ ፡ ዕለት ፡ አምስት ፡ ዓመት ፡ በኋላ ፡ ነበረ።

ልጅ ፡ ተፈሪ ፡ መኮንን ፡ በ፲፰፻፺፪ ዓ.ም.

ከዚህ ፡ በኋላ ፡ በ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ፡ የሕዝቦችን ፡ መብቶችና ፡ ተከፋይነት ፡ በመንግሥት ፡ አስፋፍቶ ፡ ሁለቱ ፡ ምክር ፡ ቤቶች ፡ እንደመረጡ ፡ አደረገ። በ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ፡ ግርማዊነታቸው ፡ የአፍሪካ ፡ አንድነት ፡ ድርጅት ፡ በአዲስ ፡ አበባ ፡ እንዲመሠረት ፡ ብዙ ፡ ድጋፍ ፡ ሰጡ። በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. ፡ ወደ ፡ ካሪቢያን ፡ ጉብኝት ፡ አድርገው ፡ የጃማይካ ፡ ራስታዎች ፡ ተገኛኙ። በ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. ፡ በማርክሲስት ፡ አብዮት ፡ ደርግ ፡ ሥልጣን ፡ ያዙና ፡ እሳቸው ፡ በእሥር ፡ ቤት ፡ ታሰሩ። በሚከተለው ፡ ዓመት ፡ ከተፈጥሮ ፡ ጠንቅ ፡ እንደ ፡ አረፉ ፡ አሉ ፤ ሆኖም ፡ ለምን ፡ እንደ ፡ ሞቱ ፡ ስለሚለው ፡ ጥያቄ ፡ ትንሽ ፡ ክርክር ፡ አለ። ብዙ ፡ ራስታዎች ፡ ደግሞ ፡ አሁን ፡ እንደሚኖሩ ፡ ይላሉ።

ስያሜያቸው

የዓፄ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ የትውልድ ፡ ስም ፡ ልጅ ፡ ተፈሪ ፡ መኮንን ፡ ነው። ስመ-መንግሥታቸው ፡ ግርማዊ ፡ ቀዳማዊ ፡ ዓፄ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ዘኢትዮጵያ ፡ ነበር። ሞዓ ፡ አንበሣ ፡ ዘእምነገደ ፡ ይሁዳ ፡ ሥዩመ ፡ እግዚአብሔር ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ዘኢትዮጵያ ፡ የሚለው ፡ የሰሎሞናዊ ፡ ሥረወ-መንግሥት ፡ ነገሥታት ፡ መጠሪያም ፡ በንጉሠ-ነገሥቱ ፡ አርማ ፡ እና ፡ ሌሎች ፡ ይፋዊ ፡ ጽሑፎች ፡ ላይ ፡ ከመደበኛው ፡ ማዕረግ ፡ ጋር ፡ ይጠቀስ ፡ ነበር። ጃንሆይታላቁ ፡ መሪ ፡ እና ፡ አባ ፡ ጠቅል ፡ በመባልም ፡ ይታወቁ ፡ ነበር።

ጥቅስ

«የእኔንም የሕይወት ታሪክ አንዳንድ ሰዎች ባለማወቅና በመሳሳት ፡ ወይም በምቀኝነት ፡ እውነት አስመስለው ጽፈው ፤ ሌሎችን እንዲመስላቸው ለማድረግ በፈትኑ ፤ የውነተኛውን ነገር ከስፍራው ሊያናውጹት አይችሉም። »

ሕይወቴና ፡ የኢትዮጵያ ፡ እርምጃ (መቅደም)


«ማናቸውም ትንሽ አገር በመጨረሻው ነጻነቱን ለማረጋገጥ የሚያገለግል አስተዋይ ውሳኔ ለመፈጽም፣ ያው ውሳኔ አድራጊዎቹን በመመዝን ሲመሠረት፣ ተስፋ ለማድረግ አይችልም፣ ዛሬ እንዲህ ያለ ምዝና ሊገኝ ገና አይችልምና። እኛ ምርጫችንን ለማድረግ፣ እና አሜሪካዊ ዘይቤ ለመበደር «ተነሥና ተቆጠር»፣ ብቻ እንችላለን።»

- 2 June 1954 ከንግግራቸው ለአሜሪካ ኮንግሬስ ውጭ ጉዳይ ጉባኤ ዋሺንግተን[1]


ዋቢ ምንጭ


  1. ^ የጉብኝታቸው ፶ኛ በዓል ማስታወሻ (እንግሊዝኛ)